AHBASH

 • ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!!

  1 The New Package of Conspiracies Being Hatched Against Ethiopian Muslims ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!! እጅግ ሰላማዊ እንቅስቃሴያችን አልሀምዱሊላህ ጥሩ እየሄደልን ይገኛል፡፡ አሁንም ግን እንቅስቃሴያችንን ወደሌላ አቅጣጫ አስይዞ ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ መጅሊስና በፊደራል ጉዳዮች ስር የሚገኘው የደህንነት ክፍል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ በመሆኑም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተጠናክረን ጥያቄያችን ህዝባዊና ሰላማዊ መሆኑን በተጨባጭ ማረጋገጥ ይጠበቅብናል፡፡ ተስፋ የምንቆርጥበት ወቅት ላይ አደለንም! አይጥ ወልዳ ወልዳ ጅራቷ ሲቀር ሲጥ የሚለው ተረት እ...ኛ ላይ እውን እንዳይሆን ተጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ከአስተማማኝ ምንጮች በተገኘ መረጃ መሰረት የደህንነት ክፍሉ (በፌደራል ጉዳዮች ስር ያለው) የሚከተሉትን እቅዶች በመተግበር ትግላችንን ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ አስቧል፡፡ አንዳንዶቹ ታምኖባቸው መተግበር የጀመሩ ሲሆን ቀሪዎቹ ገና ያልተወሰነባቸው ናቸው፡- 1. በተቻላቸው መጠን ተጻራሪ ቡድን (ተቃራኒ ቡድን) መፍጠር ይፈልጋሉ፡፡ ሽኩቻው በህዝብና በህገወጦቹ የመጅሊስ አመራር አባላት መካከል መሆኑ ቀርቶ በሁለት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች መካከል እንዲሆን ይፈልጋሉ - በሱፊያና በወሀብያ፡፡ የአወሊያውን ተቃውሞ የሚቃረንና የሚያወግዝ ሌላ ተቃዋሚ ሃይል እንዲኖርም ይፈልጋሉ፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በመስጊድ ኢማሞች በኩል ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበረ መሆኑን ሰሞኑን ሲያዘጋጁ በነበሩት ስብሰባዎች መረዳት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ሸክ ሰይድ የበኒው ለሚቀጥለው ሳምንት ንግግር በድጋሚ እንዲያደርጉ የታሰበ ሲሆን በሙሉ ፍቃደኝነት ሰውየውም ተስማምተው ‹ይቃወሙኛል፤ ተቃውሞ ያስነሱብኛል› ያሉዋቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ሰጥተዋል፡፡ ፖሊስና ደህንነትም ተዘጋጅቶላቸዋል - የኢህአዴግ ጥበቃ ሲራጥን የሚያሻግራቸው ይመስል! ይህንኑ ሱፊያ ወሀቢያ ጸብ ለመፍጠር ካሰቡት ዋነኛ ነገር አንዱ መውሊድን አጀንዳ ማድረግ ነው፡፡ መውሊድን በአዲስ መልኩ በሁለት ከተሞች ድል አድርገው ለማክበር አስበዋል፡፡ መጅሊስ ይህንን እንዲያስፈጽምም ስራ ተሰጥቶታል፡፡ አንደኛው መውሊድ የሚከበረው ኦሮሚያ ክልል ደራ ላይ ሲሆን በቱሎቪዥን ከፍተኛ ሽፋን ይሰጠዋል፡፡ የመስጊድ ኢማሞችና ሸኮች አንድ ሳይቀሩ እዚያ የሚሄዱ ሲሆን አሕባሽ ላይ የተወራው ሁሉ ውሸት መሆኑን የሚያስተምሩ የአህባሽ አባላት ተዘጋጅተዋል፡፡ ይህኛው ፕሮግራም ሲጠናቀቅ ወሎ ከልል ላይም ተመሳሳይ ዝግጅት ሊደረግ ታስቧል፡፡ በዚህም መውሊድን አስታክከው የቀድሞው ጭቅጭቅ እንዲነሳ እየሰሩ ናቸው፡፡ ሰዉን በማሳወቅ ከወዲሁ ሙከራቸውን በአላህ እርዳታ ማክሸፉ ደግሞ ውዱ ነቢይ ከኛ የተቀበሉት በይዓ መቋጠሪያ ነው! ሙስሊሞች ሆይ ንቁ! የነቢዩን ልደት አስታከው አንድነታችንን ሊበትኑ አስበዋል! ታላቁን ነቢይ የሚወድ ሁሉ ሸራቸውን በመመለስ ይተባበር አላሁ አክበር! 2. መጅሊስ ይውረድ የሚለውን ህዝባዊ ጥያቄ የአወሊያ ትምህርት ቤት ጉዳይ አንደሆነ አድርገው አጀንዳ ለማሳጣት የአወሊያን አስተዳደር ለህዝብ ለመመለስ አስበዋል፡፡ በዚህም ጥያቄያችን ተመልሷል የሚሉ ጥቂት ሰዎችን ለማራቅ ያስባሉ፡፡ ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ወተማዎችን (የአወሊያን ወላጅ ተማሪ ማህበር) በማነጋገር ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ወተማን ነጥሎ ከነሱ ወገን በማሰለፍ አጀንዳ ለማሳጫነት ሊጠቀማቸው አስቧል፡፡ እኒህ ሰዎች በእርግጥ ተታለዋል!!! ጥያቄያችን የአወሊያ አይደለም! አወሊያ መፍትሄ ቢሰጠው እሰየው ከአራቱ ጥያቄያችን አንዱ ተመለሰ ከማለት ውጪ ሶስቱን ጥያቄዎቻችንን በፍጹም አንረሳም! አላሁ አከበር! 3. መጅሊሱ ላይ የተፈጠረውን ጥያቄ ለማብረድ የተወሰኑ ሰዎችን ከመጅሊሱ ለማባረር ያስባሉ፡፡ በዚህም ሶስት ሰዎችን (ጀማልን፣ አህመዲን አብዱላሂን፣ አልሙሀመድ ሲራጅን) ለማባረርና እነ አዛምን የመሳሰሉ በህዝብ የማይታወቁ አህባሾችን እዚያው አስቀርተው ጉዳዩን ለማብረድ ይሸሉ! ልብ እንበል! የእኒህ ሰዎች መባረር ጥሩ ዜና ነው፡፡ ጥያቂያችን ግን የምናምንባቸው መሪዎች በነጻ ህዝባዊ ምርጫ ይምጡ እንጂ ጥቂት ሙሰኞች ይባረሩልን አይደለም! ሙስሊሞች ሆይ ንቁ!!! የምርጫው ጥያቄ ገፍቶ የሚመጣ ከሆነ (እኛ ታግሰን ተቃውሞዋችንን ከቀጠልን ማለት ነው) ከአመት በኋላ እንዲደረግ ሊያደርጉና ‹‹ወሃቢያ›› እንዳይገባበት ካሁኑ ሊያመቻቹ አስበዋል፡፡ እነሱ ወሀቢያ የሚሉት ደግሞ የታወቀ ነው - መብቴን ያለ ሁሉ ወሀቢያ ነው እነሱ ዘንድ፡፡ ‹ሶላት ልስገድ፣ ሂጃብ አልከልከል› ያለች ሁሉ ናት ወሀቢያ The New Package of Conspiracies Being Hatched Against Ethiopian Muslims to Abort our Civilized and Peaceful Revolution!!!! 2 በነሱ ዘንድ! ይህንንም እውን ለማድረግ ካሁኑ ሰዎችን በስራቸው እያደራጁ ነው፡፡ በ1992 ‹‹ምርጫም›› ልክ እንዲሁ ነበር ያደረጉት… አስታውሱ!!! 4. የአወሊያው ተቃውሞ አሰሚ ህዝብ ብጥብጥ ውስጥ እንዲገባ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተው አልሳካለት ብሎዋቸው ነበር፡፡ አሁን ግን ለብጥብጥ ለማነሳሳት አንድ መላ መጣልን ሲሉ ተመካክረዋል፡፡ ይሀም ከኮሚቴ አባሎች የተወሰኑትን ሰበብ ፈልጎ እስር ቤት መክተት ነው፡፡ ሊያስከስስ የሚችል ነገር እንዲፈለግባቸው እየተደረገ ነው፡፡ ከዚያ ‹‹ያሰርናቸው በወንጀል ነው፤ ከዚህ ጋር አይገኛኝም፤ ከህግ በላይ የሚሆን የለም› በማለት ለህዝቡ ይነግራሉ፡፡ ህዝቡ ሲቆጣ ይረብሻል ብለው አስበዋል፡፡ ያሳዝናል፡፡ እስካሁን ያልረበሽነው ስላልተቆጣን መስሎዋቸዋል!!! ያሳዝናል!!! ንቁ እንግዲህ! ረብሻ ለመንግስት የፈለገውን እንዲያደርግ፣ የፈለገውን እንዲያስርና እንዲያፍን አረንጓዴ መብራት ይሰጠዋል፡፡ ሰላማዊ ተቃውሞ ብቸኛ ምርጫችን ሆኖ መቆየት አለበት! ይህንን ለሁሉም እናሳውቅ፡፡ ሤራ በባህሪው ብዙ ነገሮችን መቋቋም ይችላል፡፡ መቋቋም የማይችለው መጋለጥን ብቻ ነው፡፡ ሕዝቡ ሴራውን ካወቀው ሊስፈጽሙት አይችሉም፡፡ ስለዚህ እንንቃ! ብልጦች አይደለንም! ብልጣ ብልጦች ግን አያታልሉንም! 5. ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ካሁን በፊት የመጅሊሱን ‹‹ኡለሞች›› እና ሌሎች ‹‹ተቃዋሚ›› ኡለሞችን በአህባሽ ዙሪያ ክርክር እንዲያደርጉ ሰብስቦዋቸው ሂደቱ ተቋርጦ ነበር፡፡ ሚኒስትሩ አሁን መልሶ ያስጀመረው ሲሆን አላማውም ለጉዳዩ የሚዲያ ሽፋን ሰጥቶ ግጭቱ የፊቂህ ኺላፍ እንዲሆን ለማድረግ ነበር፡፡ ጉዳዩን የሱፊያና የወሀቢያ የመዝሃብ ግጭት እንዲመስል በማድረግ ጥያቄውን ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ ነው አላማቸው፡፡ ሁላችንም እንንቃ!!! አህባሽ እና መጅሊስ ከመዝሀብ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም፡፡ ሁለቱም የባእድ አካላት ቅጥረኞች ናቸው!!! ሴራቸውን የማክሸፍ ሃላፊነት አለብን!!! አላሁ አክበር!!! 6. በየክፍለአገራቱ የተለያዩ ደህንነቶች ጋዜጠኛ መስለው እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡ ስለአህባሽ ያለውን ችግር ምንድነው ልንዘግብ ፈልገን ነው እያሉ ጥያቄዎችን በማቅረብና ኢንተርቪ በማድረግ የተቃውሞውን አንቀሳቃሾች ለይተው ለማወቅ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ሙስሊሞች ሆይ እንዳትታለሉ፡፡ ጋዜጠኛ ነኝ ብሎ የመጣ፣ የጋዜጠኛ መታወቂያ የያዘ ሁሉ ጋዜጠኛ አይደለም! ሙስሊሞች ሆይ! ታጋዮቻችሁን አጋልጣችሁ እንዳትሰጡ!!! 7. ክልሎች ላይ ያለው እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል፡፡ የምእራብ አርሲ መጅሊስ የአወሊያውን ኮሚቴ በግልጽ ደግፈው ከህዝብ ጎን በመቆም ፔቲሽን እያስፈረሙ ነው፡፡ በመጅሊሱ ፕሬዝዳንት በአህመዲን አብዱላሂ ሃገር (ሐረር ያለቸው ኮምቦልቻ ከተማ) እንኳን 21ሺ 500 በላይ ሰው ፈርሟል፡፡ ነገር ግን የክልሉ እንቅስቃሴ እስካሁን ከፔቲሽን ስላላለፈ አቃልለው ያዩት ጀምረዋል፡፡ ፔቲሽን በነሱ ቤት የህዝብ ድምፅ አይደለም እንዴ? እናም ተቃውሞው በፔቲሽን ብቻ ከቀጠለ አዲስ አበባ መጅሊስን ብቻ ለቅቀው ለምርጫ ነጻ ለማድረግና የክልሉን በዚያው በፌዴራሉ ለመቀጠል አስበዋል፡፡ አላሁ አክበር! የከልል ወንድሞቻችን ንቁ! ሰላማዊ የፔቲሽን ትግላችሁ ወደሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ካልተቀየረ ዋጋ የለውም!!! ምነው! አወሊያ ብቻ ነው እንዴ የተቃውሞ ቦታ!!! እነዚህ በሙሉ ስራ ላይ ውለዋል ማለት አይደለም፡፡ ገና ያልተወሰነባቸውና በጭቅጭቅ ላይ ያሉ ነጥቦች አሉ፡፡ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ውስጥ በዚህ ሳምንት ከፍተኛ ክርክር ሲደረግበት ነበር፡፡ ብዙዎቹ ‹‹ይበቃናል፤ እዚህ ጉድ ውስጥ እያታለለ የከተተን ጦሰኛው መጅሊስ ስለሆነ መፍትሄው ስልጣኑን ለህዝበ ሙስሊሙ መመለስ ነው›› በሚል ቢከራከሩም ፌደራል ጉዳዮችና በስሩ ያሉት የደህንነት ክፍሎች ግን በግትርነታቸው ቀጥለው እስከመጨረሻው እንሞክር እያሉ ነው፡፡ ስምምነት ላይ ስላልተደረሰ ለሚቀጥለው ሳምንት ገና ተቀጣጥረዋል፡፡ ስራ ላይ እየዋሉ ያሉ በመኖራቸው ሁሉንም ለህዝቡ በማሳወቅና በተጠንቀቅ በመጠበቅ ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ ሴራ ቢሸረብም ሁልጊዜም ተስፋ መቁረጥ የለብንም፡፡ አላህ ምንጊዜም ከጎናችን ነው፡፡ ይኸው ዛሬ እንኩዋን ኢህአዴግ ሙስሊም አባላቶቹን ጠርቶ ያደረገው ስብሰባ እንዴት እንደተደመደመ አታዩም? በአላህ ተማምነን ሰላማዊ ትግላችንን ከቀጠልን ፍሬ ማፍራታችን የማይቀር ነው! አላሁ አክበር! ይህንን መልእክት ለሁሉም ማሳወቅ ግዴታችን ነውና ሙስሊሞች ተበራቱ፡፡ አላህ ‹‹ወበሺሪል ሙእሚኒን›› ያለበት ድል ሩቅ አይደለም! አላሁ አክበር ሚን ኩሊ ከቢር! ወመከሩ ወመከረላሁ ወላሁ ኸይሩል ማኪሪን!!! ድምፃችን ይሰማ!!! Source: Face Book Read more
 • የአዲስ አበባ ከንቲባ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ ጋር ዉይይት ለማድረግ

  በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ ቲያትር እና ባህል አዳራሽ የአዲስ አበባ ከንቲባ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ ጋር ዉይይት ለማድረግ ፕሮግራም ይዘዉ ነበር::ከመንግስት በኩል ጥሪ የተደረገዉ ከየክ/ከተማዉ አስር አስር ሰዎች ብቻ ሲሆን ሙስሊሙ ግን ጉዳዩ የሁላችንም ነዉ በማለት በጠዎቱ ወደ ስብሰባ አዳራሽ ጉዞዉን ተያያዘዉ::ከጠዎቱ 3:00 ሰአት ላይ አዳራሹን ህዝበ ሙስሊሙ ጢም አደረገዉ::የከተማዉ ከንቲባን ህዝቡ በጉጉት እየጠበቀ ባለበት ሰአት አንድ የአህባሽ ቅጥረኛ መሆኑ ህዝቡ የሚያዉቀዉ ወደ አዳራሹ ዘዉ ብሎ ገባ በአዳራሹ የሚገኘዉ ህዝብ ሰዉየዉን እንደተመለከቱት ከአዳራሹ ለማስወጣት ደቂቃ አልፈጀባቸዉም ህዝቡ ከመቀመጫዉ በመነሳት በተክቢራ አዳራሹን አናወጠዉ ሰዉየዉም እጅግ በጣም ከመደንገጡ የተነሳ አይኑ ፈጠጠ ህዝቡ ዉጣ!!ዉጣ!!ሸይጣን!!በማለት ከአዳራሹ እንዲወጣ ጮሁበት ሰዉየዉም በገባበት በር ዉልቅ ብሎ ወጣ የህዝቡ አንድነት በጣም የሚገርም ነበር አብዛኛዉ ህዝብ በሸሚዙ ኪስ ላይ መጅሊስ አይወክለኝም የሚል መፈክር ለጥፈዉ ነበር ሰአቱ መንጎዱን አላቆመም የሚጠበቁት ክቡር ከንቲባ በሰአቱ አልተገኙም ሙስሊሙ ግን በትግስት እየጠበቃቸዉ ነዉ ወደ አዳራሹ አንድ የመጅሊስ ተላላኪ ወደ አዳራሹ ዘዉ ብሎ ገባ ለሁለተኛ ጊዜ አዳራሹ በተክቢራ ተናወጠ ሰዉየዉን አንጠልጥለዉ ከአዳራሹ አስወጡት ከዚህ ቡሀላ የስብሰባዉ መካሄድ አጠራጣሪ ሆነ::አዳራሹ መያዝ ከሚችለዉ በላይ በህዝበ ሙስሊሙ በመሞላቱ የመዘጋጃ ቤት ፓሊሶች ወደ አዳራሹ እየመጣ ያለዉን ህዝብ በበሩ ላይ እንዲቆም አደረጉት በዉጪ በር ላይ እንዲቆ ምየተደረገዉ ህዝብ በአዳራሹ ከተገኘዉ ህዝብ በጠም የበለጠ ነበር::ህዝቡ እንገባለን ፓሊስ ደግሞ አዳራሹ ሞልቷል በማለት ሙግቱ ቀጠለ::በዚ ሰአት ከአዳራሹ የተወሰኑ ሰዎች በመዉጣት በዉጪ ያሉትን ሰዎች ለማረጋጋት ሞከሩ::ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ወደ አዳራሹ የመንግስት ተወካዬች እየመጡ ነዉ ስለተባለ አዳራሹ በፀጥታ ተዎጠ::ወድያዉኑ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋዬ ሀ/ማርያም ወደ አዳራሹ ዘለቁ::ወደ አዳራሹ መድረክ ላይም ወተዉ በመድረክ መሪዉ ወንበር ላይ ወተዉ ተሰየሙ በአይናቸዉ አዳራሹን::ያጥለቀለቀዉን ህዝብ በአይናቸዉ ከቃኙ ቡሀላ ለህዝቡ ሰላምታቸዉን አቀረቡ:: በሞባይላቸዉ እየቀረፁ የነበሩትን ሰዎች እንዲያቆሙ ከጠየቁ ቡሀላ ድጋሚ ሰላምታ ሲያቀርቡ ሁሉም በአንድነት አልሀምዱሊላህ በማለት መለሰላቸዉ:: በመቀጠልም ጥሪያችንን አክብራችሁ የጠራናችሁም ያልጠራናችሁም ስለመጣችሁ እናመሰግናለን አሉ:: ቀጥለዉም ከግቢዉ ዉጪ በጣም ብዙ ሰዉ ስላለ እነሱ ስብሰባዉን መካፈል ስላለባቸዉና አዳራሹ ይህንን ሁላ ህዝብ ማስተናገድ ስለማይችል በሌላ ጊዜ ሰፋ ያለ አዳራሽ ይዘን እንወያያለን በማለት የዛሬዉ ስብሰባ መሰረዙን እና ለሌላ ጊዜ መዘዎወሩን ለህዝቡ አበሰሩት::ከዛም ወድያዉኑ አዳራሹን ለቀዉ ወጡ::ህዝበ ሙስሊሙ እንደተለመደዉ የመጨረሻ ተክቢራ በማሰማት ኢስላማዊ አደብ በጠበቀ መልኩ አዳራሹን በሰላም ለቀዉ ወተዎል:: አልሀምዱሊላህ ሙስሊም ላደረገን ጌታ!!!!by abu dawd Read more
 • ህዝቡ አኩሪ ጀብዶ መፈፀሙን ቀጥሏል!

  አላሁ አክበር!!አላሁ አክበር!!!!
  መጅሊስና አሕባሽ ከተንኮል ባይወገዱም
  ህዝቡ አኩሪ ጀብዶ መፈፀሙን ቀጥሏል!

  በዛሬው ዕለት ሙስሊም የአዲስ አበባ ኢሀዴግ አባላትን ለማነጋገር የኢህአዴግ ፅ/ቤት ከ2,500 በላይ አባላቱን ስብሰባ ጠራ፡፡ ስብሰባው የተካሄደው መገናኛ አካባቢ በሚገኘው ኮኮብ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነበር፡፡ የስብሰባውን ሠዓት በማክበር በቦታው የተገኙት ታዳሚዎች ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከገቡ በኋላ በመድረክ ላይ ጉብ ባሉት ሰዎች ሳይገረሙ አልቀሩም፡፡ በመቀጠልም የመድረክ ሰዎች ራሳቸውን ማስተዋወቃቸው ግድ ነበርና ማንነታቸው ታወቀ፡፡ ከሦስቱ የመድረክ ሰዎች መካከል አንደኛው ከኢህአዴግ ፅ/ቤት አቶ ፀጋዬ ሲሆኑ ሁለቱ ግን መሰሪ አጀንዳ ያነገበው ፅ...ንፈኛ ቡድን አባላት መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡ አንዱ ከመጅሊስ አቡል ሐይ ፈቲ የተባለው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከመርከዝ ነኝ ብሎ አለባብሶ ለማለፍ ሲሞክር ታዳሚው እንዲያብራራው በጠየቀው መሠረት ስሙ ኸድር እንደሚባልና ከመርከዘል አብደላህ አል-ሐረሪ የመጣሁ ነኝ ብሎ አፈነዳው-ከአሕባሽ፡፡

  ... የመድረኩ መሪ የነበሩት የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ የመድረኩን ዋና የውይት አጀንዳ ወቅታዊ እና አወዛጋቢ የሆነው ጉዳይ ዲሞክራሲችን ላይ ጥላ እጠላበት በመሆኑ ከኛ ከአባላት አንደ ድርጅት ምን ይጠበቅብናል? በማለት ካብራሩ በኋላ እኛ አንደ መንግስት በዚህ ጉዳይ ውስጥ የገባነው ፈልገን ሳይሆን መጅሊሱ ስለጋበዘን ነው፡፡ በመሆኑም ለምን እናን እንደጋበዙን እንዲያብራሩልን መድረኩን ለነሱ ክፍት ላድርግላቸው በማለት እድሉን ለሁለቱ ሰዎች ክፍት አደረጉ፡፡

  ሁኔታው ግልፅ የሆነላቸው በዕለቱ የተገኙ ተሳታፊዎች የተቃውሞ ድምፃቸውን በአንድ ላይ ለማሠማት ደቂቃ አልፈጀባቸውም፡፡ እርሶን እናውቆታለን (አቶ ፀጋዬን ማለታቸው ነው፡፡)፤ይህ የድርጅት ስብሰባ እንጂ የመጅሊስ ስብሰባ አይደለም፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ መጅሊስ እኛን ማወያየት ከፈለገ በመስጂድ ይጥራን፡፡ ይህ የድርጅት ስብሰባ ነው፡፡ከርሶ ጋር የተቀመጡት ሰዎች ህጋዊ የሆነ የህዝብ ውክልና የሌላቸው፣ ህዝብ የማያውቃቸውና ሙስሊሙ ህዝብ ይወገዱልኝ በማለት ጥያቄ ያነሰባቸው አካላት ናቸው፡፡ ምንም እንኳን እርሶን ብናከብርም እነኚህ ሰዎች ባሉበት መድረክ ይቅርና እዚህ አዳራሽ ውስጥ በተቀመጡበት ሁኔታ ፈፅሞ ስብሰባውን ማካሄድ አንችልም ይውረዱልን በማለት የበረታ ተቃውሞ አሰሙ፡፡በዚህም ምክንያት ግለሰቦቹ ከመድረክ ተሸማቅቀው ወረዱ፡፡ አላህ ሲያዋርድ እንዲህ ነው፡፡ ከመድረክ ከወረዱ በኋላ አንደኛው በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዘጋጅ የታዳሚው ተቃውሞ አሁንም ቀጠሎ ተክቢራ ማሰማት ጀመሩ፡፡ በአጠቃላይ ከአዳራሹ ይውጡልን በማለት በተክቢራ አቀለጡት፡፡ በዚህ ጊዜ ሰዎቹ የውርደት ማቅ ተከናንበው ጨርቄን ማቄን ሳይሉ በመጀመሪያው ረድፍ ተቀምጠው የነበሩ ጀሌዎቻቸውን አስከትለው ከአዳራሹ ውልቅ አሉ፡፡ አላሁ አክበር!
  ይሁንና የስብሰባው ታዳሚ ድርጅታቸውን በማክበር ስብሰባው እንዲቀጥል በፈለጉት መሠረት ከዋናው ሰብሳቢ ጎን ሌላ የኢህአዴግ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሐሰን ጧሂር መድረኩ ላይ ተሰይመው ሲያበቁ ስብሰባው ቀጥሎ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ተካሂዷል፡፡ በአብዛኛው የስብሰባ ታዳሚ እንደተነሳው ህዝቡ እያነሳ ያለው ጥያቄ አግባብነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የመጅሊስ አመራሮች ፍፁም እውቅና የሌላቸውና ህዝቡን የማይወክሉ መሆናቸው ታውቆ ከወረዳ እስከ ፌዴራል ድረስ አስቸኳይ ፍትሀዊ ምርጫ መካሄድ እንደሚኖርበት አሳስቧል፡፡ በማጠቃለያውም የመድረኩ መሪ የሚከተሉትን ነጥቦች ወርውረዋል፡-
  • መንግስት ችግሩን በውል እንደተረዳው እና አስቸኳይ መልስ መስጠት እንዳለበት
  • መጅሊስ የትምህርት ደረጃ ባላቸው ምሁራን ሊመራ እንደሚገባው
  • ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ መቀጠል እንደምንችል
  • ለየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት መሣሪያ ከመሆን እንድንቆጠብ
  • ጥያቄችንን መባሰማት ሂደት ትዕይንቱ በመስጂዶች አካባቢ ብቻ ቢሆን ተመራጭ እንሚሆንና ሌሎችንንም የማጠቃለያ ሃሳብ በመሰንዘር የውሎ ውይይቱ እኩለ ቀን ላይ በሠላም ተጠናቋል፡፡
  ይኸው ስብሰባ ነገ እሁድ በአዲስ አበባ መስተዳድር አዳራሽ በከንቲባው መሪነት ከ 1000 በላይ ተሳታፊዎች በሚገኙበት ቀጥሎ ይውላል፡፡ ሁላችንም እንደተለመደው አወንታዊ ሚናችንን በስብሰባው ላይ ተገኝተን እንወጣ፡፡መልዕክታችን ነው፡፡

  ዛሬ ከስብሰባ አዳራሽ መድረክ ተዋርደው እንደወረዱ ሁሉ ነገም ኢንሻአላህ ከሙስሊሙ መንፈሳዊ ተቋም ተዋርደው ይወገዳሉ፡፡by abu dawd
  Read more
 • Today Awoliya

  7ኛው ሳምንት ታላቁ የተቃውሞ ትዕይንት ተካሄደ!
  by Zain Usman 
  ለ7ኛ ጊዜ ቀጥሎ የዋለው የህዝበ ሙስሊሙ ትዕይንተ-ተቃውሞ በአወሊያ ተካሂዶ ዋለ፡፡ ከመቼውም ጊዜ እጅግ የላቀ የህዝብ ቁጥር ያስተናገደው ይህ ትዕይንት በሠላማዊ መንገድ ተጠናቋል፡፡ ከክልል ከተሞች ሳይቀር የመጡት ሙስሊሞች ትዕይንቱን ለመታደም ወደ አወሊያ መትመም የጀመሩት ገና በማለዳ ሲሆን ከቀኑ አምስት ተኩል አካባቢ ግቢው እጅግ ተጨናንቆ ጣት ማሣረፊያ ቦታ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡የትዕይንቱ ተሳታፊ በመመስል በታዳሚው ውስጥ ሰርገው በመግባት ትዕይንቱን የማደፍረስ ተልዕኮ ይዘው የመጡ ግለሰቦች ሊኖሩ እንደሚችሉና ህዝቡም ጥንቃቄ እንዲያደርግ የሚያውጅ መልዕክት ከመድረክ በኩል ከተላለፈ በኋላ መድረኩን ታዋቂው ዳዒ ኡስታዝ ባሕሩ ዑመር ተረክቦ ጠቃሚ እና ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ቀጥተኛ ዝምድና ያላቸውን ቁም ነገሮች ለህዝቡ እያካፈለ የኹጥባው ሠዓት ደረሰ፡፡ የሸኽ ዑመር /የመስጂዱ ኢማም/ ኹጥባን ተከትሎ የዕለቱ ዝግጅት በተከታታይ ተክቢራዎች በመታጀብ መጀመሩ ይፋ ከተደረገ በኋላ የዕለቱ ፕሮግራሞች ተዋውቀው መድረኩ ተከፈተ፡፡  የህፃን ሪሃና ‹‹መኖሬን ጠላሁት›› ግጥም እድምተኛውን እንባ አራጭቷል፡፡የራያ አባ ሜጫ የመንዙማ እንጉርጉሮ የሚፈለገውን መልዕክት ከማስተላለፍ ጋር በተያያዘ የህዝቡን ቀልብ መግዛት ችሏል፡፡ በዕለተ ረቡዕ ምሽት በራዲዮ ፋና 98.1 የተላለፈው ፕሮግራም አብዛኛው ሙስሊም እንደተከታተለው ግምት ተወስዶ የተነዛውን የማደናገሪያ እና ውዥንብር የመፍጠሪያ ፕሮፓጋንዳ ለህዝብ ግልፅ ማድረግ ያስችል ዘንድ በወጣቱ የታሪክ ፀሀፊ አሕመዲን ጀበል በኩል ኪታባቸውን ይዞ እንደ መረጃ በመጠቀም እነኚህ አላህን የማይፈሩ ሰዎች የቀጣጠፉትን ትልቅ ውሸት አጋልጧል፡፡ ንግግሩን ‹‹ … ስለሆነም ጥያቄያችን በሚዲያ ‹ሹብሀ› በሚፈጥር መልኩ ቀረብም አልቀረበም የመጅሊስ መሪዎች ይወርዳሉ! ›› በማለት አጠቃሏል፡፡ ታዳሚውም በቀረበው የአህመዲን ዝግጅት በመርካት በተደጋጋሚ ተክቢራ አሰምቷል፡፡ ይህን ተከትሎ ሁለት አዋቂ ሴቶች አህባሽን በተመለከት ያዘጋጁትን ግጥም ለታዳሚው እንካችሁ ብለዋል፡፡ በጉጉት ይጠበቅ የነበረውና የየካቲት 5 ቀጠሮ ምላሽ የመቅረቢያው ሠዓት በመድረሱ የነበሩት 17ቱም ተመራጭ ኮሚቴዎች መድረክ ላይ ተጣዱ፡፡ ኮሚቴዎቹን በመወከል ኡስታዝ ካሚል ሸምሱና ኡስታዝ አቡበክር አሕመድ ተራ በተራ ሪፖርታቸውን አቀረቡ፡፡ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የሪፖርቱን ዝርዝር ሀተታ ለኡስታዝ አቡበክር በመተው የውይይቱን አጠቃላይ አንደምታ እና  መልካም ገፅታዎች አብራርቷል፡፡ ኡስታዝ አቡበክር ያቀረበው የሪፖርት ይዘት ከሞላ ጎደል የሚከተሉትን ነጥቦች የያዘ ነበር፡፡
  የህዝቡ ጥያቄ ይበልጥ መሠማት እንዲችል፣ ጉዳዩ ከዳር እስከ ዳር እንዲደርስና የሚመለከተው አካል በሙሉ እንዲያውቅ የተከበሩ ጠ/ሚንስትሩን ጨምሮ ለስምንት የመንግስት የሚንስቴር መስሪያ ቤቶች 7 ገፅ ያለው ጥያቄዎችን ያዘሉ ደብዳቤዎችን ማስገባታቸው፣ በድንገተኛ ችግር ምክንያት ከሁለት ሰዎች በስተቀር 15ቱ የኮሚቴ አካላት በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተገኝተው ከሚንስትሩ ጋር ውይይት እንዳደረጉ በዚህም፡- ሚንስትሩ እንደተናገሩት ፡-
  ‹‹ በቀጠርናችሁና ቃል በገባነው መሠረት ጉዳያችሁ መፍትሄ ያገኛል፣ምላሽ እንሰጣለን፣ምላሽ የማንሰጠውም ነገር ካለ በግልፅ እናሳውቃለን ››ማለታቸው፣ ‹‹ጥያቄያችሁን አሁንም ባለው አግባብ  መቀጠል ትችላላችሁ›› ማለታቸው፣ ‹‹ጥያቄዎቻችሁ በሙሉ ግልፅ ናቸው ጥያቄዎቻችሁን በሙሉ ተረድተናል፣ገብቶናል›› ማለታቸው የመጨረሻውን ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 26 ቀጠሮ መሰጠቱ፣ ለየካቲት 26 የመጨረሻና ሁሉንም የሚያስደስት ምላሽ እንሰጣለን ማለታቸውን፣ ያኔ ምላሽ ካልሰጠን ምላሽ አልተሰጠንም ስትሉ የምትፈልጉትን ማድረግ ትችላላችሁ በማለት ቃል መግባታቸውን አብራርቷል፡፡ (ኡስታዝ አቡበክር ይህንን ሲናገር ህዝቡ የማያባራ ተክቢራ አሰምቷል) በመጨረሻም እስከ የካቲት 26 ድረስ ሁላችንም በትዕግስት በመጠበቅ ጠ/ሚንስትሩን ጨምሮ ደብዳቤ ያስገባንላቸው የመንግስት አካላት በጥልቅ ተወያይተውበት አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጡን ተስፋ እናደርጋለን፣ እኛም በትዕግስት እንጠብቃለን፡፡ኢንሻ አላህ! በማለት ንግግሩን አጠናቋል፡፡
  የህዝቡ የተክቢራ ጩኸት ማባሪያ አልነበረውም፡፡ ታዳሚው በሁኔታው እጅግ የተደሰተ ይመስላል፡፡
  ወደ ፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የአጭር ደቂቃ እድል ተሰጥቶት የነበረው ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ከሚንስትሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ ያስታወሳቸውን ሦስት ጠቃሚ ነገሮች እነሱም፡-
  መጅሊስ ሰፊውን ህዝብ እና ወኪሎቻቸውን  ፅንፈኛ፣ አሸባሪ… እያለ በየመድረኩ የሚናገረውን ንግግር እና የሚለጥፋቸውን ማስታወቂያዎች እንደሚቃወሙና ከዚህ በኋላ ባስቸኳይ እንዲያቆም እንደሚነግሯቸው ሚንስትሩ መናገራቸውን፣ እናንተን አሸባሪና አክራሪ ብሎ መወንጀል ከእናንተ ጋር ውይይት የሚያደርገውን መንግስትንም መወንጀል ስለሆነ እንደሚቃወሙ ሚንስትሩ መናገራቸውንና እስከ የካቲት 26 የመጨረሻ መልስ እስከሚሰጥ ድረስ እየተገናኘን መነጋገር እንድንችል ስልካችንን ተቀያይረናል ሲል ብስራት ያላቸውን ቃላት በቀልድ በማዋዛት እና ህዝቡን የቢላል(ረ.ዐ) መፈክር በመባል የምትታወቀውን ‹‹አሐዱን አሐድ!›› በማስባል መልዕክቱን ካስተላለፈ በኋላ መድረኩን ለቋል፡፡ የኡስታዝ ያሲን ኑሩ ንግግር የፕሮግራሙ መቋጫ ሆኖ በመድረኩ ቆይታ በተደጋጋሚ ሲነገር የቆየው ‹‹ሳምንት ጁምዓ በአወሊያ እንስገድ›› መልዕክት ተላልፎ የዕለቱ መድረክ በቁርኣን ንባብ ከተዘጋ በኋላ ቁጥር ስፍር የሌለው ኸልቅ በሰላም ወደ ቤቱ ተመልሷል፡፡
  Read more
 • የመሻኢኾቻችን … በሚዲያ ክፍል -አንድ

  የመሻኢኾቻችን … በሚዲያ
  ክፍል -አንድ
  እጅግ አዛኝና ሩህሩህ በሀነው በአላህ ስም 
  አላህ ቀጥተኛውን መንግድ እንዲመራኝና የዓለምን ሀዝቦች በሙሉ ወደ ቀጥተኛው መንግድ እንዲመራቸው ምኞቴም ዱዓዮም ነው፡፡
  ከዚህ በታች የታላቁ አንዋር መስጅድ ዒማም ሸይኽ ጡሃ ሙሐመድ ባለፈው ረቡዕ ማታ በፋና ብሮድካስቲንግ ፌብሩዋሪ 15 ቀን ማታ አህባሽ ማነው ታሪኩስ ተብለው የተጠየቁትን ጥያቄ ሲመልሱ የመለሱት መልስ ነው፡፡በዚህ መልስ የታዘብኩዋቸውን ግጭቶችና አደገኛ መልዕክቶች እንደሚከተለው በአላህ ፈቃደ በጥያቄ መልክ አቀርባለሁ፡፡ሆኖም ግን በምንም ሁኔታ መሻኢሆችቻንና ኡለማኦችን ልወርፋቸውም ሆነ ላጣጥላቸው እንዲሁም ክብቸውን ትቂትም መንካት አልፈልግም፡፡አላህን የምለምነው ኡለማኦቻችንን ቀስፎ የያዛቸው የፍርሃትና የዱኒያ አባዜ ተገፎላቸው ላኢላሃኢለላህ ባሉበት አንደበታቸው ስለ ጊዜያዊ ትሩፋታቸው እንዳይዘምሩ ነው፡፡ ለማንኛውም የሸህ ጡሀ ቃል እንሆ…
  ሸህ ጡሃ
  "ኢትዮጵያ በውጭ ሀገር ከድሮ ጀምሮ ሀበሻ በሚል ትታወቃለች፡፡የህ ስም አስካሁንም አለ፡፡አንድ ሃበሻ የሚባለውን ወደ ብዙ ስም ለመለወጥ አህባሽ ይባላል፡፡በነቢ ዘመን አለይሂ ሶለዋቱሏሂ ወሠላም ታዋቂ እና ለማሞገስ ሲፈለግ በሀበሻ ብቻ ነው የሚወሠነው፡፡አህባሽ የሚለው ግን አሉታዊ መልዕክት ያለው ስያሜ ነው፡፡ በዛ በዘመናቸው በሲራ እንደምናገኘው፡፡በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ሙሐድሡ ሸይኽ አብዱላሂ አልሃረሪ ከኢትዮጵያ ወደ ስዑዲ ሄደው፡፡ስዑድም ከኡለማኦች ጋር በዓቂዳ ምክንያት ሳይስማሙ ሲቀሩ ወደ ሶሪያና ሉብናን ሄደዋል፡፡በወቅቱ የነበሩት ታላላቅ ዑለማዎች አቀባበል አድርገውላቸው በተለይ ብዙም ተለይቷቸው የማያውቅ ዶ/ር ኒዘር አልሀለቢ አናውቃቸዋለን ታሪኻቸውን፡፡እዛ ሲኖሩ ነበረ ከዛም በዓቂዳ ላይ ያተኮረ ዒልም ማስፋፋት ይጀምራሉ፡፡እዛ በቡድን አደራጁ ብዙ ዑለማኦችን በተለይ ጃሚኢየቱል አዝሃር በዓለም ላይ ልዩ እውቅና ያለው የካይሮ ዩኒቨርሲቲ የወጡ ዑለማዎች ተጠጓቸው፤በቂ እውቀት እያላቸው፡፡ ከዚያም እዛ ብዙ መስመሮችን ዘረጉ፤ ህዝቡም ዑለማው፣የሶሪያ ዑለማ ጭምር አቀባበል አድርገውላቸው ቦታ ይዘው ተመከኑ፡፡ከዛ እንግዲህ ስዑዲ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ እንካስላንቲያ በፅሁፍም ከሥዑድ ዑለማዎች ጋር ብዙ (ፍጅት) ተፈጥሯል፡፡መጀመሪያ ዑለማኦቹ የስዑድ ኡለማዖች በጉልበት አወጧቸው ከሀገራቸው፡፡በኋላም መፅሀፍ ፃፉባቸው፡፡እሳቸውም እነኚህን የፃፉባቸውን ሰዎች ሁሉ በዝርዝር አጠፌታውን ብዙ ፅሁፎች መልሰዋል፡፡እዛ ላይ እንግዲህ ወሀቢያም የጠነከረበት ዘመን ነበር ያጊዜ የዛሬ 40 ዓመት በፊት ነው፡፡(በአካባቢው) የጠነከረ ነበረ፡፡ ብዙ ፅሁፎች የከረሩ ፅሁፎችን ተለዋውጠዋል ከዚያም ሶሪያ ውስጥ፣ሉብናን ውስጥም ሲደራጁ እንግዲህ እሳቸው(አል-ሀረሪ) ብዙ ደረሶችን አፈሩ፡፡ደረሶቹ ደግሞ በዚህ በሱፍያና በውሃብያ ጋር ግንኙነት የሌለው የጠራ አቂዳ ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን ማስፋፋት ጀመሩ፡፡እዛ ላይ እንግዲህ በጥላቻ ሱዕዳውያን አህባሽ የምትለውን ሥም ለጥፈውባቸዋል፡፡ነገሩ ስሙ ሀበሻ መሆናቸውን የሚገልፅ ነው እንጅ ሌላ ነገር አይደለም፡፡ወላኪን እሳቸውንና እሳቸውን ያጀቡ ሁሉ፣እንደገና የእርሳቸው ደረሳ የሆኑትን ሁሉ አህባሽ በማለት በተለያዩ መፅሀፎቻቸው ትችት አድርገውታል፡፡ በኔትዎርክ በተለያዩ ነገሮች "እኛም ብዙ ጊዜ እናነባለን" ዘርግተዋል፡፡እንግዲህ አህባሽ ማለት ስያሜው ከወዳጅ የመጣ ሳይሆን ከ…ተፃራሪ ክፍል የተለጠፈባቸው ስያሜ ነው፡፡"
  በንግግራቸው ውስጥ የተስተዋሉ ግጭቶች
  1.አህባሽ የሚለው ቃል በነቢዩ (ሡዐወ) ዘመን አሉታዊ መልዕክት ያለው ስያሜ መሆኑን መጀመሪያ ከነገሩን በኋላ ኃላ ላይ የስዑዲ ዑለማኦች በጥላቻ ስሜት ይህን ስም እንደለጠፉባቸው ጠቁመው ስሙ ሀበሻ መሆናቸውን የሚገልፅ ነው እንጅ ሌላ ነገር አይደለም ይሉናል፡፡ምን ማለት ነው ሁለት ተቃራኒ ነገሮች በአንድ ቅፅበት ውስጥ ትክክል ሊሆኑ አይችሉም፡፡አንድ በረሱሉ ዘመን የነበሩ ሰዎች አህባሽ የሚለውን ቃል ለአሉታዊ መልዕክት መጠቀማቸው ስህተት ነበር እያሉን ነው ወይም የወቅቱን የአህባሽን አስተሳሰብ ተቀብለዋል ማለት ነው፡፡በመጨረሻም ስያሜው ከተፃራሪ እንጅ ከወዳጅ የመጣ አለመሆኑን በመግለፅ ሃሳባቸውን ሲቋጩ ከባላንጣ የተሰየመ ስያሜ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ወይም በአሉታዊ የሚታይ ነው የሚል ስሜት ያስይዛል፡፡
  ሸህ ጡሃ የሚከተሉት መዝሃብ ምንድን ነው?
  ሸይኽ ጡሃ የአህባሾችን አስተምህሮ ከሱፍይም ከውሃብይም ጋር ግንኙነት የሌለው የጠራ አቂዳ ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን እንደሚያስተምሩ ነግረውናል፡፡ሸይሁ በዚህ አባባላቸው የሚከተሉትን ጭብጦች አስይዘውናል፡፡
  የአህባሽና የሱፍይ አስተምህሮ የማይገናኝ ትምህርት መሆኑን አስረግጠው ነግረውናል፡፡ታዲያ አህባሽ ሱፍይን የማይቀበል መሆኑን ከተረዱ እርሳቸው የደገፉት ምን ስለሆኑ ነው? ውሃ ብያ እንዳንል ውሃብያ ብለው የፈረጁትን ክፍል ክፍኛ ሲያብጠለጥሉት ተደምጠዋል፡፡
  የአህባሽን አስተምህሮ "የጠራ" ሲሉ ገልፀውታል፡፡ይህን ቃል ከሰነዘሩበት አግባብ (contextual meaning) አንፃር ሲገመገም አያይዘው የተጠሩት የሡፍይ እና የውሃብያ አመለካከቶቸ የጠሩ አይደሉም የሚል ትርጉም ይሠጠናል፡፡ታዲያ ሸይህ ጡሃ የትኛውን ክፍል ወግነው ይሆን ይህን የሚነግሩን?
  ጥያቄ የሚያጭሩ ሃሳቦች
  1.ከስዑዲ ኡለማኦች ጋር ያጋጫቸው ሃሳብ ምንድን ነበር?
  2. ለሳዑዲ ዑለማዎች በዝርዝር ለሁሉም የተሰጠው አፀፋዊ መልስ ሸይህ ጡሀ ካላቸው ዲናዊ እውቀት አንፃር እንዴት ያዩታል፡፡ምን አልባት ሸይኽ አብዱሏሒ በየመፅሀፎቻቸው እከሌ ካፊር እከሌ ካፊር እያሉ የፃፉትን እያሉን ከሆነ ይህ በኢስላም ይፈቀዳል ማለትዎ ነው? የገለፁበትም ስሜት ግለሰቡ ባደረጉት አፀፋዊ መልስ መርካትዎትን በሚያሳብቅ መልኩ ነበርና እርሰዎም ማክፈሩን ይጋሩታል ማለት ነው?
  3.የዑለማዕ ክብርና ደረጃ ምን ያክል ነው? እሽኮለሌ የሚገጥሙ? በጉልበት የሚጠቀሙ?
  የሳኡዲ ኡለማኦች ምን ያክል ለህዝቦቻቸው እንደሚጨነቁ እየነገሩን ይመስለኛል ምክንያቱም ለህዝባቸው የማይመጥን ካላቸው ነባራዊ ሁኔታና ለዲኑ ቅርበት አንፃር በወቅቱ መፍትሔ ሲሰጡ እናንተስ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምንያክል ታስቡለታላችሁ?ምናልባት እናስብልሃለን እናውቅልሃለን የሚጠቅምህ ይህ ነው እያሉት ከሆነ የእርሰዎ ጎራስ ከየትኛው ነው?
  ወገንተኝነት 
  1. አበዱላሂ አል-ሀረሪ ስዑዲ ከሄዱ በኋላ ከሳዑዲ አረቢያ ዑለማኦች ጋር በአቂዳ አለመስማማታቸውንና ሳዑዲያውያኑ ሸይሁን በጉልበት ከማስወጣታቸውም በተጨማሪ ሸይሁን በህትመት ውጤቶችና በተለያዩ ሚዲያዎች እንካስላንቲያ እንደፃፉባቸው ሲገልፁ የተጠቀሙት አገላለፅ በሸይህ አብዱሏሂ አልሀረሪ ሳዑዲያውያኑ ያደረሱባቸውን በደልና መከራ ለህዝቡ ማሳወቅን ነው፡፡ታዲያ ይህ አቀራረብ አድሎአዊ አይደለም ብለው ያስባሉ? በእርግጠኝነት አድሎአዊ ነው ምክንያቱም መልዕክቱን ታዳሚው ማህበረሰብ የግጭት መንስኤ የሆነውን አቂደ ማሳወቅ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ሸይሁስ በአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ህዝቦች ላይ ለመጫን ያሰቡት አስተሳሰብ ወይም የግጭቱ መንስኤ የሆነው መገለፅ አልነበረበትም?
  2. ሸይኹን ለማድነቅ ለማሞገስና ለማግዘፍ የሚከተሉትን ዘይቤዎች ተጠቅመዋል ይህ ወዴት ያመራል፡፡
  ሙሐዲሱ
  ታላላቅ ዑለማዎች፣ህዝቦችና የሶሪያ ዑለማዎች ሳይቀሩ የተቀበሏቸው መሆኑን
  የአዝሀር ዩኒቨርሲቲ ምሁሮች እንኳን የተቀበሏቸውና የተጠጓቸው መሆኑን
  Read more
 • አሕባሽ ለሀገር ልማት ????

  አሕባሽ ለሀገር ልማት
  - በርግጥ ይለምናሉ፡፡ ግን በብዛት በህይወት ያለ ሰው አያስቸግሩም! ከሞተ ሰው ነው የሚለምኑት!(ቡግየቱጧሊብ፡ 8፤ ሶሪሑልበያን፡ 57-58፤ አደሊሉል ቀዊም፡ 173) ወይም ከድንጋይ ነው በረካ የሚፈልጉት!!(ሶሪሑልበያን፡ 58፤ ኢዝሃሩል ዐቂደቲሱኒያህ፡ 244)
  - በስራ ቦታዎች ላይሆንላቸው ተፍ ተፍ በማለት የስራ ቦታዎችን አያጨናንቁም፡፡ ይልቅ ጫት ነው የሚቅሙት፡፡ እስኪ ዐስር ሶላት ላይ የማይገኙ የሱፍያ ኢማሞችን ቁጠሩ፡፡ እንግዲህ በየቀኑ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያስገቡትን አስቡት?
  - አሕባሽ ለውበት፡- ዐብደላህ አልሀረሪ፡ ሒጃብ የሰውነትን ቀለምና ፀጉርን ከሸፈነ ይበቃል ብሏል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 104(አዲሱ እትም፡137))፤ ተማሪው ኒዛር ሐለቢ፡ ሴቶች ወጣቶቻችን በጂንስ ይዋባሉ፤ ምክኒያቱም እኛ ሰውነትን መሸፈንም ፋሺን መከተልም በተመሳሳይ ጌዜ እናስገኛለን ብሏል(አልሙስሊሙን ጋዜጣ ቁጥር፡407፣ 1992)፤ ሴት ሽቶ ተቀብታ መውጣቷን ፈቅዷል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 351(አዲሱ እትም፡446))
  - አሕባሽ ሙድ የገባው፡- ከአጅነቢይ ጋር በእጆቻቸው መካከል የሚለይ ነገር አድርጎ መጨባበጥን ፈቅዷል(ሶሪሑል በያን፡ 144)፤ የሴቶችና የወንዶችን መቀላቀል ፈቅዷል(ሶሪሑል በያን፡ 178-179)፤ በስሜት ካልሆነ ሴትን ለረጅም ጊዜም ቢሆን መመልከት ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡224፣287፣288(አዲሱ እትም፡280፣266፣267))፤ ቤተሰብ ከሆነች ደግሞ ከእንብርት እስከ ጉልበት ካለው ውጭ መመልከት ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡290(አዲሱ እትም ላይ ግን አውጥቶታል)፤ ወንድ ወይም ሴት መሆኑ ከማይለይ ፍናፍንት ጋር በረመዷን ግንኙነት ማድረግ ፆም አያበላሽም(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 192(አዲሱ እትም፡243))፤ ብልት ከተሸፈነ በፓንት ሶላት መስገድ ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 139)
  - አሕባሽ የቴክኖሎጂው ትውልድ፡- የአለም ቅርፅ ላይ አዲስ ግኝት አግኝተው ቂብላ ቀይረዋል
  - አሕባሽ ዘመኑን የቀደመ የህክምና ግኝት ባለቤት፡ አንድ በርሜል ውሃ ውስጥ አንዲት ፀጉር ብቻ በመክተትና በመርጨት ለበርካቶች ፈውስ ይሰጣሉ፡፡ በዚህም ለህክምና የሚወጡ አላስፈላጊ ወጪዎችን በማስወገድ ለሀገር ኢኮኖሚ የበኩላቸውን ያበረክታል
  - አህባሽ ለአእምሮ ንቃት፡- አላህ አለ ግን ከአለም ውስጥም ከአለም ውጭም የትም የለም! ገባችሁ? ቆይ እናንተ የትኛው ነገራችን ነው የሚገባችሁ? እሺ ይሄስ ይገባችኋል? በነጃሳ ያውም በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 99-100(አዲሱ እትም፡131-132))፤ የትኋንና የቅማል ደም ግን ነጃሳ ነው፤ የነካውም ሰው አወቀም አላወቀም ሶላቱ ውድቅ ነው(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 87(ሁለተኛ እትም፡ 119))፣ ኢስቲንጃን ከውዱእ በኋላ ማድረግ ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡134)፡፡ አሁንም አልገባችሁም? አቤት አእምሮ!
  - አሕባሽ ለድህነት ቅነሳ፡ ከወረቀት የብር ኖት ዘካ የለም(ቡግየቱ ጧሊብ፡160፣ 169(አዲሱ እትም፡207))
  - ተጠየቁ! እናንተስ ሀሜተኞች ምን አበረከታችሁ?!

  አሕባሽ ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት
  - እርግጥ ነው በእውር ድንብር ያከፍራሉ፤ ለማክፈርም ያዳላሉ፡፡ በተመሳሳይ ነጥብ አንዱን አውግዘው ሌላውን ያልፋሉ፡፡ ዐብደላህ አልሀረሪ፡- ኢማሙ ዘህቢን ቆሻሻ ይላል፤ ኢብኑ ተይሚያን፣ ዳሪሚይን፣ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱልወሃብን፣ አልባኒን… ያከፍራል፡፡ ቢሆንስ የነዚህ ሰዎች መከፈር አለመከፈር ከሀገር ሰላም ጋር አዎንታዊ ካልሆነ በቀር ምንድነው አሉታዊ ውጤቱ?! እንዴ እናስተውል እንጂ!
  - መስከረም(?) ላይ የታተመው የኢትዮጵያ እስልምና ገዳይ/ መጁሰል አዕላ ልሳን የሆነው “ነጃሺ” መፅሄት (“ጃ”ን ጠበቅ ያርጓት) ከአራቱ መዝሀቦች ተከታዮች ውጭ ሙስሊም እንደሌለ አስፍሯል፡፡ ከነዚህም ውስጥ “አላህ ከዐርሹ በላይ ነው” የሚሉ፣ ለኢብኑ ተይሚያ … የሚከላከሉ ይቀነሳሉ፡፡ ቢሆንም ይሄ እራሱ ላስተዋለው ለሀገር ሰላምና መረጋጋት የራሱ ፋይዳ አለው፡፡ አገኛችሁት? ፐ!
  - -የካፊርን ገንዘብ መስረቅ(ካሴት ቁጥር፡2)፣ በቁማር መብላት ይቻላል(ሶሪሑል በያን፡133-134)፡፡ ቢሆንም ችግር በማይፈጥር መልኩ ስለሚሰራ ብዙም የሀገርን ሰላም አያናጋም፡፡
  - እናንተ የአሕባሽ ተቃዋሚዎች ግን አህባሽን በመቃወም የሀገሪቱን ሰላምና መረጋጋት ነስታችኋል!!!!
  Read more
 • በ አዲስ አበባ ኳስ ሜዳ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው ሰላሃዲን(ሐጂ የኑስ) መስጂድ የተዘጋጀው ያልተሳካው የመጅሊስ ሴራ

  By Zain Usman

  ከህዝብ እውቅና የተነፈገው እና ህዝብ ፊት የነሳው መጅሊስ እተፋፋመ የመጣውን የህዝበ-ሙስሊሙ ተቃውሞ ለማኮላሸት ካዘጋጃቸው ሴራዎች በህዝበ-ሙስሊሙ ጥረት ከሸፈ፡፡

   

  ህዝበ ሙስሊሙ ያነገባቸውን መሠረታዊ ጥያቄዎች ማሰማት ከጀመረ ስድስተኛ ሳምንቱን በያዘበት በዚህ ሳምንት የህዝቡ እንቅስቃሴ እንቅልፍ የነሳቸው የመጅሊስ አመራሮች አዲስ እና ጊዜ ማራዘሚያ ይሆናል በማለት ያዘጋጁትን ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ አደረጉ፡፡ መጅሊስ የመስጂድ ኢማሞችን ከሰበሰበ በኋላ የጁምዓ ኹጥባቸውን በአህባሽ አስተምህሮት ዙሪያ እንዲያደረጉ፣ ቅዳሜና እሁድ ደግሞ የአካባቢውን ህዝብ በመጥራት እንዲያስተምሩ ቀጭን ተእዛዝ አስተላለፈ፡፡ ፅንፈኞች እና አክራሪዎች ህዝቡን ለማወናበድ የሚያደርጉት ሙከራ እንጂ አህባሽ እና አስተምህሮቱ ባእድ እንዳልሆነ  በመሆኑም ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ምክር አዘል ተግሰፅ ለማስተላለፍም ተስቦ ነው፡፡ ይህ ተልዕኮ ከተሰጣቸውና ተግባራዊ ከሚያደርጉት ውስጥ በተለምዶ ኳስ ሜዳ በሚባለው አካባቢ  የሚገኘው ሰላሃዲን(ሐጂ የኑስ) መስጂድ አንዱ ነበር፡፡ የመስጂዱ ኢማም ባይሆኑም ዘወትር የጁምዓ ኹጥባ በማድረግ የሚታወቁት ሽኽ ---- የትላንትናውን(10/02/2012) የጁምዓ ኹጥባ ተከትሎ ነገ ቅዳሜ(11/02/2012) በዚሁ መስጂድ ስለ አህባሽ ትምህርት እንደሚሰጥና ህዝቡም እንዲታደም ማስታወቂያ ተናገሩ፡፡

  የቀጠሮው ሰዓት ከጧቱ 2፡30 ቢሆንም እስከ 4፡00 ድረስ ቀጠሮውን አክብረው በበቦታው የተገኙ ሰዎች ቁጥር ከ20 እምብዛም የዘለቀ አልነበረም፡፡የነበረው አማራጭ ባለው የታዳሚ ቁጥር መጀመር ነበርና ኡኹዋን አስመልክቶ ከኻጢቡ አንደበት የፈለቁት ቃላት ከመድረክ ወደ ታዳሚው መወርወር ጀመሩ፡፡ ወሬያቸው እየሞቀ ሲመጣ የታዳሚውን ትግስት የተፈታተነው ነገር ብልጭ አለ፡፡ ከታዳሚዎቹ አንዱ ከተቀመጠበት ተነስቶ ሲያበቃ ‹‹የተጠራነው ስለ አህባሽ ትምህርት ሊሰጥ ሆኖ ሳለ ለምን ወደ ጉዳዩ አንገባም?›› ሲል ጠየቀ፡፡ ሼኹም በወሰዱት ስልጠና መሠረት ስለ አህባሽ መናገሩን ቀጠሉ፡- ‹‹አህባሽ የሚለው ቃል ሀበሻ ከሚለው የተነሳ ሲሆን ስሙንም ጥላቻ ያለባቸው ሰዎች አመጡት እንጂ ሼኽ ዓብደላህ ሐረሪ የሚያስተምሩት ትምህርት ስህተት የለውም እና…›› እያሉ መናገራቸውን ሲቀጥሉ ታዳሚዎች መጠየቅ ሚፈልጓቸው ነገሮች እንዳሉ መናገር ጀመሩ፡፡ ሼኹ ግን ጥያቄዎችን በመቃወም ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡ በዚህ መሃል ከታዳሚዎች አንዱ በያዘው ሞባይል ቀረፃ ለማድረግ ተነሳ፡፡ ሼኹ አስተውለውት ኖሮ ቁጣቸው ገንፍሎ በመውጣት ሁኔታው ፈሩን መልቀቅ ጀመረ፡፡ የመድረኩ ሁኔታ በዚህ መንፈስ መቀጠል ባለመቻሉ ፍትጊያው ከመጠንከሩ በፊት ሰዎች ተረባርበው ነገሩን ካበረዱት በኋላ ሼኹን ከለላ በመስጠት ከመስጂዱ አስወጧቸው፡፡ በአከባቢው ለሚገኙ የጥበቃ አካላት ካስረከቧቸው በኋላ በታክሲ ወደ ቤታቸው እንዲሸኙ ሆኗል፡፡ ሆኖም በዚህ ሁኔታ የተጠናቀቀው መድረክ በወደፊቱ የመስጂዱ ሁኔታ ላይ አደጋ ማንዣበቡ ያሳሰባቸው የመስጂዱ የጀመዓ አባላት እርስ በርስ ተሰባስበው ሲያበቁ ምን እናድርግ ሲሉ ውይይት ጀመሩ፡፡በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ አንድ ግለሰብ ድንገት ከውጭ መጥቶ ሹራውን ተቀላቀለ፡፡ይህ ሰው በዚህ መስጂድ ጀመዓ ብዙም የታወቀ አይደለም፡፡ነዋሪነቱ ቀበሌ 14 የሆነው ግለሰብ አልፎ አልፎ በዚህ መስጂድ እየመጣ ይሰግዳል፡፡ የሹራ አባላቱ ሰውዬው ከመምጣቱ አስቀድሞ እንደነበረው ሹራቸውን መቀጠል አልቻሉም፡፡ ‹‹የምትናገሩትና የምታወሩት ነገር ትክክል አይደለም›› በማለት በተደጋጋሚ ሹራውን ማወክ ጀመረ፡፡ እንዲወጣ ቢፈልጉም ከመስጂደድ ኮሚቴዎች አንዱ ሰውዬ አውቀዋለሁ በማለቱ ጉዳዩ ይበልጥ ስላማይመለከተው ተነግሮት አርፎ እንዲቀመጥ አዘዙት፡፡ ተልዕኮ ያለው የሚመስለው ይኸው ግለሰብ መረበሹን ቀጠለ፡፡ ሁኔታው በዚህ ሁኔታ እንዳይቀጥል ለማድረግ ሲባል ሰውዬውን እንደሼኹ ለጥበቃ አካላት ሰጥተው ለመሸኘት ቢሞከርም ሁኔታው መልኩን ወደ አልተፈለገ አቅጣጨ ቀየረ፡፡ ግለሰቡ እሰጥ አገባ ውስጥ ገባ፡፡ ድብድብ ተጀመሮ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ግለሰቡ ሮጦ ለማምለጥ ሲሞክር ከኪሱ አንድ ወረቀት ወደቀ፡፡ ይህ ወረቀት ‹‹ተልዕኮ የተሰጠው ግለሰብ ስም ------------›› የሚል ርዕስ ያለው ሆኖ ተገኘ፡፡ በዚህም አሳፋሪው ተልዕኮ ሳይሳካ በሙስሊሞቹ የጠነከረ የአንድነት ክንድ ሳይሳካ ቀረ፡፡ በዚህ መስጂድ የነበረው የመጅሊስ ተልዕኮ በጠቅላላ ከሸፈ፡፡አልሐምዱሊላህ፡፡

  በሙስሊሞች የተባበረ የአንድነት ክንድ ኮርተናል፡፡

   

  አታላዮች አይደለንም አታላዮች ግን ፈፅሞ አያታልሉንም! 

  Read more
 • መጂሊሶች በየቦታዉ በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ላይ በጣም ተጠምደዎል by abu dawd

  መጂሊሶች በየቦታዉ በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ላይ በጣም ተጠምደዎል:: በወረቀቶቹም ላይ በአወልያ ጁምአ ጁምአ የሚሰበሰቡት ሰዎች በግብር እና በተለያዩ ምክንያቶች በመንግስት ላይ ቅሬታ ያላቸዉ ሰዎች ናቸዉ::ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም መንግስት ላይ ችግር መፍጠር የሚፈልጉ ሰዎች ናቸዉ እንጂ የሙስሊሞች ጥያቄ አስጨንቇቸዉ አይደለም ብሏል::ሌብነታቸዉ ሙሰኛነታቸዉ ለሆዳቸዉ አድርባይ መሆናቸዉን ህዝበ ሙስሊሙ ስለነቃባቸዉ በነሱ ቤት ማስቀየሳቸዉ ነዉ::"እኛ ብልጥ አይደለንም ብልጣ ብልጦችም ግን አያታሉንም" ብለዉ የለ ሰይድና ዑመር(ረ.ዐ) ::እኛን ሙስሊሞች ሳይሆን የራሳቸዉን ደቀመዝሙሮች ሄደዉ ይስበኩ::ትንሽ ቀናት ነዉ የቀራቸዉ ኢንሻአላህ ይወርዳሉ!!!by abu dawd Read more
 • መጂሊሶች በየቦታዉ በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ላይ በጣም ተጠምደዎል by abu dawd

  መጂሊሶች በየቦታዉ በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ላይ በጣም ተጠምደዎል:: በወረቀቶቹም ላይ በአወልያ ጁምአ ጁምአ የሚሰበሰቡት ሰዎች በግብር እና በተለያዩ ምክንያቶች በመንግስት ላይ ቅሬታ ያላቸዉ ሰዎች ናቸዉ::ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም መንግስት ላይ ችግር መፍጠር የሚፈልጉ ሰዎች ናቸዉ እንጂ የሙስሊሞች ጥያቄ አስጨንቇቸዉ አይደለም ብሏል::ሌብነታቸዉ ሙሰኛነታቸዉ ለሆዳቸዉ አድርባይ መሆናቸዉን ህዝበ ሙስሊሙ ስለነቃባቸዉ በነሱ ቤት ማስቀየሳቸዉ ነዉ::"እኛ ብልጥ አይደለንም ብልጣ ብልጦችም ግን አያታሉንም" ብለዉ የለ ሰይድና ዑመር(ረ.ዐ) ::እኛን ሙስሊሞች ሳይሆን የራሳቸዉን ደቀመዝሙሮች ሄደዉ ይስበኩ::ትንሽ ቀናት ነዉ የቀራቸዉ ኢንሻአላህ ይወርዳሉ!!!by abu dawd Read more
 • የኢትዪጲያ እስልምና ጉዳዬች ጠ/ምክር ቤት by abu dawd

  የኢትዪጲያ እስልምና ጉዳዬች ጠ/ምክር ቤት አመራር ተብዬች ለጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የመረጣቸዉን16 ተወካዬች የስልጣን ጥማት ያላቸዉ ሰዎች በመሆናቸዉ መንግስት እነዚህን ሰዎች ሊጠነቀቃቸዉ ይገባል በማለት ደብዳቤ አስገብተዎል!ያ ጀምአ ልብ ያለዉ ልብ ይበል!!ዎ ኢስላማ Read more

Latest Articles

Most Popular