GENERAL

  • መንግስት ቤተክርስቲያን በማቃጠል ክርስቲያኑና ሙስሊሙመሐል መቃቃር ለመፍጠር አስቧል ተባለ!!

    ድምፃችን ይሰማ
    ዛሬ ከታማኝ ምንጮች የደረሱን መረጃዎች መንግስት በኢቲቪ
    ያቀረበው ዶክመንተሪ ፊልም ባሰበው መልኩ ክርስቲያን
    ወንድሞቻችንን ሙስሊሙ ላይ ማነሳሳት ባለመቻሉ ይህንኑ
    ዐላማ ለማሳካት ሌላ ዘዴእንደቀየሰ ያሳያሉ፡፡ ሙስሊሙ
    ተቃውሞ የሚወጣበትን ዕለት ጠብቆ በአቅራቢያ የሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን በማቃጠል (ምናልባትም የሙስሊም ምልክት
    ባላቸው ሰዎች ሊሆን ይችላል) ክርስቲያኑና ሙስሊሙመሐል
    መቃቃር ለመፍጠር ታስቧል፡፡ ይህን እርኩስና ያለፈበት
    የከፋፍለህ ግዛ ዐላማ እንዳይሳካ ለማድረግ መጪው ጁሙዓ
    በአንዋርመስጂድ ታስቦ የነበረው የተክቢራ ተቃውሞ በተክቢራ
    መሆኑ ቀርቶ በዝምታ እንዲሆን ሰፊ ምክክር ተደርጎበት ተወስኗል፡፡ በመሰረቱ የደረሰብን ግፍና መከራ
    በተክቢራጩኸንም የማይወጣልን መሆኑን የምንረዳ ቢሆንም
    የመንግስትን እኩይ ዐላማ እንዳይሳካ ለማድረግና ቀኑ ፍጹም
    የተረጋጋሆኖ እንዲያልፍ ከማሰብ አንጻር
    በየክልልሉየታሰቡት የተክቢራ ተቃውሞዎች እንደተጠበቁ
    ሆነው በአንዋር መስጂድ ግን ጁሙዓ ተቃውሟችንን በአስደንጋጭ ዝምታ እንገልጻን፡፡ ሁላችንም ለተፈጻሚነቱ
    የተለመደውን ትብብር እንድናደርግና ላልሰሙት እንድናሰማ
    እንጠይቃለን፡፡ ህዝብ ሰላም አስጠባቂ መንግስት ደግሞ
    ሰላም አደፍራሽ የሆነበት አገር ግን ሰምታችሁ ታውቃላችሁ??
    Read more
  • TARIKAWI BEDEL BE ETHIOPIA MUSLIM LAY

    ﺑﺴﻢﷲﺍﻟﺮﺣﻤﻦﺍﻟﺮﺣﻴﻢ 
    ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የደረሰባቸውን ሐይማኖታዊ የመብት ጥሰት በመቃወም ስርዓቱን በጠበቀ መንገድ ጥያቄያቸውን በድምጻቸው ለመረጡት መንግስት ቢያሰሙትም ምላሹ 20 ዓመታትን በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ካሳለፈ አገዛዝ ይቅርና 20 ቀናት በዲሞክራሲ ስርዓት ከቆየ አገዛዝ የማይጠበቅ መሆኑ ልብን የሚያደማ ነው፡፡ 
    እንደ ዜጋ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ ተጥሶ ስናየው፣ መብታችንን እንደ የእግር ኳስ ከወዲህ ወዲያ እያላጉ እንቅርቅቦሽ ሲጫወቱበት ጉዳቱ ሲያመን ጊዜ ህግ እና ሥርዓት ባለበት አገር ህግና ሥርዓትን ጠብቀን በአንድ መድረክ ተሰብስበን ስናበቃ ጥያቄያችን እንዴት ሊሰማ እንደሚችል ተወያይተን ወኪሎቻችንን ህጉ በሚያዘው ቅደም ተከተል መርጠን፣ጥያቄዎቻችንን ለአረዳድም ሆነ ለምላሽ በማያዳግት መልኩ እጥር ምጥን አድርገን ለመንግስት አቀረብን፡፡ እንዲህ እንዲህ እያልን ተጉዘን ሰባት ወራትን አስቆጠርን፡፡ ይህ ሂደታችን ለራሳችን እስኪገርመን ድረስ አስተማሪነቱ ድንበር ተሻጋሪ ሆኖ አገኘነው፡፡ ይህ ሂደታችን ራሱ የኢሕአዴግ የስራ አስፈፃሚ ጉባዔንም ጭምር እንዳነጋገረ የምናውቀው እውነታ ነው፡፡ 
    ጥያቄዎቻችን ፍፁም ሐይማኖታዊ እና ሐይማኖታዊ ናቸው፡፡ በምን ቋንቋ ይሆን እነኚህ ሦስት ጥያቄዎቻችን ሐይማኖታዊ ብቻ ከመሆን ሊዘሉ የሚችሉት? ጥያቄዎቹ እኮ!
    1. የመጅሊስ አመራሮች አይወክሉንም፣ምርጫ ይደረግ፣
    2. የአሕባሽ የግዳጅ አስተምህሮት ይቁም እና
    3. አወሊያ ከህዝብ በተመረጠ ገለልተኛ የቦርድ አመራር ይተዳደር የሚሉ ናቸው፡፡
    እነኚህን ጥያቄዎች መመለስ የአንድ ቀን እና የአንድ ሌሊት የጊዜ ገደብ እንኳ አይፈጅም፡፡ጥያቄዎቹ እጅግ ግልፅ፣ ቀላል እና ለዘመን ዘመናት በራሱ አባት ተቋም ልቡ የቆሰለውን ሙስሊም ኅብረተሰብ ቁስሉን በማከም አገራችን የያዘችውን ልማት በተጠናከረ መልኩ ማስቀጠል የሚቻልበትን ጠንካራ ጡንጫ መፍጠር ያስችል ነበር፡፡ ሆኖም የምናየው ነገር የተገላቢጦሽ ሆኖ መንግስት እንደ አባት በመሆን ይህን ሚናውን እንዲጫወት ሲጠበቅበት በተቃራኒው ሕዝብ መንግስትን በልጦ የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
    በአሁኑ ጊዜ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ልቡ ይበልጡኑ ቆስሏል፡፡ ያቀረበው ሀይማኖታዊ የመብት ጥያቄ ምላሽ መነፈጉ ሳያንሰው መንግስት ራሱ ህጋዊ ሲለው የከረመውን አካሄድ ህገ-ወጥ አድርጎ ሲፈርጀው፣ በህግ አግባብ የሰየማቸውን ወኪሎቹን ህገ ወጥ ከማለቱም ባሻገር ሲያስፈራራ፣ ሲዝት፣ ሲያግት፣ሲያንገላታ እና ሲያስር ማየቱ፣ በህዝብ ግብር የሚተዳደሩ የህዝብ መገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” አይነት ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጭ ከዚህ የበለጠ ህዝብን ቅር የሚያሰኝ፣ህዝብን የሚያስኮርፍና የሚያስቆጣ ተግባር የለም፡፡ 
    መንግስት በአሁኑ ሰዓት እየተገበረው ያለው ስራ አስነዋሪ ነው፡፡ ሕገ ወጥ ነው፡፡ በእጁ ያለውን የህዝብ አደራ ያለ አግባብ በመጠቀም ላይ ይገኛል፡፡ ይህም የለየለት ሆኗል፡፡ ለዚህ ሁሉ አስነዋሪ እና ህገ ወጥ ተግባሩ የሚገባው የህዝብ ምላሽ ተመጣጣኝ መሆን ይገባው ነበር፡፡ ሆኖም ህዝበ ሙስሊሙ እያሳየ የሚገኘው ንቃትና ጨዋነት የተሞላበት አኩሪ ስነ-ምግባር መንግስትን ከዚህ በላይ እንዳይጓዝ እንቅፋት ሲሆንበት ታይቷል፡፡ ይህም ለመንግስት አካላት የራስ ምታት ሆኖባቸዋል፡፡ ምናልባት ይህ የሐይማኖት ጉዳይ መሆኑን ዘንግተውት ይሆናል፡፡
    ከባለፈው ሳምንት ዕሁድ ወዲህ ነገሮች በፍጥነት እና ባልተፈለገ አቅጣጫ እየተሾፈሩ ይገኛሉ፡፡ ህጋዊ ወኪሎቻችን በያሉበት ቦታ ታግተዋል አሊያም ታስረዋል፡፡ “እኛ የህዝብ አደራ የተሸከምን ሰላማዊ ዜጎች ነን፣ ህግ ጥሳችኋል ካላችሁና በህግ ፊት ከፈለጋችሁን ወከባ፣ሽብርና ዛቻ እንዲሁም ማስፈራራት አያስፈልጋችሁም፣ ለዚህ ስትሉ ስራ አትፍቱ የመኪና ነዳጅም አታባክኑ ሙሉ አድራሻዎቻችንን እንካችሁ በደቂቃ ውስጥ እኛው ራሳችን እናንተው ድረስ እንመጣላችኋለን” የሚል ድንቅ ንግግር ከወኪሎቻችን ቢነገራቸውም የደህንነት እና የፀጥታ አካላት እየወሰዱት ያሉት እርምጃ አሳፋሪ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የህዝብን የገነፈለ ቁጣ የሚጋብዝ ቢሆንም ህዝበ ሙስሊሙ ከነቃ ውሎ አድሯልና ነገሮችን በትዕግስት እና በሰከነ ሁኔታ መመልከትን መርጧል፡፡ 
    ህዝብ ሙስሊሙ ምንም እንኳን የመንግስትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ የሚያስተባብልበት ሁነኛ የመገናኛ መንገድ ባያገኝም ኢቴቪን እንደመልካም አጋጣሚ ይጠቀምበታል፡፡ የሚለፍፈውን በሀሰት መረጃ የታጨቀ ፕሮፓጋንዳ ላለመስማት ቴሌቪዥን ዘግቶ መቀመጥን እንደ ብቸኛ አማራጭ የወሰዱ በርካታ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ክፍሎች እንዳሉ ሁሉ ግድ ሆኖባቸው ከጣቢያው ሥርጭት ጋር የተገጣጠሙቱ ደግሞ የሚሰሙትን በተቃራኒው በመረዳት እውነታውን ይደርሱበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዘመን አመጣሹ የኢንተርኔት መረብ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ አሁን አሁን “ፌስ ቡክ ላይ ምን ተባለ?” በማለት የማይጠይቅ ሙስሊም የለም፡፡ ይህንን እውነታ በመረዳት የሚመራው አካል እውነታነታቸው የተረጋገጡትን፣ ፍጹም ከፀብ ጫሪነት፣ ከአመጽ ቀስቃሽነት እና ውለ ቢስ ከመሆን የራቁ መረጃዎችን በትኩሱ ከታማኝ ምንጮች በመውሰድ ለህዝቡ ያደርሳል፡፡
    ሆኖም ኢንተርኔት ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሊደርስበት የሚችል እንደመሆኑ መጠን ውዥንብር በመፍጠር ህዝቡን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ሊመሩት የሚችሉበት አጋጣሚ እጅግ ሰፊ ነው፡፡
    ህዝበ ሙስሊሙ በዚህ አጋጣሚ እነኚህን አካላት ጠንቅቆ ሊለያቸው ይገባል፡፡ለዚህም ዋነኛ መለያ ሊሆን የሚችለው የሰላማዊ ትግላችን ሂደት ፍፁም ሰላማዊና እና ከአመጽ የፀዳ መሆኑ መለያው ሲሆን ይህንን በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የመናድ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች መተላለፍ ሀሰተኛ እና የትግሉ አካል ያልሆኑ መሆናቸውን በቀላሉ መለየት ይቻላል፡፡
    ለምሳሌ “ዛሬ ተቃውሟችንን በዝምታ እንግለፅ” ሲባል በተቃራኒው “በተክቢራ ይደምቃል!” ወዘተ የሚሉ እና በሞባይል አጭር መልዕክት አማካይነት “ነገ ሁላችንም የስራ ማቆም አድማ እናድርግ” አይነት መልዕክቶች የሰላማዊ ትግላችን አካል አይደሉም፡፡ በመሆኑም መሰል መልዕክቶችን በጥንቃቄ ልንመለከታቸው ይገባል፡፡
    በተጨማሪም ኮሚቴዎቻችን በአሁኑ ሰዓት በእስር ላይ አሊያም በእግት ላይ መሆናቸውን እያወቅን በኢንተርኔት አለም የነሱን አድራሻ በመጠቀም በእነሱ ስም መልዕክት ለማስተላለፍ የሚደረግ ሙከራም አለ፡፡ ምንም እንኳን የሚያስተላልፉት መልዕክት ተቀባይነት እንዲኖረው ወደ እውነት የተጠጋ ቢመስልም አሁንም በጥንቃቄ ልንመለከተው ይገባናል፡፡ በተለይም መልዕክቱ ወደ አመጽ እና ረብሻ እንዲሁም ወደ ጥፋት የሚያዝ ከሆነ አይደለም በእንዲህ ሁኔታ እያሉ ይቅርና የነፃነት አየር በሚተነፍሱበት ሰዓት ከወኪሎቻችን አንደበት የሚፈልቁት ቃላት ሰላማዊ እና ሕጋዊ ብቻ ናቸው፡፡ ስለዚህም ይህ መልዕክት ከጀርባው ሰይጣናዊ አንደምታ ያለውና ከኮሚቴዎቻችን እንዳልሆነ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡
    ትግላችን በኮሚቴዎች መታሰር ምክንያት ሊዳፈን አይችልም፣ይቀጥላል፡፡ኢንሻ አላህ! ጉዟችን ተጀመረ እንጂ አልተቋጭም፡፡ ትግላችን መለያ ባህሪው ፍጹም ሰላማዊነቱ እና ቀጣይነቱ ሲሆን ማረፊያው ደግሞ ያነሳናቸው ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘታቸው ብቻ ይሆናል፡፡ የህዝቡን የልብ ትርታ የተከተሉ እና ወደ ምንፈልገው ግብ ሊደርሱን የሚችሉ ሰላምንና መረጋጋትን አደጋ ላይ የማይጥሉ እንዲሁም የትግላችንን ቀጣይነትና ውጤታማነት የሚያረጋግጡ ስትራቴጂዎች ይፋ ይሆናሉ፡፡ኢንሻ አላህ፡፡ እነኚህን በመከተል ተሰሚነታችንን እናረጋግጣለን፣ ያለምንም ኪሳራ መብታችንን እንጎናጸፋለን፡፡ ኢንሻ አላህ፡፡
    አላህ ይወፍቀን፡፡
    Read more
  • one of the largest ethiopian muslim group on Facebook request The diaspora community to send delegates to different Islamic countries

    one of the largest ethiopian muslim facebook group with over 26,000 member ETHIO ISLAMIC ART AND DA'AWA GROUP officially  request The diaspora community Badr ethiopia,first hijra , bilal communication,and other ethiopian islamic organizations in US and Europe please try to send your delegates to different Islamic countries and other influential countries as soon as possible. Read more
  • ሰበር ዜና!!!comitewochachen tortch eytedergu newu

    ሰበር ዜና!!!
    ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን!!!
    የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት የታሪክ ምሁሩ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ትላንት ለሊት በፌደራል ፖሊሶች ተይዘዉ ከታሰሩ ቡሀላ ለሊቱን ቶርች ሲገረፍ እንደነበር ከዉስጥ ያሉ ምንጮች አጋለጡ:: ያ አላህ ኧረ በቃችሁ በለን!!!
    yeh be endih endale wendm ustaz abubekrn ena wendm kamil shemsun ke cmc mesjid 400 meter 

    wered belo bemigegn bet west afenw yezewachewal, men eyaderguwachew endehon lenawk 

    alechalenm
    Read more
  • BRAKING NEWS የወንድም አክመል ነጋሽ እና የወንድም ይስሀቅ እሸቱ መኖሪያ ቤት በፖሊስ ተከቦ እየተፈተሸ ይገኛል

    በአሁኑ ሰአት የሙስሊሞች ጉዳይ መፅኤት አዘጋጅ የሆኑት የወንድም አክመል ነጋሽ እና የወንድም ይስሀቅ እሸቱ መኖሪያ ቤት በፖሊስ ተከቦ እየተፈተሸ ይገኛል:: ፈትሸዉ ሲጨርሱም ይዘዎቸዉ እንደሚሄዱ ይጠበቃል:: ኧረ ያ ጀምአ የኡማዉን ከገልጋዮች አስረዉ ጨረሱት እኮ!!! Read more
  • meninges yemuslimu bale weleta yehunuten comitewoch besheber wenjlo aserachewu

    የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የሆኑት
    ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል, 
    የታሪክ ምሁሩ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል , 
    ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፉ
     ሼህ መከተ ሞሄ, 
    ሼህ ሱልጣን እና
    ኡስታዝ ጀማል ያሲን 
    እንዲሁም የቄራ ሰላም መስጂድ ምክትል ኢማም ኡስታዝ ሰኢድ አሊ
    , ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የሙስሊሞች
     ጉዳይ መፅኤት ዎና አዘጋጁ ዩሱፍ ጌታቸዉ
     በሽብርተኝነት ፍርድ ቤት ተከሰሱ!! ዛሬ በአራዳ ክ/ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን አቃቤ ህግና ፖሊስ በሽብርተኝነት ክስ እንደመሰረተባቸዉ ለማወቅ ተችሏል:: ተጨማሪ የምርመራ ጊዜም አቃቤ ህጉ ለፍርድ ቤቱ የ28 ቀነ ቀጠሮ ጠይቆባቸዎል:: ያ ጀምአ የኡማዉ ብርሃኖችን በሀሰተኛ ዉንጀላ በእስር ቤት አጉሮ ሊጨርሳቸዉ ነዉ!! ኧረ በዱአ 
    Read more
  • የህዝበ ሙሰሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች መኖሪያ ቤት መከበቡን ምንጮቻችን አስታወቁ

    የህዝበ ሙሰሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች የኡስታዝ አቡበከር አህመድ የኡስታዝ አህመዲን ጀበል እና የኡስታዝ አህመድ ሙሰጠፉ መኖሪያ ቤት መከበቡን ምንጮቻችን አስታወቁ::እንዲሁም የታላቁ አሊም ዶ/ር ጄይላኒ ኸድር,የዶ/ር አብደላ እና የዶ/ር ከማል መኖሪያ ቤትም በፌደራል ፖሊስ መከበቡን ምንጮቻችን አስታዉቀዎል!! በዱአ እንበራታ!!!እንዲሁም የ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ በት በ አተሻ ላይ ነዉ  Read more
  • A Just and Peaceful Struggle OR as they said we are terrorists ?

    A Just and Peaceful Struggle

    Nuru Yimam, Annandale, Virginia

    The Aweliya brothers and sisters have been practicing nonviolent protest since January of 2012. From their humble beginnings, the brothers have been portrayed as extremist by the government. One of the intended purposes of the government was to divert attention from the actual validity of their arguments by discrediting them as terrorists, Jihadists, to simply isolate them from garnering public support from the general Muslim populace.

    Fortunately, the government’s sinister and dubious motives did not work.  Instead, it brought the entire Muslim population, despite their minor differences, under one fold.  Furthermore, the Christian and Muslim communities were united in support of the common democratic struggle.  I watched the Seventeen committee members’ press conference very attentively and none of them ever contradicted their method of struggle except as nonviolence.  Their call was for the government to respect and implement the constitution.

    As reported by various news outlets, just recently the government has cracked down and used forces ranging from guns, sticks, and tear gas in five areas of the city. These incidents occurred long after the Anwar Mosque mayhem that resulted in a number of deaths. Additionally, this was the second time the present regime violated the sanctity of mosques. Such actions by this undemocratic regime may force some of the youth to act out in vengeance or engage in violent reactions. My biggest fear is that some youth may fall into the government’s trap, which would give the government justification for its heavy-handed crackdown. The committee members’ appeal not to resort into violent retributions should be heeded.

     

    Since September 11, the West has associated violence with Islam despite the fact that extremists are in the marginal minority. Ethiopian Muslims are part of the majority of peace loving Muslims on the globe and have exemplified their peaceful and nonviolent character. It was therefore natural for the elected committee members to advocate for a peaceful protest through civil disobedience.

    The youth have to be constantly reminded that there are a number of Muslim conscientious objectors who are pacifists and are actively engaged in defending Islam without resorting to violence.  Iftikar Arsalan in his book “Islamic Pacifism- Global Muslims in the Post Obama Era” mentions a Muslim scholar; Sheikh Kunta Hajj of Chechnya, who is quoted as stating in his famous teachings: 

    “Defeat the evil men by your goodness and love… Defeat the greedy with your generosity…Defeat the treacherous with your sincerity…Defeat the infidel with your fidelity.”

    Our recent memory of the Egyptian revolution should not be forgotten too.  The uprising was mainly a campaign on nonviolent civil resistance which featured a series of demonstrations, marches, acts of civil disobedience and labor strikes.  Grievances of Egyptian protestors were mainly focused on legal and political issues.  In spite of the protestors’ just cause, the Mubarak regime reacted with heavy- handed brutality and many people died.   However, the leadership of the revolutionary movement was very focused on its objective, which was to elevate the demands of the people in a public domain without employing violent tactics or violent confrontation with the authorities. This strategy resulted in the humiliation and defeat of their despotic leader and his allies who ruled Egypt for thirty years.

    The Ethiopian Muslims’ demand is very simple; let us elect our leaders and keep the government’s hands out of our religious affairs.  For those who label this as extremism, I believe they have an ulterior motive to destroy the country and limit the progress that has been made so far.  No matter what silly names the likes of Dr. Shieferaw can conjure up inside their brains, the Muslim youth should continue their peaceful struggle.

    As long as the Aweliya leadership sticks to its demand and continue the just struggle, hopefully, victory will come to them.  Now is not the time to capitalize on emotions but rather reflect and think ahead.  Peaceful and nonviolent movements can affect positive sociopolitical changes within Ethiopia.

    I appeal to the young generation who are emotionally charged no to fall in the government’s trap by resorting to violence.  Dr. Martin Luther King Jr. once said that “peace is not mainly a distant goal that we seek but means by which we arrive at that goal.”

    The struggle Continues!

    Nuru Yimam

    Annandale, Virginia

    Read more
  • ትኩስ መረጃ leak from government about mejlis mercha

    ወንድሞችና እዚህ የሚገለጹ መረጃዎች ዝም ብለው እንዲነበቡ ብቻ ሳይሆን ከተነበቡ በሁዋላ ሁሉም በተቻለው አቅም መረጃውን በማዳረስም ሆነ የጸረ ሙስሊሞችን ሴራ ለማኮላሸት ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ሀላፊነታችንን እንድንወጣ ጭምር ነው፡፡ ትኩስ መረጃ 1. የፌዴራል ጉዳዮች የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ ከሰኔ 13 እስከ 15 እንዲሆን መወሰኑ ተሰምቷል፡፡ ምርጫውን በድንገት ህዝቡ ሳያስበው ለማካሄድና ቶሎ ለማጠናቀቅ ጥድፊያ ላይ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ ምርጫውን በቀበሌ በኩል ለማድረግና ህዝቡን ከረመዳን በፊት ለመሸወድ ስላሰቡ በገጠርም በከተማም የምንገኝ ሁሉ በየቀበሌያችን ያሉ እንቅስቃሴዎችን በጥብቅ መከታተል አለብን፡፡ በየወረዳችንና ዞናችን የሚገኙ የመጅሊስ ተወካዮችንም እንቅስቃሴ በደንብ እንቃኝ፡፡ ምክንያቱም የሽወዳ ስራ ለመስራት እንዳሰቡ ታውቆባቸዋል፡፡ ትኩስ መረጃ 2. ምርጫን በተመለከተ ጨምሮ የደረሰን መረጃ የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን አብዱላሂ በድጋሚ ለምርጫ መወዳደር መወሰኑንና ለምርጫ ቅስቀሳም ከሰሞኑ ሀረር ኮምቦልቻ ለሳምንት ያህል ከርሞ መመለሱ ተሰምቷል፡፡ ብር ለአካባቢው ህዝብ ሁሉ ሲበትንም እንደነበር ይነገራል፡፡ ፌዴራል ጉዳዮች ከኦሮሚያ ከሚመረጡ 50 የኦሮሚያ ተወካዮች 30 ሰዎችን መርጦ የጨረሰ ሲሆን 20ዎቹ ግን በህዝብ ይመረጣሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ሆኖም ከእነዚህ ህዝብ ከሚመርጣቸው 20 ተወካዮች መካከልም ፌዴራል ጉዳዮች የራሱን ሰዎች ለማስረግ ጥረት ያደርጋል፡፡ የመጅሊስ አመራሮችም በሙሉ ከሰሞን ለቅስቀሳ ወደየክልላቸው ይጓዛሉ፡፡ የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን አብዱላሂ ሰሞንን ለመጅሊስ ሰራተኞች እኛ ሰልጣን ብንለቅ እንኳ ተመርጠው የሚመጡ ሰዎች እኛ ካስቀመጥነው መንገድ ውጪ የመሄድ አማራጭም መብትም የላቸውም ብሎ ተናግሯል፡፡ አስመራጮችን በተመለከተ ፌዴራል ጉዳዮች ከኦሮሚያ ለሚመጡ 190 የአህባሽ ስልጠና የወሰዱ አስመራጮች ከዚህ ሰምንት ጀምሮ የ9ቀን ስልጠና ይሰጣል፡፡ ትኩስ መረጃ 3. በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ አባዲ ዘሙ መንግስት የአህባሽን ስልጠና እንዲያካሂድ ከአሜሪካ መንግስት 250 ሚሊዮን ዶላር መቀበሉንና ስልጠናውንም ሊያቆም እንደማይችል ሱዳን ኤምባሲ ውስጥ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን አብዱላሂ ጨሎም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሊባኖስ ቤሩት ከሚገኘው የአህባሾች ግሎባል ዩኒቨርሲቲ ጋር የአህባሽን ስልጠና በዘላቂነት ለመስጠት ፍርርምና ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከሰሞኑ ሀረር ውስጥ ገልጧል፡፡ አወሊያንም ትናንሽ ስልጠናዎች ሰጪ በማድረግ በሂደት ግን የአህባሽ ዩኒቨርሲቲ ለማድረግ መታሰቡም የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን ተናግሯል፡፡ ትኩስ መረጃ 4. የመጅሊስ አመራሮች በአሁኑ ሰአት የብር ፈሰስ የሌላቸው መሆኑ የታወቀ ሲሆን ሳኡዲ ለሐጅ በሄዱበት ወቅት ዘርፈው በኢትዮጵያ ቆንስላ በአደራ ያስቀመጡትን 8 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቅ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ አልቁድስ ጋዜጣም በብር እጥረት ምክንያት ክፍያው ቆሞበታል፡፡ ለዚህም ነው ከባለፈው ሳምንት ወዲህ ወሃቢያ እያለ ማላዘኑን ያቆመው፡፡ ትኩስ መረጃ 5. የመንግስት ሚዲያዎች በተለይም አዲስ ዘመን ሙስሊሞችን ማሻማቀቁን ቀጥሎበታል፡፡ አሁን ደግሞ አዲስ ዘመን ወሀቢያ እና ሱፊያ እያለ የሂላፍ አጅንዳዎችን በተከታታይ ለማተምና የተገኘውን አንድነት ለመናድ ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ ትኩስ መረጃ 6. የአዲስ አበባ መጅሊስን አስመልክቶ ፕሬዚዳንቱ ሰይድ ግዛውና ዋና ጸሐፈው ሁሴን ኑረዲን ከፍተኛ ጸብ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ የፀባቸው መንስኤ ብር ሲሆን ሁሴን ኑረዲን በግሎ መልምሎ ባስቀጠረው ምክትል ፕሬዚዳንት በኩል የፈለገውን ደብዳቤ እያስፈረመ ፕሬዚዳንቱን ድጋፍ አልባ ያደረገው ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ሰይድ ግዛውም ሁሴን ኑረዲን በመርዝ ይገድለኛል ብሎ በመስጋት አዲስ አበባ መጅሊስ ውስጥ ማኪያቶ እና ቡና እንኳ መጠጣት ማቆሙ ተሰምቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁሴን ኑረዲን ምርጫ እንዳይወዳደርና በምትኩም ሌላ ስራ እንደሚሰጠው በመንግስት ቃል ተገብቶለታል፡፡ የአዲስ አበባ መጅሊሱ ሁሴን ኑረዲን በየቦታው ቲሸርት የለበሱና ተክቢራ ያሉ ሰዎች ላይ በማስመስከር ለእያንዳንዱ መስካሪ 1300 ብር እየከፈለ ይገኛል፡፡ መስካሪዎቹ ፍርድ ቤት ሄደው ከመመስከራቸው በፊት ምን ብለው መመስከር እንዳለባቸው የአዲስ አበባ መጅሊሱ ሁሴን ኑረዲን እና አቶ ሰይድ ኢብራሂም የተባለ ለምስክርነት በመጅሊሱ የተቀጠረ ሰው ገለጻ እንደሚሰጧቸው ታውቋል፡፡ ትኩስ መረጃ 7. የአዲስ አበባ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስብሰባ ጠርቶ የነበረ ቢሆንም በብዙዎቹ ቦታዎች 500 ሰው ተጠርቶ የተገኘው 30 እና 40 ስው ብቻ በመሆኑ በብዙዎቹ ቦታዎች ስብሰባው ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ሆኖም ስብሰባዎቹ በተካሄዱባቸው ቦታዎች በየመስጊዱ ተክቢራ የሚሉና የሚያስብሉ ሰዎችን አሳልፋችሁ ስጡን ብለው ጠይቀዋል፡፡ ግን ስብሰባዎች ብዙም ሳይሳካላቸው ቀርተዋል፡፡ Read more

Latest Articles

Most Popular