BILAL TUBE NEWS AMHARIC

  • ከተባረክ መስጅድ አራት ሰዎች ታሰሩ

    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 6/2004 በአዲስ አበባ ሜክሲኮ ጀርመን ግቢ እየተባለ ከሚጠራው መስጂድ ጀመዐ አራት ሰዎች መታሰራቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡ ግለሰቦቹ የታሰሩት ትላንት በስቲያ ምሽት ላይ ነው፡፡የታሰሩበት ምክኒያት ደግሞ ድምፃችን ይሰማ የሚል በራሪ ወረቀት በየመስጂዱ ለመበተን ተንቀሳቅሰዋል የሚል ነው፡፡ ግለሰቦቹ ዛሬ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ህንፃ አካባቢ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ታይቶ ነበር፡፡ Read more
  • በምስራቅ ሀረርጌ የመንግስት አስተዳዳሪዎች የሙስሊሙ ህብረተሰብ አህባሽን እንዲቀበል መገደዱ ተነገረ፡፡

    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 2/2004 በምስራቅ ሀረርጌ ከሚገኙ 19 ወረዳዎች ውስጥ አንዷ በሆነችው በጭናቅሰን አካባቢ የወረዳው አስተዳዳሪ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የአህባሽን መንገድ መከተል እንዳለበት መግለፃቸው ተጠቆመ፡፡ ውሃቢያን ለመዋጋር ከ19ኙም የምስራቅ ሀረርጌ ወረዳዎች ሦስት ሦስት ሰዎችን በመምረጥ ስልጠና መዘጋጀቱንና ከዞኑ ትህዛዝ መተላለፉን የሬዲዮ ቢላል ምንጭ ከአካባቢው አድርሶናል፡፡ የጭናቅሰን ወረዳ አስተዳዳሪና የወረዳው የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ ህብረተሰቡ ውሃብያና አህሉልተውሂዶችን መዋጋት እንዳለበትና ለምርጫና ለስልጠና ከ19ኙም ወረዳዎች ሦስት ሦስት ሰዎች መዘጋጀት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ የአካባቢው ሙስሊም ህብረተሰብ በበኩሉ መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ መግባት የምንከተለውን ሀይማኖት ሊመርጥልን አይገባም ትክክለኛውን የነብዩ(ሰ.ወ) መንገድ እየተከተልን ነው ማለታቸውን ከአካባቢው ምንጭ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተያያዘ ዜና በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በመዩ ሉቄ ወረዳ 27 ሰዎች ከሰላትና ከስራቸው አንዱን እንዲመርጡ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው ውስጥ በሰላት ምክኒያት ከስራ መታገዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንደ አካባቢው ምንጭ በምስራቅ ሀረርጌ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ እየተፈጠረ ያለው ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ Read more
  • በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቅዱስ ቁርዓንን ክብር ያጎደፈው ግለሰብ ድርጊቱን እንደፈጸመ አመነ፡፡

    በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቅዱስ ቁርዓንን ክብር ያጎደፈው ግለሰብ ድርጊቱን እንደፈጸመ አመነ፡፡ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 23/2004 በጎንደር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ተቆጣጣሪ የነበረው ግለሰብ የቅዱስ ቁርዓንን ገፆች መፀዳጃ ቤት መጠቀሙን አመነ፡፡ ግለሰቡ ድርጊቱን መፈፀሙን ያመነው ከትላንት በስቲያ ለፖሊስ በሰጠው የእምነት ክሀደት ቃል ነው ለምን ድርጊቱን እንደፈፀመ ሲያስረዳም በመፅሀፉ ስለማያምንበት መሆኑን ገለልጾዋል፡፡ ፖሊስ የእምነት ክህደት ቃን ከተቀበለ በኋላ ከሌሎች ማስረጃዎች በማያያዝ በአቃቢ ሕግ ክስ እንደሚመሰረትበት አስታውቋል ፡፡ ይህንኑ ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ግለሰቡ ስራው በስራው እንዲሰናበት ደብዳቤ በዩኒቨርስቲው ሶስቱም ካምፓሶቹ ለጥፏል፡፡ ከስራ ማሰናበት ብቻም ሳይሆን ጠበቃ በማቆም በህግ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ክትትል እንደሚያደርግ መግለፁን የአካባቢው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ Read more
  • የፖሊስ አባላት የሆኑ ሙስሊሞች መለዮ አድርገው መስጂድ እንዳይገቡ የክልከላ ትዛዝ ተሰጣቸው

    የፖሊስ አባላት የሆኑ ሙስሊሞች መለዮ አድርገው መስጂድ እንዳይገቡ የክልከላ ትዛዝ ተሰጣቸው አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 24/2004 በአዲስ አበባ አስተዳደር የሚገኙ ሙስሊም ፖሊሶች መለዮ አድርገው ወደ መስጂድ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የሬዲዮ ቢላል ምንጮች አስታወቁ፡፡ ምንጮቻችን ዛሬ እንዳስታወቁት መለዮ አድርገው ወደ መስጂድ እንዳይገቡ የተከለከሉት 22አካባቢ በሚገኘው የትራፊክ ፅ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ባለፈው አርብ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በተሰጠው አዲስ መመሪያ ነው፡፡ በስብሰባው የተሳተፉ ሙስሊም የትራፊክ ፖሊስ አባላት በወቅቱ በሰጡት አስተያየት እገዳውና ክልከላው ህገ መንግስታዊ የሀይማኖት ነፃነትና መብት ድንጋጌዎች እንደሚፃረር ገልፀዋል፡፡ ይሁንና የመድረኩ መሪ የሆኑ አዛዦች መመሪያው ከመጋቢት 21 ቀን ጀምሮ የፀና መሆኑን ገልፀዋል፡፡በእለቱ በስራ ላይ የነበሩ ሙስሊም የፖሊስ አባላት የጁምዐ ሰላት ለመስገድ መለዮአቸውን ሌላ ቦታ አስቀምጠው ለመስገድ የተገደዱ ሲሆን አንዳንዶቹ ማዕረጋቸውን ብቻ በማውለቅ ወደ መስጂድ ሲገቡ መታየታቸውን ምንጮቻችን አስረድተዋል፡፡ Read more
  • በላሊበላ ከተማ በመንገድ ላይ ሰላት በመስገድ አንድ አመት የተፈረደበት ወጣት ይግባኝ ጠየቀ

    በላሊበላ ከተማ በመንገድ ላይ ሰላት በመስገድ አንድ አመት የተፈረደበት ወጣት ይግባኝ ጠየቀ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 22/2004 የመግሪብ ሰላቱን መንገድ ዳር የካቲት 24/2004 አባ ወልደ ሰንበት ዋሻ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ላይ በመስገዱ ነው ወጣቱ የታሰረው፡፡ ገና በሰላቱ ላይ እያለሁ ከ100 ሰው በላይ ከበበኝ ከዚያም ፖሊስ መጣና ይዞኝ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደ ፡፡ ቃል ስጥ ተባልኩ ቃሌን ሰጠሁ ብሏል፡፡ የሰገድክበት ቦታ የጊዮርጊስ ክልል ነው ቢሉኝም መከለሉን ሳላውቅ መስገዴን አስረድቻለሁ በኋላም እኔ ከቤተ ክርስቲያኑ 600 ሜትር በላይ እርቀት ላይ ነው የሰገድኩት ብያለሁ ነው ያለው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአካባቢው ነዋሪዎች በአህላል ሻሮች የተሰጠ 476 ካ.ሜ የመስጂድና 2000 ካ.ሜ የቀብር ቦታ እንደተወሰደባቸውም ከስፍራው ያገኘነው የሬዲዮ ቢላል ምንጭ ገልፀዋል፡፡ Details Category: News In Amharic Read more
  • በአዲስ አበባና በጅማ ከተማ በሚገኙ መስጂዶች ከፍተኛ የተክቢራ ስነ ስርዓት ማካሄዳቸው ተገለፀ

    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 21/2004 ለተከታታይ 11 ሳምንታት በአወሊያ ተካሂዶ በነበረው የመጅሊስን ተቃውሞ እንቅስቃሴ ለሶስት ሳምንታት መቋረጡንና ህዝቡ የመስጂዱ ሰላማዊ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል በኮሚቴዎቹ መልዕክት መተላለፉ ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ዛሬ በአንዳንድ የአዲስ አበባ መስጂዶች እና በክልል መስጂዶች መጅሊስና የአህባሽ አስተምህሮት በመቃወም የተክቢራ ሰነ-ስርዓት መካሄዱ ተገለፀ፡፡ በባዩሽ በአንሱር፣በተባረክ ፣መስጂዶች የተካሄዱ እንቅስቃሴዎች ከአዲስ አበባ መስጂዶች ይጠቀሳሉ ይህ በእንዲህ እንዳለ በኑር መስጂድና በታላቁ አንዋር የተገኙ ዱዓና የድምፃችን ይሰማ የሚል ፅሁፍ በህብረተሰቡ መበተኑን በስፍራው ወነበሩ ሪፖርተሮቻችን ዘግበዋል በተመሳሳይ በጅማ ከተማ በሚገኙ ሁሉም መስጂዶች ዛሬ በተካሄደው የጁምዐ ሰላት ስነስርዓት መጠናቀቅ በኋላ ምዕመናኑ ተክቢራ ማሰማታቸውን ከምንጮቻችን ገለጻ ለማወቅ ተችሏል፡፡ Read more
  • በሐረሪ ክልል አዲሰ የዑለሞች ምክር ቤት ተቋቋመ የምክር ቤቱ ክንፍ ሆኖ የሚሰራ የፈትዋ ዳዕዋ ኮሚቴም ተደራጅቷል፡፡

    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 21/2004 በሐረር ክልል ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እንዲሁም ከሐረር ከተማ ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ ዑለሞች የራሳቸውን የዑለሞች ምክር ቤት አቋቋሙ ካቋቋሙት ምክር ቤት በተጓዳኝ የፈትዋ ዳዕዋ ኮሚቴ አደራጅተዋል፡፡ አዲስ የተቋቋመው የሐረር ክልል ዑለሞች ምክር ቤት አባል ዛሬ ለሬዲዮ ቢላል እንዳስታወቁት ምክር ቤቱን በክልል በዞንና በወዳ ደረጃ ማቋቋም ያስፈለገው የቀድሞው መጅሊስ አመራር አባላት በክልሉ ሕዝበ ሙስሊም እውቅና የተነፈጋቸው በመሆኑ ነው፡፡ ነባሩ መጅሊስ አመራር በክልሉ ህዝብ እውቅና የተነፈገው በመሆኑም ህብረተሰቡ ኢስላማዊ አገልግሎት የሚሰጥ የተደራጀ አካል በማስፈለጉ የዑለሞች ምክር ቤት ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አስረፍተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የምዕራብ ሀረርጌ ወረዳዎችን የሚወክሉ አባላት ያሉት ሐረርጌ ወረዳዎችና ከሐረር ከተማ የተውጣጡ 20 አባላት ያሉት የዑለሞች ምክር ቤት መቋቋማቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከሁለቱም ዞኖችና ዳዕዋ ኮሚቴዎች የዑለሞች ምክር ቤቶች ጋር በጥምረት የሚሰሩ የፈትዋና ዳዕዋ ኮሚቴዎች መደራጀታቸውንም የዑለሞች ምክር ቤቱ አባል አስረድተዋ፡፡ የዑለሞች ምክር ቡቱ ነበሩ መጅሊስ ያተወጣቸውን ኃላፊነቶች ለመወጣት የሚያሻሽሉት ዝርዝር የሥራ ኋላፊነት እንደሚኖር ተናግረዋል ፡፡ መድረሳ የማቋቋም ዳዕዋ የማካሄድ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት የማጠናከር ፣በሀገራዊ ጉዳቶች ተሳትፎ እንዲያደርግ የማበረታቻ ፣ፀረ ኢስላም አቋሞችንና አመለካከቶችን የመታገል ኃለፊነቶች እንደሚኖሩት አብራርተዋ፡፡ በተመሳሳይ የፈትዋና የዳዕዋ ኮሚቴው ማብራሪያ በሚፈለጉ ጉዳዮች ላይ ከሸሪኸው አንፃር ማብራሪያ የመስጠትና የዳዕዋና ኹጥባ ፕሮግራሞችን የማስተባበር ኃላፊነት እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ የዑለሞች ምክር ቤቶች አባላት በህዝብ ሠፊ ተቀባይነት ያላቸው ዑለሞች ፣የመስጂድ ኢማሞች የአገር ሽማግሌዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የሁለቱ ዞን ዑለሞች ምክር ቤት በክልል ደረጃ ሃጂ ቀመር አብዱላሂ የፈትዋና የዳዕዋ ኮሚቴውን ደግሞ ሸህ ጀማል ሰኢድ በሊቀመንበርነት እንደሚመሩት ለማወቅ ተችሏል፡፡ Read more
  • የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ነገ ጁምዓ በአንዋር እና በኑር መስጂድ ህዝበ ሙስሊሙን እንዳልጠራ አረጋገጠ

    የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ነገ ጁምዓ በአንዋር እና በኑር መስጂድ ህዝበ ሙስሊሙን እንዳልጠራ አረጋገጠ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 20/2004 የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ነገ ጁምዓ አንዋር መስጂድና በኑር መስጂዶች ሙስሊሙን እንደጠራ ተደርጎ እየተናፈሰ ያለው ወሬ የተሳሳተ መሆኑ ተገለፀ፡፡ መሀል አዲስ አበባ ዛሬ በስፋት እየተወራ የሚገኘው ይህ መረጃ ከኮሚቴው አባላት እንዳልተላለፈ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢው ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ለሬዲዮ ቢላል አስታውቀዋል፡፡ ይሁንና ነገ ጁምዐ ህብረተሰቡ በየአካባቢው ባሉመስጂዶች የሚያደርገው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ካለ ሂደቱ ሠላማዊ ሊሆን እንደሚገባው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ህብረተሰቡ ሰላሙን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት ያሉት ዑስታዝ አቡበከር አህመድ በየአካባቢው የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሠላማዊ መሠረትና መስመራቸውን የጠበቁ እንዲሆኑም አሳስበዋል፡፡ Read more
  • yemuslimu tegele beyemeskidu endeqetele tenegere Allahu akber

    በአወሊያ ሲካሄድ የነበረው የሙስሊሙ ህብረተሰብ የመብት ጥያቄ በመስጂዶችም ቀጥሏል አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት17/2004 ለተከታታይ 11 ሳምንት በአወሊያ ሲካሄ የነበረው በአሁኑም ወቅት በከተማዋ ባ ሌሎች መስጂዶች መጀመሩን በየመስጂዱ የሚገኙ ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡ ታቃውሞው እየተገለፀያለው በተክቢራ ሲሆን እንቅስቃሴው ከተጀመረባቸው መስጂዶች መካከል የአንዋር የቄራ እንደሚጠቀሱ ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ የመፍትሄ አፈላላጊው ኮሚቴው ባለፈው ጁምዓ ከአወሊያ ኢስላማዊ ማዕከል ለተገኘው ሕዝብ ሙስሊም በየአካባቢው በሚገኙ መስጂዶች ሕዝቡ ሰላማዊ ትግሉን መቀጠል እንደሚችል ጠቅሶ ነበር፡፡ ኮሚቴው በቀጣይ ሶስት ሳምንታት ጅምር እንቅስቃሴዎች አጠናክሮ በመቀጠል የደረሰበትን ለህዝበ ሙሊሙ እንደሚያሳውቅ ቃል መግባቱ አይዘነጋም ፡፡ የህን ተከትሎ ባፈው ጁምዓ ቅዳሜ በርካታ ምዕመናን በየአቅራቢያቸው በሚገኙ መስጂዶች የህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጣቸው በተክቢራ ጠይቀዋል፡፡ Read more
  • be tegray Imamu yale mekniyat taseru

    በትግራይ ክልል መሆኒ ከተማ ኢማሙ ባልታወቀ ምክኒያት ታሠሩ ኢማሙ ትላንት የጁምዓ ሠላት ከተሰገደ በኃላ ነው ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ያዋሏቸው፡፡ የሬዲዮ ቢላል ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት ከዛሬ 6 ዓመት በፊት በከተማዋ በሚገኘው ዋና መስጂድ መሰገድ በመከልከላችን ሣቢያ አንድ ባለሀብት ቤት ውስጥ ለ4 ዓመታት በመድረሳም በመስጂድም መልክ ስንጠቀምበት ብንቆይም በየግዜው የሚመነጡት ማስፈራሪያዎች ስጋት ጥሎብናል ብለዋል፡፡ ኃላም ይህ እየሰገዳቹ ያላችሁት ቤት እውቅና የለውም በሚል እንደወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ ኢማሙ የታሰሩበትንም ምክኒያት ሲያስረዱ እናንተ አሸባሪዎችና ዋሃቢዮቸ ናችሁ በሚል ምክኒያት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ Read more

Latest Articles

Most Popular