BILAL TUBE NEWS AMHARIC

  • mjlish tegelun lemebeten gebre hayl eyaquwaqeme newu

    መጅሊስ ሠላማዊ ትግሉን ለመበተን ግብረኃይል እያቋቋም ነው አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 8/2004 የሚካሄደውን የሕዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል ለመበተን የሚያስችለውን ግብረ ኃይል እያደራጀ መሆኑ ተገለፀ፡፡ መጅሊሱ ዛሬ ጦርኃይሎች በሚገኘው ቅጥር ግቢው ከመዲናዋ የተለያዩ መስጂዶች ኢማሞች ጋር ባካሄደው ውይይት እንዳስታወቀው እየተጠናከረ የመጣውን የሕዝቡን ተቃውሞ ለመበተን የሚየስችል እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ባውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት የተለያዩ ኢማሞችና ዱዓቶች ሥራ መሰራቱን ለሬዲዮ ቢላል አስታውቀዋል፡፡ ለደህንነታችን እንደሰጋለን ያሉ አስተያየት ሰጪዎቻችን እንዲገልፁት የመጅሊሱን እንቅስቃሴና የስብሰባ አጀንዳ ግልፀኝነት እንደሚጎድለው አመልክተዋል፡፡ ዛሬ ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ የሼህ አብደላ አልሃረሪ መፀገፎች መበተናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በስብሰባው በርካታ ወጣት ዳዒዎች፣ዑስታዞች እንዳይሳተፉ ታግደዋል፡፡ተሳታፊዎቹ የተመረጡት በመጅሊሱ አመራሮች መሆኑንም ታማኝ ገልጸዋል፡፡ Read more
  • በትግራይ ክልል መሆኒ ከተማ ኢማሙ ባልታወቀ ምክኒያት ታሠሩ

    ኢማሙ ትላንት የጁምዓ ሠላት ከተሰገደ በኃላ ነው ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ያዋሏቸው፡፡ የሬዲዮ ቢላል ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት ከዛሬ 6 ዓመት በፊት በከተማዋ በሚገኘው ዋና መስጂድ መሰገድ በመከልከላችን ሣቢያ አንድ ባለሀብት ቤት ውስጥ ለ4 ዓመታት በመድረሳም በመስጂድም መልክ ስንጠቀምበት ብንቆይም በየግዜው የሚመነጡት ማስፈራሪያዎች ስጋት ጥሎብናል ብለዋል፡፡ ኃላም ይህ እየሰገዳቹ ያላችሁት ቤት እውቅና የለውም በሚል እንደወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ ኢማሙ የታሰሩበትንም ምክኒያት ሲያስረዱ እናንተ አሸባሪዎችና ዋሃቢዮቸ ናችሁ በሚል ምክኒያት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ Read more
  • መጅሊስ ሠላማዊ ትግሉን ለመበተን ግብረኃይል እያቋቋም ነው

    የሚካሄደውን የሕዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል ለመበተን የሚያስችለውን ግብረ ኃይል እያደራጀ መሆኑ ተገለፀ፡፡ መጅሊሱ ዛሬ ጦርኃይሎች በሚገኘው ቅጥር ግቢው ከመዲናዋ የተለያዩ መስጂዶች ኢማሞች ጋር ባካሄደው ውይይት እንዳስታወቀው እየተጠናከረ የመጣውን የሕዝቡን ተቃውሞ ለመበተን የሚየስችል እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ባውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት የተለያዩ ኢማሞችና ዱዓቶች ሥራ መሰራቱን ለሬዲዮ ቢላል አስታውቀዋል፡፡ ለደህንነታችን እንደሰጋለን ያሉ አስተያየት ሰጪዎቻችን እንዲገልፁት የመጅሊሱን እንቅስቃሴና የስብሰባ አጀንዳ ግልፀኝነት እንደሚጎድለው አመልክተዋል፡፡ዛሬ ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ የሼህ አብደላ አልሃረሪ መፀገፎች መበተናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በስብሰባው በርካታ ወጣት ዳዒዎች፣ዑስታዞች እንዳይሳተፉ ታግደዋል፡፡ተሳታፊዎቹ የተመረጡት በመጅሊሱ አመራሮች መሆኑንም ታማኝ ገልጸዋል፡፡ Read more
  • be alamata 4 gelsboch taseru be ahbash mekniyat

    በአላማጣ ከተማ አራት ግለሰቦች መታሰራቸው ተገለፀ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 4 2004 በአላማጣ አካባቢ የአህባሽን አስተምህሮት ለመስጠት የሄዱ ግለሰቦች ለማስተናገድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው፡ የአህባሽን አስተምዕሮት ለመስጠት አላማጣ አካባቢ ግለሰቦቹ የተንቀሳቀሱት ባለፈው ቅዳሜ ነበር፡፡ ሁለት ኢትጲያውያንና አንድ ሊባኖሳውያን የአህባሽ አስተምህሮት ለአምስት ቀናት በአላ አካባቢ ከሚገኘው መስጂድ ለመሰጠት ያሰቡት ጉዞ ግን አልተሳካም፡፡ ምክኒያቱ ደግሞ የአካባቢው ሰዎች አስተምህሮቱን አንቀበልም በማለታቸው ነበር፡፡ አስተምህሮቱን በኃይል የመጫን እንቅስቃሴው ታዲያ እስር ማስከተሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ሁለት የመስጂድ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ግለሰቦችም መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል፡፡ Read more
  • BE DESE 10 WETATOCH TASERU በደሴ 10 የሚሆኑ ወጣቶች ታሠሩ

    በደሴ 10 የሚሆኑ ወጣቶች ታሠሩ የሸዋ በር መስጂድ ኢማም ዛቻና ማስፈራሪያ ደረሰባቸው በደሴ ከተማ ሰሞኑን በተለያየ ጊዜ 10 ወጣቶች በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ወህኒ መውረዳቸውን ምንጮች አስታወቁ ታማኝ የሬዲዮ ቢላል ምንጮቻችን ከሥፍራው እንዳደረሱን ወጣቶቹ የታሰሩት ህዝበ ሙስሊሙ ከሕገመንግስቱ ጋር የተያያዙ የኃይማኖት የመብት ጥያቄዎቹን ማሰማት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ይሁንና በተጨማሪ የተያዙት ጉዳይ ምን እንደሆነ በግልፅ የታወቀ ነገር አለመኖሩን አመልክተዋል ወጣቶቹ ባለፈው ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ፖሊስ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ይሠጠኝ በማለቱ ክስ ሳይመሰረትባቸው ቀርቷል ፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ የሸዋ በር መስጂድ ታዋቂ አሊም የሆኑት ሼህ ያቁት በደሴ ከተማ ወረዳ እስተዳደር አካላት ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡ ሬዲዮ ቢላል የካቲት 30/2004 MARCH 9, 2012 Read more
  • be adewa muslimoch bemskid selat hone quran tekelekelu gud eko newu

    የአድዋ ሙስሊሞች በመስጂዳቸው ሰላት መስገድም ሆነ ቁርኣን መቅራት ተከለከሉ አድዋ አካባቢ የሚኖሩ ሙስሊሞች በመስጂድ ውስጥ ሰላት መስገድም ሆነ ቁርኣን መቅራት አትችሉም ተብለው መታሠራችን እና በፍርድ ቤት ትህዛዝ እያንዳንዳቸው 800 ብር ተቀጥተው ከዚህ በኋላ በስፍራው መስገድም ሆነ ቁርአን መቅራት እንደማይችሉ ተነግሮአቸው መለቀቃቸውን ገለፁ፡፡ Read more
  • berari wereqet betenewal yetebalut tefetu

    በራሪ ወረቀት በትናችኋል በሚል ታስረው የነበሩት ወጣቶች ተፈቱ

    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል የካቲት 16/2004

    ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ምንጩ ያልታወቀ በራሪ ወረቀት አወለያ መስጂድ አካባቢ በትናቹኋል በሚል ታስረው የነበሩት ወጣቶች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ተፈቱ፡፡

    በአወልያ እየተሰገደ ባለው የጁምዓ ሰላት ላይ አህባሽንና መጅሊስን የሚቃወም በራሪ ወረቀት ለህዝበ ሙስሊሙ ለመበተን ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ነበር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ፡፡

    ከታሰሩት ውስጥ ሰሚር የተባለ ወጣት ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደነበረና እህቱን በስልክ አነጋግረን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

    ይህ ምንጩ አልታወቀም ተብሎ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የተደረጉት ወጣቶች ወረቀቱን እንዲበትኑ ያዘዟቸውን ሰዎች እስካልጠቆሙ ድረስ በእስር እንደሚቆዩ ተገልፆላቸው ነበር፡፡ በፖሊስ ጥቆማ ሲፈለግ የነበረው አብዱረዛቅ የተባለው ወጣት ፖሊስ ጣቢያ ቀርቧል፡፡ እርሱ ከቀረበ በኋላም እሱና ሌሎቹ ቀድመው የታሰሩት ጓደኞቹ ተፈተዋል፡፡

    Read more

Latest Articles

Most Popular