BILAL TUBE NEWS AMHARIC

 • የአወሊያ የህዝብ ንቅናቄን ተከትሎ የተቋቋሙ ኮሚቴ ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ባካሄደው ውይይት ተስፋ ሰጪ ምላሽ ማግኘቱን ገለፀ

  ጥር 21/2004 ላለፉት አራት ተከታታይ የጁመዓ ሰላቶች በአወሊያ የተካሄደውን የህዝበ ሙስሊሙ ጠንካራ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ተከትሎ የተቋቋመው መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በተካሄደው ውይይት ተስፋ ሰጪ ምላሽ ማግኘት መቻሉን አስታወቀ፡፡ ኮሚቴው ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር የሚያካሄደውን ውይይት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የፊታችን ረቡዕ ቀጣይ ውይይት ለማድረግ የሚያስችለውን ቀጠሮ እንደያዘም አመልክቷል፡፡ ኮሚቴው በአወሊያ ሰሞኑን በተከታታይ የተካደውን ጠንካራ የሕዝብ ንቅናቄ ተከትሎ ነው የተቋቋመው… በትዕይንተ ሕዝቡ ተሳታፊ በሆኑ የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ኮሚቴው ሲሰየም ስድስት አባላትን ያካተተ ነበር፡፡ ባለፈው ጁመዓ ደግሞ አቅሙን አጠናክሮ ወደ 16 አባላትን በማቀፍ መፍትሔ ማፈላለግ ስራውን ተያይዞታል፡፡ ወጣት ዳዒያንን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ ዑለሞችንና ተሰሚነት ያላቸውን ተዋቂ ምሁራንን ያሰባሰበው ይኼው ኮሚቴ ለሚሊዮኖች ቅሬታ ዘላቂ መፍትሔ የማፈላለግ ኃላፊነቱን ከተረከበ ከሳምንት ያለፈ ዕድሜ የለውም፡፡ ሆኖም በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ከኮሚቴው አባላት መካከል ዘጠኙ የተሳፉበትን ውይይት ከሁለት የመንግስት ከፍተኛ ባስልጣናት ጋር ማካሄድ ችለዋል፡፡ ውይይቱ የተካደው ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ሽፈራው ተ/ማሪያምና ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ ጋር ሲሆን ለሶስት ሰዓታት ያህል የዘለቀ ነበር፡፡ የኮሚቴው አባላት ለሚኒስትሮች ያነሷቸው ነጥቦች በሶስት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ እንደሆኑም በውይይት ተሳታፊ የነበረው ዳዒ ያሲን ኑሩ ይናገራል፡፡ የመጅሊስ አመራር ምርጫ ይካሄድ፣ የአህባሽ ቡድን አስተምህሮትና ጫና ይቁም፣ የመንግስት የኃይማኖት ጣልቃ ገብነት ይቁም፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተተገበረ ያለው መመሪያ የህዝበ ሙስሊሙን ነፃነት ይጋፋልና ይስተካከልል የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የአወሊያ ኢስላማዊ ማዕከል የህዝብ ነውና ሕዝባዊነቱን ጠብቆ ይተዳደር የሚለውን ነጥብ ጨምሮ ሁለቱም ሚኒስትሮች በኮሚቴው አባላት ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ በተነሱት ሕዝባዊ ቅረታዎች ዙሪያ ከሚኒስትሮች መፍትሔ ለማፈላለግ የሚረዳ ተስፋ ሰጪና በጎ ሊባል የሚችል ምላሽ መገኘቱን ዳዒ ያሲን ኑሩ ገልፆልናል፡ Read more
 • መጅሊስ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የለጠፈው ማስታውቂያ ያለበትን ጭንቀት እንደሚያመላክት ተገለፀ

  ጥር 23/2004 የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለአዲስ አበባ ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ከትናንት ጀምሮ እየለጠፈ ያለው ማስታውቂያ ጭንቀቱን እንደሚያመላክት አስተያየት ሰጪዎች ገለጹ፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ ዛሬ ለሬዲዮ ቢላል እንዳስታወቁት መጅሊሱ የለጠፈው ማስታውቂያ ከህብረተሰቡ እየደረሰበት ያለውን ከባድ ጫናና ተቃውሞ ተከትሎ የተፈጠረበትን ውጥረት የሚያስረዳ ነው፡፡ የአወሊያ የጁመዓ አድማ የ1987 አሳዛኝ ስተት ናፋቂዎች ድርጊት እንደሆነ የገለፁበትን ይህን ማስታውቂያ ህብረተሰቡን ይበልጥ እያስቆጣው እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም ህበረተሰቡ ማስታውቂያውን በመገንጠል ተቃውሞውን መግለፅ መጀመሩን አመልክተዋል፡፡ አወሊያ ሊወሰድ ነው አረብኛ ትምህርት ሊዘጋ ነው አህባሾች ከአገራችን እንዲወጡ መንግስትን እንወትወት በማለት እንቅቃሴ የሚያደርጉትን እንዳትቀበሉ የሚል ይዘት ያለው ነው፡፡ Read more
 • በትግራይ ክልል መሆኒ ወረዳ ኩኩፍቱ ከተማ 16 ሙስሊሞች መታሠራቸው ተገለፀ

  አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ጥር 25/2004 ሙስሊሞቹ የታሠሩት በከተማዋ የሚገኘውን ኡመር ኢብን አብድል አዚዝ የተባለውን የጀመዓ መስጂድ ይዘጋ አይዘጋ በሚል እሠጥ አገባ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ከ8 ዓመታት በፊት ነበር ከዚህ ወረዳ ግጭት ተነስቶ የነበረው ጉዳዩም በባህልና በሐዲስ መቀላቀል ሳቢያ ነው የአካባቢው ዑለሞች በጉዳዩ በመምከር እልባት ሰጥተውትም አልፈዋል፡፡ ነገር ግን አሁን መጅሊስ አህባሽ የተባለውን አስተምህሮት ካልተከተላችሁ በሚል በጀመዓ ስንሰግድበት የነበረውን የኡመር ኢብን አብደልአዚዝ መስጂድን ዘግቶብናል ብለዋል ከስፍራው መረጃውን ያደረሱን ምንጮቻችን፡፡ በአሁኑ ሰዓትም 16 ሙስሊሞች በመሆኒ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ መታሠራቸውን ነግረውናል፡፡

  Read more
 • በኢትዮጵያ በኃይማኖት ዘላቂነት ያለው ሰላምና መቻቻል ማረጋገጥ እንደሚገባ በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ የተካሄው ኢስላማዊ ኮንፈረንስ ጉባኤ ተሳታፊዎች አመለከቱ ፡፡

  የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ላለፉት ሦስት ቀናት ሰላም የሕይዎት ቁልፍ አካል ነው በሚል ርዕስ ያካሄዱትን ኮንፈረንስ ትናንት ማምሻውን ሲያጠናቅቁ ባወጡት የጋራ መግለጫ ነው ይህን ያሉት፡፡ በኃይማኖት መካከል የመቻቻል ባህልን ማዳበርና ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮችን በመለየት በህግ ማዕቀፍ ክልከላ ማድረግ እንደሚገባም ተሳታፊዎቹ አመልክተዋል፡፡ በኮንፈረንሱ ላይ ከአውስትራሊያ፣ እንግሊዝ ፣ ቱርክ፣ ኢዶኖዢ ፣ ደቡብ አፍሪካና ከሌሎች 50 የዓለማችን አገራት የተውጣጡ ሙስሊም ምሁራን ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ኮንፈረንሱን በባለቤትነት ያዘጋጀው የሶማሌ ክልል ሸሪዓ ፍርድ ቤት ነው፡፡የሸሪዓ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ለሬዲዮ ቢላል እንዳስታወቁት እንዲህ አይነት ኮንፈረንስ በክልሉ ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው፡፡

  Read more

Latest Articles

Most Popular