ህዝቡ አኩሪ ጀብዶ መፈፀሙን ቀጥሏል!

አላሁ አክበር!!አላሁ አክበር!!!!
መጅሊስና አሕባሽ ከተንኮል ባይወገዱም
ህዝቡ አኩሪ ጀብዶ መፈፀሙን ቀጥሏል!

በዛሬው ዕለት ሙስሊም የአዲስ አበባ ኢሀዴግ አባላትን ለማነጋገር የኢህአዴግ ፅ/ቤት ከ2,500 በላይ አባላቱን ስብሰባ ጠራ፡፡ ስብሰባው የተካሄደው መገናኛ አካባቢ በሚገኘው ኮኮብ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነበር፡፡ የስብሰባውን ሠዓት በማክበር በቦታው የተገኙት ታዳሚዎች ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከገቡ በኋላ በመድረክ ላይ ጉብ ባሉት ሰዎች ሳይገረሙ አልቀሩም፡፡ በመቀጠልም የመድረክ ሰዎች ራሳቸውን ማስተዋወቃቸው ግድ ነበርና ማንነታቸው ታወቀ፡፡ ከሦስቱ የመድረክ ሰዎች መካከል አንደኛው ከኢህአዴግ ፅ/ቤት አቶ ፀጋዬ ሲሆኑ ሁለቱ ግን መሰሪ አጀንዳ ያነገበው ፅ...ንፈኛ ቡድን አባላት መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡ አንዱ ከመጅሊስ አቡል ሐይ ፈቲ የተባለው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከመርከዝ ነኝ ብሎ አለባብሶ ለማለፍ ሲሞክር ታዳሚው እንዲያብራራው በጠየቀው መሠረት ስሙ ኸድር እንደሚባልና ከመርከዘል አብደላህ አል-ሐረሪ የመጣሁ ነኝ ብሎ አፈነዳው-ከአሕባሽ፡፡

... የመድረኩ መሪ የነበሩት የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ የመድረኩን ዋና የውይት አጀንዳ ወቅታዊ እና አወዛጋቢ የሆነው ጉዳይ ዲሞክራሲችን ላይ ጥላ እጠላበት በመሆኑ ከኛ ከአባላት አንደ ድርጅት ምን ይጠበቅብናል? በማለት ካብራሩ በኋላ እኛ አንደ መንግስት በዚህ ጉዳይ ውስጥ የገባነው ፈልገን ሳይሆን መጅሊሱ ስለጋበዘን ነው፡፡ በመሆኑም ለምን እናን እንደጋበዙን እንዲያብራሩልን መድረኩን ለነሱ ክፍት ላድርግላቸው በማለት እድሉን ለሁለቱ ሰዎች ክፍት አደረጉ፡፡

ሁኔታው ግልፅ የሆነላቸው በዕለቱ የተገኙ ተሳታፊዎች የተቃውሞ ድምፃቸውን በአንድ ላይ ለማሠማት ደቂቃ አልፈጀባቸውም፡፡ እርሶን እናውቆታለን (አቶ ፀጋዬን ማለታቸው ነው፡፡)፤ይህ የድርጅት ስብሰባ እንጂ የመጅሊስ ስብሰባ አይደለም፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ መጅሊስ እኛን ማወያየት ከፈለገ በመስጂድ ይጥራን፡፡ ይህ የድርጅት ስብሰባ ነው፡፡ከርሶ ጋር የተቀመጡት ሰዎች ህጋዊ የሆነ የህዝብ ውክልና የሌላቸው፣ ህዝብ የማያውቃቸውና ሙስሊሙ ህዝብ ይወገዱልኝ በማለት ጥያቄ ያነሰባቸው አካላት ናቸው፡፡ ምንም እንኳን እርሶን ብናከብርም እነኚህ ሰዎች ባሉበት መድረክ ይቅርና እዚህ አዳራሽ ውስጥ በተቀመጡበት ሁኔታ ፈፅሞ ስብሰባውን ማካሄድ አንችልም ይውረዱልን በማለት የበረታ ተቃውሞ አሰሙ፡፡በዚህም ምክንያት ግለሰቦቹ ከመድረክ ተሸማቅቀው ወረዱ፡፡ አላህ ሲያዋርድ እንዲህ ነው፡፡ ከመድረክ ከወረዱ በኋላ አንደኛው በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዘጋጅ የታዳሚው ተቃውሞ አሁንም ቀጠሎ ተክቢራ ማሰማት ጀመሩ፡፡ በአጠቃላይ ከአዳራሹ ይውጡልን በማለት በተክቢራ አቀለጡት፡፡ በዚህ ጊዜ ሰዎቹ የውርደት ማቅ ተከናንበው ጨርቄን ማቄን ሳይሉ በመጀመሪያው ረድፍ ተቀምጠው የነበሩ ጀሌዎቻቸውን አስከትለው ከአዳራሹ ውልቅ አሉ፡፡ አላሁ አክበር!
ይሁንና የስብሰባው ታዳሚ ድርጅታቸውን በማክበር ስብሰባው እንዲቀጥል በፈለጉት መሠረት ከዋናው ሰብሳቢ ጎን ሌላ የኢህአዴግ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሐሰን ጧሂር መድረኩ ላይ ተሰይመው ሲያበቁ ስብሰባው ቀጥሎ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ተካሂዷል፡፡ በአብዛኛው የስብሰባ ታዳሚ እንደተነሳው ህዝቡ እያነሳ ያለው ጥያቄ አግባብነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የመጅሊስ አመራሮች ፍፁም እውቅና የሌላቸውና ህዝቡን የማይወክሉ መሆናቸው ታውቆ ከወረዳ እስከ ፌዴራል ድረስ አስቸኳይ ፍትሀዊ ምርጫ መካሄድ እንደሚኖርበት አሳስቧል፡፡ በማጠቃለያውም የመድረኩ መሪ የሚከተሉትን ነጥቦች ወርውረዋል፡-
• መንግስት ችግሩን በውል እንደተረዳው እና አስቸኳይ መልስ መስጠት እንዳለበት
• መጅሊስ የትምህርት ደረጃ ባላቸው ምሁራን ሊመራ እንደሚገባው
• ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ መቀጠል እንደምንችል
• ለየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት መሣሪያ ከመሆን እንድንቆጠብ
• ጥያቄችንን መባሰማት ሂደት ትዕይንቱ በመስጂዶች አካባቢ ብቻ ቢሆን ተመራጭ እንሚሆንና ሌሎችንንም የማጠቃለያ ሃሳብ በመሰንዘር የውሎ ውይይቱ እኩለ ቀን ላይ በሠላም ተጠናቋል፡፡
ይኸው ስብሰባ ነገ እሁድ በአዲስ አበባ መስተዳድር አዳራሽ በከንቲባው መሪነት ከ 1000 በላይ ተሳታፊዎች በሚገኙበት ቀጥሎ ይውላል፡፡ ሁላችንም እንደተለመደው አወንታዊ ሚናችንን በስብሰባው ላይ ተገኝተን እንወጣ፡፡መልዕክታችን ነው፡፡

ዛሬ ከስብሰባ አዳራሽ መድረክ ተዋርደው እንደወረዱ ሁሉ ነገም ኢንሻአላህ ከሙስሊሙ መንፈሳዊ ተቋም ተዋርደው ይወገዳሉ፡፡by abu dawd
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular