መጅሊስ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የለጠፈው ማስታውቂያ ያለበትን ጭንቀት እንደሚያመላክት ተገለፀ

ጥር 23/2004 የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለአዲስ አበባ ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ከትናንት ጀምሮ እየለጠፈ ያለው ማስታውቂያ ጭንቀቱን እንደሚያመላክት አስተያየት ሰጪዎች ገለጹ፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ ዛሬ ለሬዲዮ ቢላል እንዳስታወቁት መጅሊሱ የለጠፈው ማስታውቂያ ከህብረተሰቡ እየደረሰበት ያለውን ከባድ ጫናና ተቃውሞ ተከትሎ የተፈጠረበትን ውጥረት የሚያስረዳ ነው፡፡ የአወሊያ የጁመዓ አድማ የ1987 አሳዛኝ ስተት ናፋቂዎች ድርጊት እንደሆነ የገለፁበትን ይህን ማስታውቂያ ህብረተሰቡን ይበልጥ እያስቆጣው እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም ህበረተሰቡ ማስታውቂያውን በመገንጠል ተቃውሞውን መግለፅ መጀመሩን አመልክተዋል፡፡ አወሊያ ሊወሰድ ነው አረብኛ ትምህርት ሊዘጋ ነው አህባሾች ከአገራችን እንዲወጡ መንግስትን እንወትወት በማለት እንቅቃሴ የሚያደርጉትን እንዳትቀበሉ የሚል ይዘት ያለው ነው፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular