ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!!

1 The New Package of Conspiracies Being Hatched Against Ethiopian Muslims ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!! እጅግ ሰላማዊ እንቅስቃሴያችን አልሀምዱሊላህ ጥሩ እየሄደልን ይገኛል፡፡ አሁንም ግን እንቅስቃሴያችንን ወደሌላ አቅጣጫ አስይዞ ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ መጅሊስና በፊደራል ጉዳዮች ስር የሚገኘው የደህንነት ክፍል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ በመሆኑም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተጠናክረን ጥያቄያችን ህዝባዊና ሰላማዊ መሆኑን በተጨባጭ ማረጋገጥ ይጠበቅብናል፡፡ ተስፋ የምንቆርጥበት ወቅት ላይ አደለንም! አይጥ ወልዳ ወልዳ ጅራቷ ሲቀር ሲጥ የሚለው ተረት እ...ኛ ላይ እውን እንዳይሆን ተጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ከአስተማማኝ ምንጮች በተገኘ መረጃ መሰረት የደህንነት ክፍሉ (በፌደራል ጉዳዮች ስር ያለው) የሚከተሉትን እቅዶች በመተግበር ትግላችንን ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ አስቧል፡፡ አንዳንዶቹ ታምኖባቸው መተግበር የጀመሩ ሲሆን ቀሪዎቹ ገና ያልተወሰነባቸው ናቸው፡- 1. በተቻላቸው መጠን ተጻራሪ ቡድን (ተቃራኒ ቡድን) መፍጠር ይፈልጋሉ፡፡ ሽኩቻው በህዝብና በህገወጦቹ የመጅሊስ አመራር አባላት መካከል መሆኑ ቀርቶ በሁለት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች መካከል እንዲሆን ይፈልጋሉ - በሱፊያና በወሀብያ፡፡ የአወሊያውን ተቃውሞ የሚቃረንና የሚያወግዝ ሌላ ተቃዋሚ ሃይል እንዲኖርም ይፈልጋሉ፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በመስጊድ ኢማሞች በኩል ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበረ መሆኑን ሰሞኑን ሲያዘጋጁ በነበሩት ስብሰባዎች መረዳት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ሸክ ሰይድ የበኒው ለሚቀጥለው ሳምንት ንግግር በድጋሚ እንዲያደርጉ የታሰበ ሲሆን በሙሉ ፍቃደኝነት ሰውየውም ተስማምተው ‹ይቃወሙኛል፤ ተቃውሞ ያስነሱብኛል› ያሉዋቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ሰጥተዋል፡፡ ፖሊስና ደህንነትም ተዘጋጅቶላቸዋል - የኢህአዴግ ጥበቃ ሲራጥን የሚያሻግራቸው ይመስል! ይህንኑ ሱፊያ ወሀቢያ ጸብ ለመፍጠር ካሰቡት ዋነኛ ነገር አንዱ መውሊድን አጀንዳ ማድረግ ነው፡፡ መውሊድን በአዲስ መልኩ በሁለት ከተሞች ድል አድርገው ለማክበር አስበዋል፡፡ መጅሊስ ይህንን እንዲያስፈጽምም ስራ ተሰጥቶታል፡፡ አንደኛው መውሊድ የሚከበረው ኦሮሚያ ክልል ደራ ላይ ሲሆን በቱሎቪዥን ከፍተኛ ሽፋን ይሰጠዋል፡፡ የመስጊድ ኢማሞችና ሸኮች አንድ ሳይቀሩ እዚያ የሚሄዱ ሲሆን አሕባሽ ላይ የተወራው ሁሉ ውሸት መሆኑን የሚያስተምሩ የአህባሽ አባላት ተዘጋጅተዋል፡፡ ይህኛው ፕሮግራም ሲጠናቀቅ ወሎ ከልል ላይም ተመሳሳይ ዝግጅት ሊደረግ ታስቧል፡፡ በዚህም መውሊድን አስታክከው የቀድሞው ጭቅጭቅ እንዲነሳ እየሰሩ ናቸው፡፡ ሰዉን በማሳወቅ ከወዲሁ ሙከራቸውን በአላህ እርዳታ ማክሸፉ ደግሞ ውዱ ነቢይ ከኛ የተቀበሉት በይዓ መቋጠሪያ ነው! ሙስሊሞች ሆይ ንቁ! የነቢዩን ልደት አስታከው አንድነታችንን ሊበትኑ አስበዋል! ታላቁን ነቢይ የሚወድ ሁሉ ሸራቸውን በመመለስ ይተባበር አላሁ አክበር! 2. መጅሊስ ይውረድ የሚለውን ህዝባዊ ጥያቄ የአወሊያ ትምህርት ቤት ጉዳይ አንደሆነ አድርገው አጀንዳ ለማሳጣት የአወሊያን አስተዳደር ለህዝብ ለመመለስ አስበዋል፡፡ በዚህም ጥያቄያችን ተመልሷል የሚሉ ጥቂት ሰዎችን ለማራቅ ያስባሉ፡፡ ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ወተማዎችን (የአወሊያን ወላጅ ተማሪ ማህበር) በማነጋገር ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ወተማን ነጥሎ ከነሱ ወገን በማሰለፍ አጀንዳ ለማሳጫነት ሊጠቀማቸው አስቧል፡፡ እኒህ ሰዎች በእርግጥ ተታለዋል!!! ጥያቄያችን የአወሊያ አይደለም! አወሊያ መፍትሄ ቢሰጠው እሰየው ከአራቱ ጥያቄያችን አንዱ ተመለሰ ከማለት ውጪ ሶስቱን ጥያቄዎቻችንን በፍጹም አንረሳም! አላሁ አከበር! 3. መጅሊሱ ላይ የተፈጠረውን ጥያቄ ለማብረድ የተወሰኑ ሰዎችን ከመጅሊሱ ለማባረር ያስባሉ፡፡ በዚህም ሶስት ሰዎችን (ጀማልን፣ አህመዲን አብዱላሂን፣ አልሙሀመድ ሲራጅን) ለማባረርና እነ አዛምን የመሳሰሉ በህዝብ የማይታወቁ አህባሾችን እዚያው አስቀርተው ጉዳዩን ለማብረድ ይሸሉ! ልብ እንበል! የእኒህ ሰዎች መባረር ጥሩ ዜና ነው፡፡ ጥያቂያችን ግን የምናምንባቸው መሪዎች በነጻ ህዝባዊ ምርጫ ይምጡ እንጂ ጥቂት ሙሰኞች ይባረሩልን አይደለም! ሙስሊሞች ሆይ ንቁ!!! የምርጫው ጥያቄ ገፍቶ የሚመጣ ከሆነ (እኛ ታግሰን ተቃውሞዋችንን ከቀጠልን ማለት ነው) ከአመት በኋላ እንዲደረግ ሊያደርጉና ‹‹ወሃቢያ›› እንዳይገባበት ካሁኑ ሊያመቻቹ አስበዋል፡፡ እነሱ ወሀቢያ የሚሉት ደግሞ የታወቀ ነው - መብቴን ያለ ሁሉ ወሀቢያ ነው እነሱ ዘንድ፡፡ ‹ሶላት ልስገድ፣ ሂጃብ አልከልከል› ያለች ሁሉ ናት ወሀቢያ The New Package of Conspiracies Being Hatched Against Ethiopian Muslims to Abort our Civilized and Peaceful Revolution!!!! 2 በነሱ ዘንድ! ይህንንም እውን ለማድረግ ካሁኑ ሰዎችን በስራቸው እያደራጁ ነው፡፡ በ1992 ‹‹ምርጫም›› ልክ እንዲሁ ነበር ያደረጉት… አስታውሱ!!! 4. የአወሊያው ተቃውሞ አሰሚ ህዝብ ብጥብጥ ውስጥ እንዲገባ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተው አልሳካለት ብሎዋቸው ነበር፡፡ አሁን ግን ለብጥብጥ ለማነሳሳት አንድ መላ መጣልን ሲሉ ተመካክረዋል፡፡ ይሀም ከኮሚቴ አባሎች የተወሰኑትን ሰበብ ፈልጎ እስር ቤት መክተት ነው፡፡ ሊያስከስስ የሚችል ነገር እንዲፈለግባቸው እየተደረገ ነው፡፡ ከዚያ ‹‹ያሰርናቸው በወንጀል ነው፤ ከዚህ ጋር አይገኛኝም፤ ከህግ በላይ የሚሆን የለም› በማለት ለህዝቡ ይነግራሉ፡፡ ህዝቡ ሲቆጣ ይረብሻል ብለው አስበዋል፡፡ ያሳዝናል፡፡ እስካሁን ያልረበሽነው ስላልተቆጣን መስሎዋቸዋል!!! ያሳዝናል!!! ንቁ እንግዲህ! ረብሻ ለመንግስት የፈለገውን እንዲያደርግ፣ የፈለገውን እንዲያስርና እንዲያፍን አረንጓዴ መብራት ይሰጠዋል፡፡ ሰላማዊ ተቃውሞ ብቸኛ ምርጫችን ሆኖ መቆየት አለበት! ይህንን ለሁሉም እናሳውቅ፡፡ ሤራ በባህሪው ብዙ ነገሮችን መቋቋም ይችላል፡፡ መቋቋም የማይችለው መጋለጥን ብቻ ነው፡፡ ሕዝቡ ሴራውን ካወቀው ሊስፈጽሙት አይችሉም፡፡ ስለዚህ እንንቃ! ብልጦች አይደለንም! ብልጣ ብልጦች ግን አያታልሉንም! 5. ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ካሁን በፊት የመጅሊሱን ‹‹ኡለሞች›› እና ሌሎች ‹‹ተቃዋሚ›› ኡለሞችን በአህባሽ ዙሪያ ክርክር እንዲያደርጉ ሰብስቦዋቸው ሂደቱ ተቋርጦ ነበር፡፡ ሚኒስትሩ አሁን መልሶ ያስጀመረው ሲሆን አላማውም ለጉዳዩ የሚዲያ ሽፋን ሰጥቶ ግጭቱ የፊቂህ ኺላፍ እንዲሆን ለማድረግ ነበር፡፡ ጉዳዩን የሱፊያና የወሀቢያ የመዝሃብ ግጭት እንዲመስል በማድረግ ጥያቄውን ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ ነው አላማቸው፡፡ ሁላችንም እንንቃ!!! አህባሽ እና መጅሊስ ከመዝሀብ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም፡፡ ሁለቱም የባእድ አካላት ቅጥረኞች ናቸው!!! ሴራቸውን የማክሸፍ ሃላፊነት አለብን!!! አላሁ አክበር!!! 6. በየክፍለአገራቱ የተለያዩ ደህንነቶች ጋዜጠኛ መስለው እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡ ስለአህባሽ ያለውን ችግር ምንድነው ልንዘግብ ፈልገን ነው እያሉ ጥያቄዎችን በማቅረብና ኢንተርቪ በማድረግ የተቃውሞውን አንቀሳቃሾች ለይተው ለማወቅ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ሙስሊሞች ሆይ እንዳትታለሉ፡፡ ጋዜጠኛ ነኝ ብሎ የመጣ፣ የጋዜጠኛ መታወቂያ የያዘ ሁሉ ጋዜጠኛ አይደለም! ሙስሊሞች ሆይ! ታጋዮቻችሁን አጋልጣችሁ እንዳትሰጡ!!! 7. ክልሎች ላይ ያለው እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል፡፡ የምእራብ አርሲ መጅሊስ የአወሊያውን ኮሚቴ በግልጽ ደግፈው ከህዝብ ጎን በመቆም ፔቲሽን እያስፈረሙ ነው፡፡ በመጅሊሱ ፕሬዝዳንት በአህመዲን አብዱላሂ ሃገር (ሐረር ያለቸው ኮምቦልቻ ከተማ) እንኳን 21ሺ 500 በላይ ሰው ፈርሟል፡፡ ነገር ግን የክልሉ እንቅስቃሴ እስካሁን ከፔቲሽን ስላላለፈ አቃልለው ያዩት ጀምረዋል፡፡ ፔቲሽን በነሱ ቤት የህዝብ ድምፅ አይደለም እንዴ? እናም ተቃውሞው በፔቲሽን ብቻ ከቀጠለ አዲስ አበባ መጅሊስን ብቻ ለቅቀው ለምርጫ ነጻ ለማድረግና የክልሉን በዚያው በፌዴራሉ ለመቀጠል አስበዋል፡፡ አላሁ አክበር! የከልል ወንድሞቻችን ንቁ! ሰላማዊ የፔቲሽን ትግላችሁ ወደሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ካልተቀየረ ዋጋ የለውም!!! ምነው! አወሊያ ብቻ ነው እንዴ የተቃውሞ ቦታ!!! እነዚህ በሙሉ ስራ ላይ ውለዋል ማለት አይደለም፡፡ ገና ያልተወሰነባቸውና በጭቅጭቅ ላይ ያሉ ነጥቦች አሉ፡፡ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ውስጥ በዚህ ሳምንት ከፍተኛ ክርክር ሲደረግበት ነበር፡፡ ብዙዎቹ ‹‹ይበቃናል፤ እዚህ ጉድ ውስጥ እያታለለ የከተተን ጦሰኛው መጅሊስ ስለሆነ መፍትሄው ስልጣኑን ለህዝበ ሙስሊሙ መመለስ ነው›› በሚል ቢከራከሩም ፌደራል ጉዳዮችና በስሩ ያሉት የደህንነት ክፍሎች ግን በግትርነታቸው ቀጥለው እስከመጨረሻው እንሞክር እያሉ ነው፡፡ ስምምነት ላይ ስላልተደረሰ ለሚቀጥለው ሳምንት ገና ተቀጣጥረዋል፡፡ ስራ ላይ እየዋሉ ያሉ በመኖራቸው ሁሉንም ለህዝቡ በማሳወቅና በተጠንቀቅ በመጠበቅ ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ ሴራ ቢሸረብም ሁልጊዜም ተስፋ መቁረጥ የለብንም፡፡ አላህ ምንጊዜም ከጎናችን ነው፡፡ ይኸው ዛሬ እንኩዋን ኢህአዴግ ሙስሊም አባላቶቹን ጠርቶ ያደረገው ስብሰባ እንዴት እንደተደመደመ አታዩም? በአላህ ተማምነን ሰላማዊ ትግላችንን ከቀጠልን ፍሬ ማፍራታችን የማይቀር ነው! አላሁ አክበር! ይህንን መልእክት ለሁሉም ማሳወቅ ግዴታችን ነውና ሙስሊሞች ተበራቱ፡፡ አላህ ‹‹ወበሺሪል ሙእሚኒን›› ያለበት ድል ሩቅ አይደለም! አላሁ አክበር ሚን ኩሊ ከቢር! ወመከሩ ወመከረላሁ ወላሁ ኸይሩል ማኪሪን!!! ድምፃችን ይሰማ!!! Source: Face Book
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular