በምስራቅ ሀረርጌ ላፕቶፕ የተጠቀሙ ዓሊሞች መታሰራቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 7/2004 በምስራቅ ሀረርጌ ኮምቦልቻ ወረዳ ላፕቶፕ የሚጠቀሙና ኪታቦችን እና ልዩ ልዩ ኢስላማዊ መፅሀፍቶችን በመኖሪያ ቤታቸው ያስቀመጡ ዓሊሞች በሽብርተኝነት ተጠርጥረው መታሰራቸው ተገለፀ፡፡ መፅሐፎቹ እየጠፉ በመቸገራቸው እና መረጃዎችን በተሻለ መንገድ ማስቀመጥ እንዳለባቸው በማመናቸው ላፕቶፖችን ገዝተው መረጃዎችን ማስቀመጣቸውን የገለፁት ዑለማዎቹ ስለተጠረጠሩበት የሽብርተኝነት ወንጀል ምንም አይነት ተሳትፎ እንደሌላቸው ነው የገለፁት በስፍራው የሚገኘው የፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ላፕቶፕ መጠቀም አያስፈልጋቸውም በመፅሐፍ በመፅሀፍ ተጠቀሙ እንዳሏቸው ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው የሚገኙ መፅሀፍ እና ላፕቶፕ በሙሉ እንደተወሰደባቸውም አመልክተዋል በከባድ ዛቻና ማስጠንቀቂያ እንደተለቀቁም አስረድተዋል፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular