በአሜሪካ ታላቅ የአንድነት የሰደቃና የዱዓ ፕሮግራም ሊያከናውኑ መሆኑ ታውቀ ,ፕሮግራምን ለመዘገብ አልጀዚራ ቢቢሲ ሲኤንኤን ቪኦኤ ዶቼ ዌሌ ይገኛሉ

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን ሙስሊሞች መጪው ቅዳሜ ጁላይ 28 በዋሺንግተን ታላቅ የአንድነት የሰደቃና የዱዓ ፕሮግራም ሊያከናውኑ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይኸው በአሜሪካ የሚገኙ በርካታ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ማህበራት በጋራ ያዘጋጁት ፕሮግራምን ለመዘገብ አልጀዚራ ቢቢሲ ሲኤንኤን ቪኦኤ ዶቼ ዌሌና ሌሎችም ዐለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን በኢትዮጲያ ሙስሊሞች ላይ መንግስት እያደረሰ ያለውን ግፍና በደል ለዐለም ህብረተሰብ የማሳወቅ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መንግስት የሙስሊሙን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ኮሚቴዎቻችንንና ሌሎችም በርካታ ንጹሐን ዜጎችን ለእስር መዳረጉን በማውገዝ በመጪው ሳምንት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ውሳኔ ያደረጉ ሲሆን በዚሁ ፕሮግራም ላይም ቀኑ በትክክል መቼ እንደሚሆን 
ይወሰናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አላሁ አክበር!
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular