በኢትዮጵያ በኃይማኖት ዘላቂነት ያለው ሰላምና መቻቻል ማረጋገጥ እንደሚገባ በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ የተካሄው ኢስላማዊ ኮንፈረንስ ጉባኤ ተሳታፊዎች አመለከቱ ፡፡

የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ላለፉት ሦስት ቀናት ሰላም የሕይዎት ቁልፍ አካል ነው በሚል ርዕስ ያካሄዱትን ኮንፈረንስ ትናንት ማምሻውን ሲያጠናቅቁ ባወጡት የጋራ መግለጫ ነው ይህን ያሉት፡፡ በኃይማኖት መካከል የመቻቻል ባህልን ማዳበርና ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮችን በመለየት በህግ ማዕቀፍ ክልከላ ማድረግ እንደሚገባም ተሳታፊዎቹ አመልክተዋል፡፡ በኮንፈረንሱ ላይ ከአውስትራሊያ፣ እንግሊዝ ፣ ቱርክ፣ ኢዶኖዢ ፣ ደቡብ አፍሪካና ከሌሎች 50 የዓለማችን አገራት የተውጣጡ ሙስሊም ምሁራን ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ኮንፈረንሱን በባለቤትነት ያዘጋጀው የሶማሌ ክልል ሸሪዓ ፍርድ ቤት ነው፡፡የሸሪዓ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ለሬዲዮ ቢላል እንዳስታወቁት እንዲህ አይነት ኮንፈረንስ በክልሉ ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው፡፡

Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular