የመሻኢኾቻችን … በሚዲያ ክፍል -አንድ

የመሻኢኾቻችን … በሚዲያ
ክፍል -አንድ
እጅግ አዛኝና ሩህሩህ በሀነው በአላህ ስም 
አላህ ቀጥተኛውን መንግድ እንዲመራኝና የዓለምን ሀዝቦች በሙሉ ወደ ቀጥተኛው መንግድ እንዲመራቸው ምኞቴም ዱዓዮም ነው፡፡
ከዚህ በታች የታላቁ አንዋር መስጅድ ዒማም ሸይኽ ጡሃ ሙሐመድ ባለፈው ረቡዕ ማታ በፋና ብሮድካስቲንግ ፌብሩዋሪ 15 ቀን ማታ አህባሽ ማነው ታሪኩስ ተብለው የተጠየቁትን ጥያቄ ሲመልሱ የመለሱት መልስ ነው፡፡በዚህ መልስ የታዘብኩዋቸውን ግጭቶችና አደገኛ መልዕክቶች እንደሚከተለው በአላህ ፈቃደ በጥያቄ መልክ አቀርባለሁ፡፡ሆኖም ግን በምንም ሁኔታ መሻኢሆችቻንና ኡለማኦችን ልወርፋቸውም ሆነ ላጣጥላቸው እንዲሁም ክብቸውን ትቂትም መንካት አልፈልግም፡፡አላህን የምለምነው ኡለማኦቻችንን ቀስፎ የያዛቸው የፍርሃትና የዱኒያ አባዜ ተገፎላቸው ላኢላሃኢለላህ ባሉበት አንደበታቸው ስለ ጊዜያዊ ትሩፋታቸው እንዳይዘምሩ ነው፡፡ ለማንኛውም የሸህ ጡሀ ቃል እንሆ…
ሸህ ጡሃ
"ኢትዮጵያ በውጭ ሀገር ከድሮ ጀምሮ ሀበሻ በሚል ትታወቃለች፡፡የህ ስም አስካሁንም አለ፡፡አንድ ሃበሻ የሚባለውን ወደ ብዙ ስም ለመለወጥ አህባሽ ይባላል፡፡በነቢ ዘመን አለይሂ ሶለዋቱሏሂ ወሠላም ታዋቂ እና ለማሞገስ ሲፈለግ በሀበሻ ብቻ ነው የሚወሠነው፡፡አህባሽ የሚለው ግን አሉታዊ መልዕክት ያለው ስያሜ ነው፡፡ በዛ በዘመናቸው በሲራ እንደምናገኘው፡፡በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ሙሐድሡ ሸይኽ አብዱላሂ አልሃረሪ ከኢትዮጵያ ወደ ስዑዲ ሄደው፡፡ስዑድም ከኡለማኦች ጋር በዓቂዳ ምክንያት ሳይስማሙ ሲቀሩ ወደ ሶሪያና ሉብናን ሄደዋል፡፡በወቅቱ የነበሩት ታላላቅ ዑለማዎች አቀባበል አድርገውላቸው በተለይ ብዙም ተለይቷቸው የማያውቅ ዶ/ር ኒዘር አልሀለቢ አናውቃቸዋለን ታሪኻቸውን፡፡እዛ ሲኖሩ ነበረ ከዛም በዓቂዳ ላይ ያተኮረ ዒልም ማስፋፋት ይጀምራሉ፡፡እዛ በቡድን አደራጁ ብዙ ዑለማኦችን በተለይ ጃሚኢየቱል አዝሃር በዓለም ላይ ልዩ እውቅና ያለው የካይሮ ዩኒቨርሲቲ የወጡ ዑለማዎች ተጠጓቸው፤በቂ እውቀት እያላቸው፡፡ ከዚያም እዛ ብዙ መስመሮችን ዘረጉ፤ ህዝቡም ዑለማው፣የሶሪያ ዑለማ ጭምር አቀባበል አድርገውላቸው ቦታ ይዘው ተመከኑ፡፡ከዛ እንግዲህ ስዑዲ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ እንካስላንቲያ በፅሁፍም ከሥዑድ ዑለማዎች ጋር ብዙ (ፍጅት) ተፈጥሯል፡፡መጀመሪያ ዑለማኦቹ የስዑድ ኡለማዖች በጉልበት አወጧቸው ከሀገራቸው፡፡በኋላም መፅሀፍ ፃፉባቸው፡፡እሳቸውም እነኚህን የፃፉባቸውን ሰዎች ሁሉ በዝርዝር አጠፌታውን ብዙ ፅሁፎች መልሰዋል፡፡እዛ ላይ እንግዲህ ወሀቢያም የጠነከረበት ዘመን ነበር ያጊዜ የዛሬ 40 ዓመት በፊት ነው፡፡(በአካባቢው) የጠነከረ ነበረ፡፡ ብዙ ፅሁፎች የከረሩ ፅሁፎችን ተለዋውጠዋል ከዚያም ሶሪያ ውስጥ፣ሉብናን ውስጥም ሲደራጁ እንግዲህ እሳቸው(አል-ሀረሪ) ብዙ ደረሶችን አፈሩ፡፡ደረሶቹ ደግሞ በዚህ በሱፍያና በውሃብያ ጋር ግንኙነት የሌለው የጠራ አቂዳ ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን ማስፋፋት ጀመሩ፡፡እዛ ላይ እንግዲህ በጥላቻ ሱዕዳውያን አህባሽ የምትለውን ሥም ለጥፈውባቸዋል፡፡ነገሩ ስሙ ሀበሻ መሆናቸውን የሚገልፅ ነው እንጅ ሌላ ነገር አይደለም፡፡ወላኪን እሳቸውንና እሳቸውን ያጀቡ ሁሉ፣እንደገና የእርሳቸው ደረሳ የሆኑትን ሁሉ አህባሽ በማለት በተለያዩ መፅሀፎቻቸው ትችት አድርገውታል፡፡ በኔትዎርክ በተለያዩ ነገሮች "እኛም ብዙ ጊዜ እናነባለን" ዘርግተዋል፡፡እንግዲህ አህባሽ ማለት ስያሜው ከወዳጅ የመጣ ሳይሆን ከ…ተፃራሪ ክፍል የተለጠፈባቸው ስያሜ ነው፡፡"
በንግግራቸው ውስጥ የተስተዋሉ ግጭቶች
1.አህባሽ የሚለው ቃል በነቢዩ (ሡዐወ) ዘመን አሉታዊ መልዕክት ያለው ስያሜ መሆኑን መጀመሪያ ከነገሩን በኋላ ኃላ ላይ የስዑዲ ዑለማኦች በጥላቻ ስሜት ይህን ስም እንደለጠፉባቸው ጠቁመው ስሙ ሀበሻ መሆናቸውን የሚገልፅ ነው እንጅ ሌላ ነገር አይደለም ይሉናል፡፡ምን ማለት ነው ሁለት ተቃራኒ ነገሮች በአንድ ቅፅበት ውስጥ ትክክል ሊሆኑ አይችሉም፡፡አንድ በረሱሉ ዘመን የነበሩ ሰዎች አህባሽ የሚለውን ቃል ለአሉታዊ መልዕክት መጠቀማቸው ስህተት ነበር እያሉን ነው ወይም የወቅቱን የአህባሽን አስተሳሰብ ተቀብለዋል ማለት ነው፡፡በመጨረሻም ስያሜው ከተፃራሪ እንጅ ከወዳጅ የመጣ አለመሆኑን በመግለፅ ሃሳባቸውን ሲቋጩ ከባላንጣ የተሰየመ ስያሜ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ወይም በአሉታዊ የሚታይ ነው የሚል ስሜት ያስይዛል፡፡
ሸህ ጡሃ የሚከተሉት መዝሃብ ምንድን ነው?
ሸይኽ ጡሃ የአህባሾችን አስተምህሮ ከሱፍይም ከውሃብይም ጋር ግንኙነት የሌለው የጠራ አቂዳ ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን እንደሚያስተምሩ ነግረውናል፡፡ሸይሁ በዚህ አባባላቸው የሚከተሉትን ጭብጦች አስይዘውናል፡፡
የአህባሽና የሱፍይ አስተምህሮ የማይገናኝ ትምህርት መሆኑን አስረግጠው ነግረውናል፡፡ታዲያ አህባሽ ሱፍይን የማይቀበል መሆኑን ከተረዱ እርሳቸው የደገፉት ምን ስለሆኑ ነው? ውሃ ብያ እንዳንል ውሃብያ ብለው የፈረጁትን ክፍል ክፍኛ ሲያብጠለጥሉት ተደምጠዋል፡፡
የአህባሽን አስተምህሮ "የጠራ" ሲሉ ገልፀውታል፡፡ይህን ቃል ከሰነዘሩበት አግባብ (contextual meaning) አንፃር ሲገመገም አያይዘው የተጠሩት የሡፍይ እና የውሃብያ አመለካከቶቸ የጠሩ አይደሉም የሚል ትርጉም ይሠጠናል፡፡ታዲያ ሸይህ ጡሃ የትኛውን ክፍል ወግነው ይሆን ይህን የሚነግሩን?
ጥያቄ የሚያጭሩ ሃሳቦች
1.ከስዑዲ ኡለማኦች ጋር ያጋጫቸው ሃሳብ ምንድን ነበር?
2. ለሳዑዲ ዑለማዎች በዝርዝር ለሁሉም የተሰጠው አፀፋዊ መልስ ሸይህ ጡሀ ካላቸው ዲናዊ እውቀት አንፃር እንዴት ያዩታል፡፡ምን አልባት ሸይኽ አብዱሏሒ በየመፅሀፎቻቸው እከሌ ካፊር እከሌ ካፊር እያሉ የፃፉትን እያሉን ከሆነ ይህ በኢስላም ይፈቀዳል ማለትዎ ነው? የገለፁበትም ስሜት ግለሰቡ ባደረጉት አፀፋዊ መልስ መርካትዎትን በሚያሳብቅ መልኩ ነበርና እርሰዎም ማክፈሩን ይጋሩታል ማለት ነው?
3.የዑለማዕ ክብርና ደረጃ ምን ያክል ነው? እሽኮለሌ የሚገጥሙ? በጉልበት የሚጠቀሙ?
የሳኡዲ ኡለማኦች ምን ያክል ለህዝቦቻቸው እንደሚጨነቁ እየነገሩን ይመስለኛል ምክንያቱም ለህዝባቸው የማይመጥን ካላቸው ነባራዊ ሁኔታና ለዲኑ ቅርበት አንፃር በወቅቱ መፍትሔ ሲሰጡ እናንተስ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምንያክል ታስቡለታላችሁ?ምናልባት እናስብልሃለን እናውቅልሃለን የሚጠቅምህ ይህ ነው እያሉት ከሆነ የእርሰዎ ጎራስ ከየትኛው ነው?
ወገንተኝነት 
1. አበዱላሂ አል-ሀረሪ ስዑዲ ከሄዱ በኋላ ከሳዑዲ አረቢያ ዑለማኦች ጋር በአቂዳ አለመስማማታቸውንና ሳዑዲያውያኑ ሸይሁን በጉልበት ከማስወጣታቸውም በተጨማሪ ሸይሁን በህትመት ውጤቶችና በተለያዩ ሚዲያዎች እንካስላንቲያ እንደፃፉባቸው ሲገልፁ የተጠቀሙት አገላለፅ በሸይህ አብዱሏሂ አልሀረሪ ሳዑዲያውያኑ ያደረሱባቸውን በደልና መከራ ለህዝቡ ማሳወቅን ነው፡፡ታዲያ ይህ አቀራረብ አድሎአዊ አይደለም ብለው ያስባሉ? በእርግጠኝነት አድሎአዊ ነው ምክንያቱም መልዕክቱን ታዳሚው ማህበረሰብ የግጭት መንስኤ የሆነውን አቂደ ማሳወቅ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ሸይሁስ በአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ህዝቦች ላይ ለመጫን ያሰቡት አስተሳሰብ ወይም የግጭቱ መንስኤ የሆነው መገለፅ አልነበረበትም?
2. ሸይኹን ለማድነቅ ለማሞገስና ለማግዘፍ የሚከተሉትን ዘይቤዎች ተጠቅመዋል ይህ ወዴት ያመራል፡፡
ሙሐዲሱ
ታላላቅ ዑለማዎች፣ህዝቦችና የሶሪያ ዑለማዎች ሳይቀሩ የተቀበሏቸው መሆኑን
የአዝሀር ዩኒቨርሲቲ ምሁሮች እንኳን የተቀበሏቸውና የተጠጓቸው መሆኑን
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular