የአዲስ አበባ ከንቲባ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ ጋር ዉይይት ለማድረግ

በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ ቲያትር እና ባህል አዳራሽ የአዲስ አበባ ከንቲባ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ ጋር ዉይይት ለማድረግ ፕሮግራም ይዘዉ ነበር::ከመንግስት በኩል ጥሪ የተደረገዉ ከየክ/ከተማዉ አስር አስር ሰዎች ብቻ ሲሆን ሙስሊሙ ግን ጉዳዩ የሁላችንም ነዉ በማለት በጠዎቱ ወደ ስብሰባ አዳራሽ ጉዞዉን ተያያዘዉ::ከጠዎቱ 3:00 ሰአት ላይ አዳራሹን ህዝበ ሙስሊሙ ጢም አደረገዉ::የከተማዉ ከንቲባን ህዝቡ በጉጉት እየጠበቀ ባለበት ሰአት አንድ የአህባሽ ቅጥረኛ መሆኑ ህዝቡ የሚያዉቀዉ ወደ አዳራሹ ዘዉ ብሎ ገባ በአዳራሹ የሚገኘዉ ህዝብ ሰዉየዉን እንደተመለከቱት ከአዳራሹ ለማስወጣት ደቂቃ አልፈጀባቸዉም ህዝቡ ከመቀመጫዉ በመነሳት በተክቢራ አዳራሹን አናወጠዉ ሰዉየዉም እጅግ በጣም ከመደንገጡ የተነሳ አይኑ ፈጠጠ ህዝቡ ዉጣ!!ዉጣ!!ሸይጣን!!በማለት ከአዳራሹ እንዲወጣ ጮሁበት ሰዉየዉም በገባበት በር ዉልቅ ብሎ ወጣ የህዝቡ አንድነት በጣም የሚገርም ነበር አብዛኛዉ ህዝብ በሸሚዙ ኪስ ላይ መጅሊስ አይወክለኝም የሚል መፈክር ለጥፈዉ ነበር ሰአቱ መንጎዱን አላቆመም የሚጠበቁት ክቡር ከንቲባ በሰአቱ አልተገኙም ሙስሊሙ ግን በትግስት እየጠበቃቸዉ ነዉ ወደ አዳራሹ አንድ የመጅሊስ ተላላኪ ወደ አዳራሹ ዘዉ ብሎ ገባ ለሁለተኛ ጊዜ አዳራሹ በተክቢራ ተናወጠ ሰዉየዉን አንጠልጥለዉ ከአዳራሹ አስወጡት ከዚህ ቡሀላ የስብሰባዉ መካሄድ አጠራጣሪ ሆነ::አዳራሹ መያዝ ከሚችለዉ በላይ በህዝበ ሙስሊሙ በመሞላቱ የመዘጋጃ ቤት ፓሊሶች ወደ አዳራሹ እየመጣ ያለዉን ህዝብ በበሩ ላይ እንዲቆም አደረጉት በዉጪ በር ላይ እንዲቆ ምየተደረገዉ ህዝብ በአዳራሹ ከተገኘዉ ህዝብ በጠም የበለጠ ነበር::ህዝቡ እንገባለን ፓሊስ ደግሞ አዳራሹ ሞልቷል በማለት ሙግቱ ቀጠለ::በዚ ሰአት ከአዳራሹ የተወሰኑ ሰዎች በመዉጣት በዉጪ ያሉትን ሰዎች ለማረጋጋት ሞከሩ::ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ወደ አዳራሹ የመንግስት ተወካዬች እየመጡ ነዉ ስለተባለ አዳራሹ በፀጥታ ተዎጠ::ወድያዉኑ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋዬ ሀ/ማርያም ወደ አዳራሹ ዘለቁ::ወደ አዳራሹ መድረክ ላይም ወተዉ በመድረክ መሪዉ ወንበር ላይ ወተዉ ተሰየሙ በአይናቸዉ አዳራሹን::ያጥለቀለቀዉን ህዝብ በአይናቸዉ ከቃኙ ቡሀላ ለህዝቡ ሰላምታቸዉን አቀረቡ:: በሞባይላቸዉ እየቀረፁ የነበሩትን ሰዎች እንዲያቆሙ ከጠየቁ ቡሀላ ድጋሚ ሰላምታ ሲያቀርቡ ሁሉም በአንድነት አልሀምዱሊላህ በማለት መለሰላቸዉ:: በመቀጠልም ጥሪያችንን አክብራችሁ የጠራናችሁም ያልጠራናችሁም ስለመጣችሁ እናመሰግናለን አሉ:: ቀጥለዉም ከግቢዉ ዉጪ በጣም ብዙ ሰዉ ስላለ እነሱ ስብሰባዉን መካፈል ስላለባቸዉና አዳራሹ ይህንን ሁላ ህዝብ ማስተናገድ ስለማይችል በሌላ ጊዜ ሰፋ ያለ አዳራሽ ይዘን እንወያያለን በማለት የዛሬዉ ስብሰባ መሰረዙን እና ለሌላ ጊዜ መዘዎወሩን ለህዝቡ አበሰሩት::ከዛም ወድያዉኑ አዳራሹን ለቀዉ ወጡ::ህዝበ ሙስሊሙ እንደተለመደዉ የመጨረሻ ተክቢራ በማሰማት ኢስላማዊ አደብ በጠበቀ መልኩ አዳራሹን በሰላም ለቀዉ ወተዎል:: አልሀምዱሊላህ ሙስሊም ላደረገን ጌታ!!!!by abu dawd
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular