የኢህአዴግ አመራሮችና አባላት ለሚከተሉት እምነት እላፊ ድጋፍ የሚሰጡበት ሁኔታ መኖሩ ተገለፀ

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 8/2004 የኢህአዴግ አመራሮችና አባላት በሚከተሉት እምነት በመንግስት በህዝብ በተሰጣቸው ኃላፊነት መካከል የሚወራውን ድንበር በማለፍ እላፊ ድጋፍ የሚሰጡበት ሁኔታ መኖሩን አንድ ሰነድ አመለከተ፡፡ በሰላምና በህገ መንግስቱ ዙሪያ ሀገራዊ መግባባት መፍጠር የዜጎችና የመንግስት መብትን ግዴታም ነው በሚል ርዕስ በቅርቡ በኢህዴግ ፅ/ቤት የወጣው ሰነድ እንዳመለከተው የድርጅቱ አመራሮችና አባላት በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ለሚከተሉት እምነት እላፊ ድጋፍ ሲሰጡ የሚታዩበት ሁኔታ በርካታ ነው፡፡ እንደ ማሳያም በአንዳንድ አዓላት ሀገሪቱን የኃይማኖቶች መቻቻልና መከባበር ሳይሆን የፉክክርና የፍጥጫ ማዕከል እንደሆነች በሚያስመስል መልኩ ድጋፍ ሲሰጡ ይታያል ነው ያለው ሰነዱ፡፡ የጋራ የሆኑ የመንግስት አደባባዮች፣ቢሮዎች፣የሌላ ኃይማኖት ተከታይ የሆኑ መኖሪያ ቤቶችና አጥሮች ጭምር በአንድነት ምልክቶችና የሌላውን እምነት በሚነካኩ እንዲሁም ህገመንግስቱና የሰንደቅ ዓላማ በሚፃረር መልኩ ሲንፀባረቁ የሚተባበሩበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቅሰዋል፡፡ ሰነዱ በእነዚህ ድርጊቶች ተባባሪ ከሆኑና በመጠኑ የተሸሉት ብሎ የጠቀሳቸው ደግሞ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን ሳያስተካክሉ አጥር ጥግ ቆመው የሚመለከቱትን አመራሮችና አባላትን ነው፡፡ እናም አብሮ ማጥፋትና ሌላው ሲያጠፋ እያዩ እንዳላዩ ማለፍ ስህተት ነው ያለው ይኼው ከኢህአዴግ ጽ/ቤት የወጣው ሰነድ በሁለቱም መንገድ ጥፋቶቹ ከመፈፀም የሚገቱበት ሁኔታ አንደማይኖርም አመልክቷል፡፡ ሙስሊምና ክርስቲየን የሆኑ የኢህዴግ አባላትና አመራሮች ይህን ተከተሉ ያን አትከተሉ የሚባሉበት ሁኔታ እንደሌለም ገልፀዋል፡፡ በዚህ ረገድ ችግሩ የሚስተዋለው ከሚከተሉት እምነት ወይም የእምነት ቡድን (ሴክት) ውስጥ መቻቻልን ህገመንግስቱን የሚሸረሽሩ አዝማሚያዎች ሲንፀባረቁ ከድርጅቱ መርህና ከሀገሪቱ ህገመንግስት መንፈስ አንፃር በጥብቅ ዲሲፕሊን የማይታገሉ መሆናቸው እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ የኢህአዴግ አባል የእምነት ነፃነት አለው ሲባል ፀረ ህገመንግስት አቋሞችን የሚያራምድ ድርጅት ወይም በኃይማኖት ሽፋን በሚያስኬድ እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ አለበት ማለት አለመሆኑን አስረድቷል፡፡ በመሆኑም በኢህዴግ አባላትና አመራሮች አቋማቸውን ሳያስተነትኑ ከሚከተሉት እምነት መሰረታዊ አስተምህሮት ፈንጠር ያሉና ፀረ ህገመንግስታዊ መግለጫ ያላቸው አቋሞችን ተላብሰው ይታያሉ ነው ያለው ሰነዱ፡፡ በዚህም መሰረት አንዳንድ የኢህዴግ አባላትና አመራሮች ኢህዴግነትንም ፀረ-ኢህአዴጋዊ አቋሞች የያዙ ቡድኖችንም የሚያንቀሳቅሱበት ሁኔታ በገሃድ እንደሚታይ ነው ሰነዱ ይፋ ያደረገው፡፡ ስለሆነም ከዚህ አንፃር የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ግልፅነት በመፍጠር የአባላቱንና አመራሮቹን አሰላለፍ ማስተካከል እንደሚገባ ለማስተካከል የሚቸገር ደግሞ ከድርጅቱ መፅዳት እንዳለበት ነው ያመለከተው፡፡ ህገ መንግስቱ በኃይማኖት ዙሪያ ካስቀመጣቸው መርሆሆች በመነሳት በአባሉና አመራሩ ዘንድ የጋራ ግንዛቤ መፍጠርና ትግሉም ይህንኑ መሰረት ሊያደርግ እንደሚገባ ጠቅሷል፡፡ ህገ መንግስቱ ለግለሰብና ለቡድን መብቶች አስተማማኝ ጥበቃ የሰጠውን ያህል መብቶችን ለመተግበር የሚደረጉ እንቅስቃሰሴዎች መከተል የሚገቡ መርሆዎችና ዳር ድንበሮች በዝርዝር እንዳስቀመጠም ጠቅሷል ከኢህአዴግ ፅ/ቤት ለድርጅቱ አመራሮችና አባላት መወያያነት በቅርቡ የወጣው ይህው ሠነድ፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular