ሙስሊሙ ምን ታስቦለት ይሆን?

ሙስሊሙ ምን ታስቦለት ይሆን? በትላንትናው ዕለት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተወካዮቻችንን ከሰዓት በኋላ ከማናገሩ በፊት ከጠዋቱ 5፡30 ጀምሮ ከመጅሊስ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጎ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጦላቸውና ለኮሚቴው የሚሰጠውን መልስም ጭምር አሳውቋቸው እንደነበር ታወቀ፡፡ በሌላ በኩል አቶ ጸጋዬ ቅዳሜ ቀን አቶ አህመዲን ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን መንግስት የሰጣቸውን የቤት ስራ ባግባቡ እንዳልተወጡ ወቀሳ ተሰንዝሮባቸው ለወደፊት እንዲያስተካክሉና መንግስት በአቶ አህመዲን ላይ ከፍተኛ መተማመን እንዳለው ማብራራቱን ከመጅሊስ አካባቢ የተገኙ ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ተጠራርገን መውጣታችን ነው ብለው ስጋት ላይ የነበሩት መጅሊሶች ከመንግስት መተማመኛ ስለተሠጣቸው በደስታ መጅሊስ ጊቢ ውስጥ አርደው መደገሳቸውን እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ እንደዚሁም የመስጂድ ኢማሞቻችን በግድ ስለ አህባሽ እንዲያስተምሩ የተደረገባቸው ጫና አላንስ ብሎ አሁን ደግሞ ሙስሊሙ ጥያቄው ስለተመለሰ ለህዝቡ የእንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልእክት በግድ እንዲያስተላልፉ እየታሰበ መሆኑ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም የአህባሽ ስልጠና በሰፊው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ለየካቲት ወር ብቻ 12 ሚሊየን ብር በጀት ተይዞ በአምቦ በውቅሮ በሻሸመኔና ሌሎችም ቦታዎች እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል የመጪውን ጁሙዓ የአወሊያ ፕሮግራም ለማሰናከል ከሰላት በፊት መድረክ መሪዎችንና የተወሰኑ የኮሚቴው አባላትን ለተወሰነ ሰዓት አግቶ ለመልቀቅ እቅድ የተያዘ በመሆኑ ሁላችንም በንቃት በመከታተል ይህ እኩይ ዐላማ እንዳይሳካ ጥረት ማድረግና ነቅተን መጠበቅ አለብን፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular