በምስራቅ ሀረርጌ የመንግስት አስተዳዳሪዎች የሙስሊሙ ህብረተሰብ አህባሽን እንዲቀበል መገደዱ ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 2/2004 በምስራቅ ሀረርጌ ከሚገኙ 19 ወረዳዎች ውስጥ አንዷ በሆነችው በጭናቅሰን አካባቢ የወረዳው አስተዳዳሪ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የአህባሽን መንገድ መከተል እንዳለበት መግለፃቸው ተጠቆመ፡፡ ውሃቢያን ለመዋጋር ከ19ኙም የምስራቅ ሀረርጌ ወረዳዎች ሦስት ሦስት ሰዎችን በመምረጥ ስልጠና መዘጋጀቱንና ከዞኑ ትህዛዝ መተላለፉን የሬዲዮ ቢላል ምንጭ ከአካባቢው አድርሶናል፡፡ የጭናቅሰን ወረዳ አስተዳዳሪና የወረዳው የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ ህብረተሰቡ ውሃብያና አህሉልተውሂዶችን መዋጋት እንዳለበትና ለምርጫና ለስልጠና ከ19ኙም ወረዳዎች ሦስት ሦስት ሰዎች መዘጋጀት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ የአካባቢው ሙስሊም ህብረተሰብ በበኩሉ መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ መግባት የምንከተለውን ሀይማኖት ሊመርጥልን አይገባም ትክክለኛውን የነብዩ(ሰ.ወ) መንገድ እየተከተልን ነው ማለታቸውን ከአካባቢው ምንጭ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተያያዘ ዜና በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በመዩ ሉቄ ወረዳ 27 ሰዎች ከሰላትና ከስራቸው አንዱን እንዲመርጡ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው ውስጥ በሰላት ምክኒያት ከስራ መታገዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንደ አካባቢው ምንጭ በምስራቅ ሀረርጌ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ እየተፈጠረ ያለው ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular