በአሰሳ በቤት ለቤት አሰሳ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 4/2004 በአርሲ ዞን አሰሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊም የሕብረተሰብ ክፍሎች ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን ለሬዲዮ ቢላል ምንጮች አስታወቁ፡፡ በከተማዋ ቀበሌ 02 ኑር መስጂድ ሚያዚያ 19/2004 የተከሰተውን ሁከትና ግርግር ተከትሎ የፀጥታና ደህንነት ኃይሎች ከሚያዚያ 23 ቀን ጀምሮ የአካባቢውን ሙስሊም ነዋሪዎች ቤት ለቤት በመፈተሸ የቤት እመቤቶችንና አባወራዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ስማችን እንዳይጠቀስና ድምጻችን እንዳይቀረጽ ያሉ የአሳሳ ነዋሪዎች እንዳመለከቱት የፀጥታ ኃይሎች የቤት ለቤት አሰሳውና እስር እያካሄዱ ያሉት ከአልቃኢዳና አሸባሪ ቡድኖች ጋር የግንኙነት መረብ አላቸው በሚል ነው፡፡ከዚህ ባለፈ ግነ መረጃ ለመስጠት ስጋትና ፍርሀት እንዳለባቸው ነው የገለጹት፡፡ ባለፈው አንድ ሳምንት በካሄዱት አሰሳም ከ90 በላይ የሚሆኑ አባወራ ዑለሞች ኡስታዞችና ወጣቶችን ጨምሮ የቤት እመቤቶች በመኪና ተጭነው መወሰዳቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ወደ ሻሸመኔ መስመር ሳይወሰዱ እንዳልቀረ ነው ምንጮች ግምታቸውን የሰጡት፡፡ በሻሸመኔ ከአራት ቀናት በፊት 44 ሴቶችና 50 ወንዶች ከአሳሳ በጸጥታ ሀይሎች ተይዘው መምጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡እነዚሁ 94 አስረኞች በአሁኑ ወቅት በሻሸመኔ ከተማ ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular