በአሰሳ በእስር ከሚገኙት መካከል 100 የሚሆኑት ወዳልታወቀ ስፍራ መዛወራቸው ተነገረ

በአሰሳ በእስር ከሚገኙት መካከል 100 የሚሆኑት ወዳልታወቀ ስፍራ መዛወራቸው ተነገረ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 27/2004 ከሳምንት በፊት በአሰሳ የተፈጠረውን ግርግር ተከትሎ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው 185 የሚሆኑ ሰዎች መካከል የተመረጡ 100 ወጣቶች ወደ ማይታወቅ ስፍራ መዛወራቸውን የአካባቢው ምንጮች አመለከቱ ፡፡ ምንጮቻችን እንዳመለከቱት ከሆነ የተመረጡት ወጣቶች ከአራት ቀናት በፊት ከአሰሳ ማረሚያ ቤት ጨለማን ተገን በማድረግ ወዳልታወቀ ስፍራ በመኪና ተጭነው ተወስደዋል፡፡ ከተወሰዱት ወጣቶች መካከል አንደኛው የሌላ እምነት ተከታይ ስለመሆኑ መታወቂያውን በማሳየት በሰጠው ማረጋገጫ ከተለቀቀ በኋላ ለማወቅ መቻላቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ወጣቱ ባደረሳቸው መረጃ መሰረትም ከአሰሳ ማረሚያ ቤት ተመርጠው የተወሰዱት ወጣቶች የሚገኙበት ስፍራ በግምት ከከተማዋ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ካለ ልዩ ማቆያ ቦታ ሳይሆን እንዳልቀረ አብራርተዋል፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular