በዛሬው የጁመዓ ሠላት በታላቁ አንዋር መስጂድ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ የተባለ የተቃውሞ ድምጽ ተሰማ

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 05/08/04 በተለዩ ክልሎችም የሚኖሩ ምዕመናን ተመሳሳይ የተቃውሞ ድምጽ አሰምተዋል፡፡ ዛሬ ጁመኣ ከወትሮው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን በሰገዱበት በታላቁ አንዋር መስጂድ ከጁመዓ ሰላት መጠናቀቅ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ የተባለ የተቃውሞ ድምፅ ተሰማ፡፡ የመዕመናኑ የተቃውሞ ድምጽ ታላቅ ሊባል የቻለው በአወሊያ ቀደም ሲል የተቀሰቀሰው የህዝበ ሙስሊሙ ቁጣ በአንዋር መስጂድ ሊከሰት የችላል ተብሎ ይጠበቅ የነበረ በመሆኑ ነው፡፡ ከጁመኣ ሰላት ቀደም ብሎም የህዝበ ሙስሊሙን ወቅታዊ መብት ይከበርልን ጥያቄዎች የያዙና ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› የሚሉ በራሪ ወረቀቶች ሲበተኑ እንደነበርም በስፍራው የተገኙ የሬዲዮ ቢላል ዘጋቢዎች ተመልክተዋል፡፡ በተክቢራና በመፈክሮች የደመቀው የታላቁ አንዋር መስጂድ የሕዝበ ሙስሊሙ የተቃውሞ ድምጽ በሰላም መጠናቀቁንም ለማወቅ ተችሎአል፡፡ በተመሳሳይ ዜና በፒያሳው ኑር (በኒን) መስጂድ ቁጥራቸው ከ100 ሺ በላይ የሚሆኑ ምዕመናን የጁመዓ ሰላት መጠናቀቅን ተከትሎ በተክቢራና በተለያዩ መፈክሮች የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡ ለሃያ ደቂቃዎች የዘለቀው ይሄው የተቃውሞ ድምፅ የማሰማት እንቅስቃሴ በዙሪያው በተመደቡ የጸጥታና የደህንነት አካላት በካሜራ ቢቀረጽም ምዕመናኑ በሰላማዊ መንገድ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተው በሰላም ወደየቤታቸው መግባታቸውን ሪፖርተሮቻችን ዘግበዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ በደሴ ፉርቃን መስጅድ ዛሬ በተካሄደው የጁመዓ ሰላት የተገኙ 50 ሺ መዕመናን በተከቢራ የተቃውሞ ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡ በዚህም በሰረት በደሴ መጅሊስ፣ በመድረሳ ትምህርት ቤቶችና መርከዞች እንዲሁም በህዝባዊ ልማት ተቃማት ላይ እየደረሰ ያለው ጫና በአስቸካይ እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡ በሌላ በኩል በሓረርና በአዲስ አበባ አንዳንድ መስጂዶች ዛሬ በተካሄደው የጁመዓ ሰላት በወቅታዊ የህዝበ ሙስሊሙ አጀንዳዎች ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚስችሉ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በዛሬው ጁመዓ ከወትሮው ቁጥሩ በርካታ የሆነ ምዕመናን በየመስጂዶቹ የተገኘ ሲሆን፤ የጁመዓ ሰላት ስግደቱን በሰላም አጠናቆ ወደየቤቱ መግባቱን ለማወቅ ተችላል፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular