ከተባረክ መስጅድ አራት ሰዎች ታሰሩ

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 6/2004 በአዲስ አበባ ሜክሲኮ ጀርመን ግቢ እየተባለ ከሚጠራው መስጂድ ጀመዐ አራት ሰዎች መታሰራቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡ ግለሰቦቹ የታሰሩት ትላንት በስቲያ ምሽት ላይ ነው፡፡የታሰሩበት ምክኒያት ደግሞ ድምፃችን ይሰማ የሚል በራሪ ወረቀት በየመስጂዱ ለመበተን ተንቀሳቅሰዋል የሚል ነው፡፡ ግለሰቦቹ ዛሬ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ህንፃ አካባቢ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ታይቶ ነበር፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular