የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠና ባልጨረሱ ፖሊሶች ተደበደቡ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠና ባልጨረሱ ፖሊሶች ተደበደቡ -በጥይትና በከባድ ድብደባ የተጎዱ ተማሪዎች ህክምና ላይ ናቸው -የከተማው ነዋሪም ተቃውሞውን ተቀላቅሏል ትላንት ለተቃውሞ በወጡ የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ታጣቂዎችበጥይትና በዱላ ጉዳት ማድረሳቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ ከትላንት በስቲያ እሁድሚያዝያ 28 እና ትላንት ሰኞ ሚያዝያ 29 በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ሊከሰትየቻለው ተማሪዎች ተጓደለ ያሉትን የምግብ ጥራት በመቃወማቸው እንደሆነምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ እሁድ ሚያዝያ 28 ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ በተቀጣጠለው በዚህ ተቃውሞ አብዛኛው ተማሪቁጣውን የዩኒቨርስቲውን መስታወቶች በመሰባበር እንደገለፀ የሚናገሩት ምንጮቻችንምሽት ላይ በድንገት ወደ ግቢው የገቡት ታጣቂዎች ተማሪዎቹ ላይ ከመጠን ያለፈኃይል በመጠቀም ጉዳት እንዳደረሱ ገልፀዋል፡፡ በወቅቱ በታጣቂዎች በተወሰደውእርምጃ ከ60 ያላነሱ ተማሪዎች መታሰራቸውና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ላይድብደባ እንደተካሄደ ታውቋል፡፡ በወቅቱ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከፍተኛ የተኩስእሩምታ የተሰማ ሲሆን ኢብራሂም መሀመድ የተባለ የ2ኛ አመት የማኔጅመንት ተማሪ በጥይት መመታቱ ታውቋል፡፡ ተማሪው በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳትበደብረ ማርቆስ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ በመከታተል ላይ እንደሚገኝ ፍኖተ ነፃነት ስፍራው ድረስ በመደወል አረጋግጣለች፡፡ ተማሪ ኢብራሂም መሃመድ በስልክ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፀው ከትላንት በስቲያ ምሽት ታጣቂዎቹ በቀጥታ በጥይት እግሩ ላይ መተውአቁስለውታል፡፡ ሌላው በታጣቂዎች ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመበት የ2ኛ አመት የማኔጅመንት ተማሪ የሆነውና ከትግራይ ክልል የመጣው ገብረ ኪዳንብርሃኔ ትላንት ጠዋት በጀርባውና በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ለዝግጅት ክፍሉ ተናግሯል፡፡ በትላንትናው እለት ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ‹‹የታሰሩ ተማሪዎች ይፈቱ›› የሚል ጥያቄን ይዞ የቀጠለው ተቃውሞ ቀስ በቀስ ከዩኒቨርሲቲው ውጪመስፋፋቱን ከከተማው ያገኘናቸው መረጃዎች አመላክተዋል፡፡ ተቃውሞው በደብረ ማርቆስ ከተማ ጎዳናዎች ላይ በቀጠለበት ወቅት በርካታ የከተማውነዋሪዎችም ትዕይንቱን ተቀላቅለው ጥያቄው ፖለቲካዊ ይዘት ተላብሶ ገዢውን ፓርቲ በማውገዝ እና ለኑሮ ውድነቱ ገዢውን ፓርቲ መኮነናቸውንምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ታጣቂቆች ቶክስ በመክፈታቸው ተቃውሞው ተበትኗል ሲሉ ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ በሁኔታውየተደናገጡት ተማሪዎች ወደ ተለያየ አቅጣጫ ሲበታተኑ ታጣቂዎችና ፖሊሶች አብዛኞቹን እያፈሱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዳጓጓዟቸው የከተማው ነዋሪዎችለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ወደ ህትመት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ አፈሳው እንደቀጠለ ተናግረዋል፡፡ ጨምረውም በድብደባዉከተጎዱ ተማሪዎች መካከል አይናቸዉ ተመትቶ ኡፕራሲዮን የተደረጉ እንደሚገኙበት አስረድተዋል፡፡ ከስፍራው የደረስን መረጃ እንደሚያመለክተውበተማሪዎቹ ላይ እርምጃ የተወሰደው ስልጠናቸውን ባልጨረሱ ፖሊሶች ጭምር መሆኑን ያመለክታል፡፡ ማምሻውን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተውአሁንም በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ዩኒቨርሲቲውና ወደ ደብረማርቆስ ሆስፒታል ደውለን ምላሽወደ ህትመት እስከገባንበት ሰአት ድረስ ምላሽ ማግኘትአልቻልንም፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular