የጎንደር ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ከሚያዚያ 08/2004 ጀምሮ የምግብ ማቆም አድማ እንደሚያደረጉ ተገለጸ

የጎንደር ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ከሚያዚያ 08/2004 ጀምሮ የምግብ ማቆም አድማ እንደሚያደረጉ ተገለጸ፡፡ምክንያቱንም ሲናገሩ መጋቢት 19/2004 ዓ.ም በጂሲ ካምፓስ በቁርዓን ሽንት ቤት ተጠቅሞ ሲጸዳዳ እጅ ከፍንጅ የተያዘው የዩኒቨርሲቲው ባለደረባ ከእስር መለቀቅን ተከትሎ የሚደረግ ነው ማለታቸውን የዜና ምንጫችን ከጎንደር አስታውቋል፡፡የምግብ ማቆም አድማው እስከመቸ እንደሚቆይ የታወቀ ነገር የለም፡፡ዝርዝሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ኡኡ የመንግስት ያለህ…… ኡኡ የፍትህ ያለህ….. የጎንደር የአራቱ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊምተማሪዎች ድምጽ ይሰማ…… ኡኡ የፍትህ ያለህ…..ኡኡኡ ለዜናየ መነሻ እንዲሆነኝ አንድ ነገር ልጥቀስ፡፡በአውሮፓዊቷ ሀገር ዴንማርክ አንድ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ነብዩ ሙሀመድን(ሰ.ዓ.ወ)በካር ቶን ስዕል በመሳሉ በተነሳው ችግር ሀገሪቱ በየወሩ 7.3 ቢሊዮን ዩሮ ኪሳራ ይደርስባት እንደነበርና ሰውየው ለፍርድ ቀርቦ የቅጣት ውሳኔ ካገኘ በኋላ እንደድሮው ባይሆንም ለአመታት ገቢዋ እንደቀነሰ የቅርብ ትዝታ ነው፡፡ሁሉም ሙስሊም ሀገራት ከዴንማርክ የሚገዙትን ሸቀጣሸቀጥ በማቆማቸው ነበር ይህ ሁሉ ኪሳራ የደረሰባት፡፡ወደ ርዕሴ ልመለስ፡፡ አርብ የካቲት 22/2004 በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጂሲ ግቢ ሽንት ቤት ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች የቁርዓን ቅዳጅ በአይነ ምድር ተለውሶ ወይም ሰገራ ታብሶበት ያገኛሉ፡፡በሁኔታው ግራ የተጋቡት እነኚህ ተማሪዎች ጉዳዩን በሚስጥር ይይዙትና ክትትላቸውን ይቀጥላሉ፡፡ድርጊቱ በድጋሜ ፈጸማል፡፡ በጉዳዩየተበሳጩት እነዚህ ጥቂት ሙስሊም ተማሪዎች የራሳቸውን ዘዴ መቀጠስ ጀመሩ፡፡ነገሩን ለሁሊም ሙስሊም ተማሪዎች ቢናገሩ የሚመጣውን አደገኛ ችግር ለመፍታት ዘዴ ቀየሱ፡፡ 1. ጉዳዩን ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቢያሳውቁ እንንተ ናችሁ ይህንን ያደረጋችሁ ሊባሉና ችግሩ ወደራሳቸው እንደሚመጣ ግምት ውስጥ በማስገባት ጉዳዩን በሚሥጥር በመያዝ ድርጊቱን የሚፈጽመውን ግለሰብ እጅ ከፍንጅ መያዝ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አስቀመጡ 2. ጉዳዩ ከተወሰኑ ሙስሊም ተማሪዎች በስተቀር ሌሎች እንዳይሰሙ በሚስጥር እንዲያዝ ወሰኑ፡፡ 3. ሰውየው እጅ ከፍንጅ እስኪዝ ድረስ ሰዓታቶች ተከፋፍለው ተማሪዎቹ ዋርድያ እንዲወጡ ተወሰነ፡፡ጥበቃውም በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠንከር ያለ ውሳና አስተላለፉ፡፡ 4. ሰውየው ምን አልባት ቢገኝ ምን እርምጃ ይወሰድበት በሚለው ዙሪያም ከፍተኛ ውይይት ካደረጉ በኋላ ለህግ ማቅረብብቻ እንደሚገባ ወሰኑ፡፡ 5. የሰውየውን ማንነት መለየት፤ተማሪ፣የከተማ ነዋሪ ወይም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ እንደሆነ መጀመሪ ማረጋገጥና እጅ ከፍንጅ በመያዝ ድርጊቱን ሲፈጽም በፎቶግራፍና በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ መያዝ እንደሚኖርባቸው ውሳኔ አሳለፉ፡፡ እንደተባለው ጥበቃው እንደ ነገሩ ክብደት እየከበደና እየረቀቀ መጣ፡፡የነዚህ ተማሪዎች ተስፋ በከንቱ አልቀረም፡፡ሁለተኛውን ድርጊት ከፈጸመ ከጥቂት ቀናት በኋላሌሊት የተለመደውን ተግባር ለመፈጸም አንድ ግለሰብ ወደ ሽንት ቤቱ አመራ፡፡ዘብ ነበሩት ተማሪዎች ሰውየውን ሲከታተሉት ወዘ ልውጥ የነርሱ ግቢ ሰው አለመሆኑን አረጋገጡ፡፡እንግዳ ፊት፡፡ሽንት ቤት ተጠቅሞ ሲወጣ ተከታትለው ሲገቡ የቁርዓን ቅዳጁ አይነ ምድር ተለውሶ ያገኛሉ፡፡ጠባቂዎቹ በነገሩ ቢበሳጩም በትግዕስት ሰውየውን ተከትለው ቤቱ ሲገባ ያዩታል፡፡እዚያው አካባቢ ቁጭ ብለው በማንጋት ማንነቱን ለዩ፡፡የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ሞግዚትና የደህንነት ሰራተኛ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ አሁን ነበር ትልቁ ፈተና የመጣው፡፡ተረኛ ሆነው ያደሩት ዘብ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ካምፓሳቸው ተመልሰው ጉዳዩን ለሚያውቁት ሙሉ መረጃውን ይነግሯቸዋል፡፡በነዚህ ብልህ ተማሪዎች መካከል አለመግባባት ተፈጠረ፡፡በጉዳዩ የተበሳጩትእርምጃ መውሰድን ቢመርጡም ከብዙ ውይይት በኋላ መስማማት ላይ ተደረሰ፡፡ሰውየው እንደለመደው ሊጠቀምበት ሲመጣ እንደሚይዙት እርግጠና ነበሩ፡፡ጥበቃው ሽንት ቤት ውስጥ ሆነ፡፡ጉዳዩን የሚፈጽመው ግለሰብ የሚያድረው ከዘቦች ቤት እንደሆነ ተረጋገጠ፡፡ግን ለምን ቤት እያለው ያለሥራ ቦታው ያውም ጥበቃ ሰራተኞች ቤት እንዲተኛ ተደረገ፤ሁሉንም ጊዜ ይፈታዋል፡፡ ስለ ሰውየው መያዝ፡- ሙስሊም ተማሪዎቹ 27 ቀናት ያለመታከት ሌሊት ሽንት ቤት ውስጥ እየተፈራረቁ ከጠበቁ በኋላ መጋቢት 19/2004 ግለሰቡ እንደለመደው ከጥበቃ ሰራተኞች ቤት ወጥቶ ሽንት ቤትከተጠቀመ በኋላ በጁ ይዞት በነበረው የቁርዓን ቅዳጅ ሊጠቀምሲል “አላህን ፍራ የያዝከው የጌታ(የአላህ) ቃል ስለሆነ አትጠቀምበት በማለት በፎቶና በቪዲ ይቀርጹት ጀመር፡፡የያዘው የቁርዓን ቅዳጅ አጨማትሮ “ምን ታመጣላችሁ”በማለት ከሱሪው የመቀመጫ ኪስ ከቶ ለመማታትና ለማምለጥ ቢሞክርም አልቻለም፡፡የቁርዓኑን ቅዳጅ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁትም አሻከፈረኝ አለ፡፡ግብረ አበሮቹ በመምጣት ምንአደረጋችሁ በማለት ለማስለቀቅና ለማስመለጥ ሞከሩ፡፡አልተሳካም፡፡ ከዚያም ግርግር በመነሳቱ ሰውየው ከነግብረ አባሮቹ ወደ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ፡፡ የሙስሊም ተማሪዎች መስማትና መሰባሰብ፡- ጉዳዩ 27 ቀናት ሽንት ቤት ውስጥ በጥበቃ መከራቸውን ሲያዩለነበሩት ጥቂት ተማሪዎች አላህ አስደሰታቸው፡፡የ4ቱ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎችም በደቂቃዎች የጎንደር ዩኒቨርሲቲህክምና ሳይንስ ኮሌጅን ቅጥር ግቢ አጥለቀለቁት፡፡ውጥረት ነገሰ፡፡ግን ሙስሊም “ሰላም” ነውና በርጋታ ጉዳዩን መጠየቅና መስማት ጀመሩ፡፡አዎ ውጥረት ነገሰ፡፡የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕረዚደንት፣የተማሪዎች ዲን፣የጥበቃ ኃላፊዎችና የተለያዩ ባለሥልጣናት ሙስሊም ተማሪዎችን ተቀላቀሉ፡፡ሁሉም ተማሪዎችም ሆኑ የዩኒቨርሲቲውባለሥልጣናት የአንድ ቀን ውጤት መስሏቸው ነበር፡፡ግን አይደለም፡፡ነገር ግን ውይይቱ ተጀምሮ ጉዳዩን ይከታተሉት ከነበሩት ውስጥ አንዱ 27 ቀናት በሽንት ቤት ውስጥ ስላሳለፉት ችግርና ይህንንም ያደረጉት ከሌሎች ሙስሊም ካልሆኑ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር የነበራቸው ሰላም እንዳይደፈርስና የዩኒቨርሲቲውን ሥም ለማስጠበቅ እንደነበርሲያስረዳ ወንዶች ከመድረክ ፊትለፊት ሴቶች ደግሞ ከበስተጀርባ የተሰማቸውን ሀዘን በእንባ እየተራጩ መግለጽ ቀጠሉ፡፡የማይረሳ ቀን ነበር፡፡የተማሪዎች ዲንም ምንም እንኳ ሙስሊም ባይሆንም በሁኔታው በማዘን በእንባ ሲታጠብ ውሏል፡፡በዙሪያቸው የነበሩ ፖሊሶች እንኳ በተማሪዎች ምርጥሥራ ተገርመው ያዳምጡ ነበር፡፡ ሙስሊም ተማሪዎችም የሰውየውን ሁኔታ ማወቅ እንፈልጋለን በማለት ጥያቄያቸውን ማቅረብ ጀመሩ፡፡የውይይቱ ድባብ ተቀየረ፡፡በተለይ የሰውየው ሁኔታ ሲታወቅ ተማሪዎቹ እጅግ ተበሳጩ፡፡አንድ ውሳኔ እስኪሰሙም እንደማይንቀሳቀሱ አሳወቁ፡፡የዩኒቨርሲቲው ም/ፕረዚደንትም ጉዳዩን ከያዙት ወንድሞች ጋር በመሆን ውሳኔያችንን እንሳውቃችኋለን ጠብቁ ብለው ተሰናበቱ፡፡ሁሉም ምሳውን እዚያው ተመገቡ፡፡ሁሉም እህሉ እንደመረራቸው ያስታውቃል፡፡ከአስር ሰላት በኋላ ም/ፕረዚደንቱና ተማሪዎች ተመልሰው መጡ፡፡ተማሪዎች ምላሹንለመስማት ጓጉተዋል፡፡ሁሉም ነገር ጸጥ አለ፡፡የዩኒቨርሲቲውአስተዳደር የወሰነው ውሳኔ ቀረበ፡፡ 1. ዩኒቨርሲቲው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታግለሰቡን ከሥራ ማባረሩን አሳወቀ፡፡ 2. ዩኒቨርሲቲው ግለሰቡ ይህንን ተግባር ሊፈጽም የቻለበት ዓላማና ተልዕኮ ምን እንደሆነ እንደሚመረምርና ጉዳዩን በራሱ የህግ ባለሙያዎች ተከታትሎ ውሳኔ እንደሚያሰጥ ቃል ገባ፡፡ 3. ጉዳዩንም ሁሉም ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መከታተልእንደሚችሉ አስታወቀ፡፡ 4. ጉዳዩም በፍርድ ቤት እንደሚታይና ለዐቃቤ ሕግ እንደተሰጠ በማስረዳት ሙስሊም ተማሪዎች 27 ቀናት በትግዕስት ተሞልተው የተማሪዎችን ሰላም በማስጠበቅ ወንጀለኛውን በመያዛቸው አመስግነው ወንጀለኛውን እንደሚያስቀጡት ድስኩር አሰሙ፡፡ 5. በዚህ የ12 ሰዓት ቆይታ ሙስሊም ተማሪዎች ሙስሊም ባልሆኑ አንዳንድ ግለሰቦች የተፈጸመባቸውን፣የሚፈጸም ባቸውንና ሊፈጸምባቸው የታቀዱትን ጉዳዮች በማንሳት እየደረሰባቸው ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣እየደረሰባቸው ያለው ግፍና በደል እንዲቆምላቸው የሚጠይቅ የፓናል ውይይትም ተካሂዷል፡፡ውይይቱም በሰላም ተጠናቀቀ……………. የወንጀለኛው መለቀቅ፡- ይህ ከባድ ወንጀለኛ የተከሰሰው በጎንደር ወረዳ ፍርድ ቤት ነበር፡፡ሆኖም ወንጀሉ ክባድ በመሆኑ እኛ የማየት ሥልጣን የለንም በማለት ወደ ሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይገፋዋል፡፡የሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍ/ቤትም እኔን አይመለከተኝም በማለት ወደ አማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይልከዋል፡፡ይህም ፍርድ ቤት ወደ ፌደራል ይልከዋል፡፡ነገሩክብደት ተሰጥቶታል፤ በሚል ፍትህ ልናገኝ ነው እያሉ ሲጠብቅለነበሩት የአራቱ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች፣የጎንደር ሙስሊም ህብረተሰብ፣ጉዳዩን ለሰሙት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን አንጀታችንን የሚሳርር ውሳኔ ተሰጠ፡፡ሰውየው ቀኑን በውል ባላውቀውም (ሚያዚያ 1 ወይም 2)/2004 በ15000.00(አስራ አምስት ሽህ ብር)ዋስተለቀቀ፡፡እርግጠኛ ሁኑ፡፡በዓይናችን በብረቱ ስላየነው፡፡ሁላችንም ግራ ተጋባን፡፡ዕውን ፍትህ አለ ለማለት ተገደናል፡፡ለዚህ ነው ኡኡኡኡኡአ የፍት ያለህ…… የመንግስት ለህ ያልነው፡፡ ጥያቄ፡ 1. ጉዳዩ በመጀመሪያ እንደተፈጸመ ለሁሉም ሙስሊም ተማሪዎችቢነገራቸው ምን ይከሰት ነበር 2. ተማሪዎቹ 27 ቀን ሽንት ቤት እያደሩ በብርድ እየተንሰፈሰፉ የያዙትን “በዘመኑ ቋንቋ” ትልቅ አሸባሪ እንደያዙት ቢገድሉትስ ኖሮ 3. ተማሪዎቹ እንደሰሙ እረብሻ ቢያነሱ ኖሮ በሁሉም አካባቢዎች(ዩኒቭረሲቲዎች ) ምን ሊከሰት እንደነበር ገምተዋል 4. አንድ ሙስሊም (አያደርገውም እንጅ)መጽሀፍ ቅዱስን ለሽንት ቤት መጠቀሚያ ቢደርግ እውን በዋስትና ይወጣ ይሆን ይህንን ልተወው፡፡ ግለሰቡ ይባስ ብሎ ከተፈታ በኋላ በተማሪዎች የመኝታ ክፍል ዙሪያ፣በካፌዎችና በዙሪያው እየተንጎራደደ ድሮ ሽፍታ ከዚያም ወታደር ከዚያ ደህንነት ነኝ እያለ እነዚያን ለሰላም የተዋደቁ ምስኪን ሙስሊም ተማሪዎች ማሰፍራራት መጀመሩ ለምን ይሆን፡፡ለነገሩ”ጌታዋንየተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች”ይባል የለ፡፡ምን ይደረግ! ለነርሱ አላህ አላቸው፡፡ ማጠቃለያ፡- 1. ይህ ግለሰብ ሙስሊሞችንና የሌላ ዕምነት ተከታይ ተማሪዎችን በማፋጀት የዩኒቨርሲቲውን ሰላም፣የሀገራችንን ሰላምለማደፍረስና ሀገራችን ከሌሎች ሙስሊም ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ግንገኙነት በማሻከር ካለብን ድህነት ላይ ሌላ ድህነት ለመጨመር ዓላማው አድርጎ የተነሳን ግለሰብ በዋስ መልቀቅ ምን ይሉታል ፍትሀዊ ነው ይገርማል፡፡ለነገሩ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” ይባላልእኮ….. 2. ዩኒቨርሲቲው ለሙስሊም ተማሪዎች የገባውን ቃል ለምን አልጠበቀም ለነገሩ ከማን የተማረውን 3. ዩኒቨርሲቲው ምናልባት ምንም አያመጡም ብሎ አስቦ ከሆነ ችግረ አለ ችግርም ይኖራል፡፡ወንጀለኛውም እነዚህን ምስኪንተማሪዎች ከማስፍራራት የማይቆጠብ ከሆነ…… ሰውየው ሌላ ተልዕኮ አለው ማለት ነው 4. መንግስት በዚህ ግለሰብ ላይ አፋጣኝ እርምጃ የማይወስድ ከሆነ ሁሉም ሙስሊሞች ጉዳዩን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ሚዲያዎች በማሳወቅ የሙስሊሙን ችግር ማሳወቅ ኖርብናል፡፡ስለዚህ ሁላችንም ለዚህ ዝግጁ እንሁን፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular