የ”አልቁድስ” ጋዜጣ ከመጅሊስ የበጀት ድጋፍ እንደሚደረግለት ተገለፀ

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 13/2004 የመጅሊስ አመራር በህዝበ ሙስሊሙ ላይ አስከትሏቸዋል በተባሉት ችግሮች ዙሪያ በአወሊያ ተቃውሞውን እያሰማ በሚገኘው ህዝበ ሙስሊም ህዝበ መሀል ይፋ የሆነው መረጃ ነው-የአልቁዱስ ጋዜጣ ከመጅሊስ የበጀት ደጋፈ እንደ ሚያገኝ ያጋለጠው፡፡ የጋዜጣው ዝግጅት ክፍል ከቅርብ ወራት ወዲህ በተደጋጋሚ የሚያወጧቸው ዘገባዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ውዥብር መፍጠራቸውን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡በዚህ ሁኔታ ላይ ተመሳሳይ ችግሮች ያሉባቸውን ዘገባዎች ዛሬም ይዞ መምጣቱን የቀጠለበት የአልቅዱስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ትላንት በአወሊያ ለ12ኛ ጊዜ በተካሄደው ሰላማዊ የመብት ማስከበር ሕዝባዊ ንነቅናቄ ላይ ከመጅሊሱ ለአንድ የጁምዐ ህትመት እስከ 22ሺብር የሚደርስ የበጀት ድጋፍ እንደተደረገለት ይፋ ሆኗል ፡፡ ለአንድ ወር 88 ሺ ብር ከመጅሊስ እንደተሰጠውም ተናግሯል፡፡ ለዚህም በማስረጃነት ቀረበው የመጅሊሱ ማህተም ያረፈበት ደብዳቤ ነው፡፡ መረጃውን ይፋ ያደረገው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው አባልና የታሪክ ፀሀፊው አህመዲን ጀበል ነበር፡፡ የአልቁድስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የመጅሊስን ድክመት በማጋለጥ ትታወቅ የነበረ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት ግን ሙሉ በሙሉ የመጅሊስን አቋም የሚያንፀባርቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular