alimu yedin temert endayastemru tekelekelu

አሊሙ የዲን ትምህርት እንዳያስተምሩ ታገዱ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ፊንፍኔ ወረዳ በሚገኘው ቡራዮ ኑር መስጂድ ጀመዓ አባላትን የዲን ትምህርት ሲያስተምሩ የነበሩት ዓሊም በክልሉ መጅሊስ አላግባብ መታገዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ ከስምንት ወራት በፊት ከኢማምነታቸው በክልሉ መጅሊስ አላግባብ እንዲነሱና በሌላ እንዲተኩ ከተደረገ በኋላ ሰሞኑን ደግሞ ቅሪአት እንዲያቆሙ እገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡ ቀደም ሲል ከኢማምነታቸው እንዲነሱ ሲደረግ የአካባቢው ጀመዓ አባላት ሠላምን በመውደዳቸው መቆየታቸውን ጠቁመዋል በአሁኑ ወቅት የአካባቢው ወጣቶች ያላቸውን የዲን እውቀት እንዲያስተላልፉ የክበቡ መጅሊስ አገዳ መጣሉ እንዳስቆጣቸው ገልጸዋል፡፡ ዓሊሙ ባቸው ተቀባይነት የቸካባቢው ህብረተሰብ በ180 ሺ ብር ወጪ የመኖሪያ ቤት እንደገዛላቸው አስታውቀዋል፡፡ ሼህ ሀሰን መሐመድ በበኩላቸው በመጅሊሱ አመራር አላግባብ ተፅዕኖ እደተደረገባቸው ይገልፃሉ፡፡ ውሃብይና አክራሪ በሚል ታርጋ ከኢማምነታቸው ካነሷው ወራት ቆይተውል፡፡ የቀበሌ አስዳደር አካላትም ዛቻና ማስፈራሪያ እንዳደረሱባቸው መሆኑን ተናግረዋል በጉዳዩ ዙሪያ የኦረሮሚያ መጅሊስን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካልንም፡

Related Articles

Latest Articles

Most Popular