Allahu Akber!! Yemejis ameraroch mulu lemulu kesltanachew endinesu tewesene

አላሁ አክበር!አላሁ አክበር! የመጅሊስ አመራሮች ሙሉ ለሙሉ ከስልጣናቸዉ እንዲነሱ ተወሰነ:: የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ወይም የመጅሊስ አመራሮች ሙሉ ለሙሉ ከስልጣናቸዉ እንዲወርዱ ዉሳኔ መተላለፍ ተሰማ:: ይህ ዉሳኔ የተላለፈዉ ባሳለፍነዉ ሀሙስ ሲሆንለመጅሊስ አመራሮች ይህ መራር ዜና በአቶ ፀጋዬ በርሄና በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተርዶ/ር ሽፈራዉ አማካኝነት ይፉ ተደርጎል:: በዉሳኔዉም መሠረት አሁን በስልጣን ላይ የነበሩት አመራሮች በሙሉ ከስልጣናቸዉ እንዲነሱና ስልጣናቸዉን እንዲያስረክቡ መወሰኑ ተገልፆል:: ከመጅሊስ አመራሮች በኩል እንዴት እንዲህ ይወሰንብናል በማለት ቅሬታቸዉን ቢያሰሙም ከላይ የመጣዉሳኔ መሆኑ ተገልፆላቸዎል:: የመጅሊስ አመራሮች ምርጫም ከሰኔ ወር ጀምሮ ሀምሌ ላይ እንደሚጠናቀቅ ታዉቇል:: የምርጫዉን ሙሉ ሂደት በተመለከተ የፌደራል ጉዳዮች ደንብ ያዘጋጀ ሲሆን ሙሉ የምርጫ ወጪዉም በፌደራል ጉዳዮች እንደሚሸፈን ምንጮች ገልፀዎል:: ምርጫዉን የኡለማዎች ም/ቤት እንዲያካሂደዉ የተወሰነ ሲሆን በምርጫዉ ላይ መወዳደርም ሆነ ታዛቢ መሆን የሚችለዉ የነባሩ እስልምና ተከታይ ብቻ መሆን እንዳለበት ተወስኗል:: ምርጫዉም በምንም አይነት መልኩ መስጂድ ዉስጥ እንደማይካሄድእና በየቀበሌዉ እንደሚካሄድም ወስነዎል:: የመጅሊስ አመራሮች ምርጫዉ በዚህ ጊዜ መካሄዱ የማይፈለጉ ሰዎች ሊቆጣጠሩት አይችሉም ወይ በማለት ስጋታቸዉን የገለፁ ሲሆን የፌደራል ጉዳዮች ለዚህ በቂ ዝግጅት ማድረጉን እና ስለዚህ ጉዳይ የመጅሊስ አመራሮች እንደማይመለከታቸዉ ተነግሮአቸዎል:: የአህባሽ ስልጠናም ነባሩየኢትዮጲያ እምነት በመሆኑ በአዲሱ መጅሊስም በተጠናከረና በአዲስ መልክ ተቀጣጥሎ እንደሚቀጥል ተወስኗል:: አወልያን በተመለከተ በአዲሱ መጅሊስ ሰርእንደሚተዳደርም ወስነዎል:: ይህንን በመጅሊስ አመራሮች ላይ የተወሰነዉን ዉሳኔ ቅዳሜ እለት ዎና ዎና አመራሮችን ጠርተዉ እንዲያሳዉቁ በፌደራል ጉዳዮች ስለታዘዙ ዉሳኔዉን ቅዳሜ እለት አሳዉቀዎል:: በዚህ ዉሳኔ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ክልል መጅሊስ አመራሮች ከፍተኛ ተቃዉሞ አሰምተዎል:: ይህን ሁላ ትግል እያደረግን እንዴት እንዲህ ይወሰንብናል ያሉ ሲሆን ይህ ዉሳኔ ከበላይ የመጣ በመሆኑ ዎጥ አድርጉና መራራዉን አጣጥሙ ተብለዎል:: በቅርቡ ተሹመዉ የነበሩት የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት እና የኡለማዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አማካሪዎች ግን ካሉበት ስልጣን ፍንክች እንደማይሉና ባሉበት እንደሚቀጥሉ መወሰኑ ታዉቆል:: በዛሬዉ እለትም የሁሉምክልል መጅሊሶች እና ጠቅላላ ጉባኤዉ ተሰብስቦ የተወሰነባቸዉን የስንብት ዉሳኔ ወይም መርዷተቀብለዎል Source: ድምፃችን ይሰማ page
Be the first to comment

Latest Articles

Most Popular