be alem lay yeminoru ethiopian yemuslimun teyaqe degefu

ኢትዮጵያውያኑ የህዝበ ሙስሊሙን የመብት ጥያቄ እንደሚጋሩት ገለፁ፡፡
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል የካቲት 
በላስ ቬጋስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮ አሜሪካውያን ሙስሊሞች በአወሊያ ተቋም ተማሪዎችና መላው 
ሙስሊም ህብረተሰብ መብቱን ለማስከበር ሠላማዊ ትግል ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ ፡፡
በላስ ቬጋስ ነቫዳ የሚገኙት ኢትዮጵያውያንና ኢትዮ አሜሪካውያን ሙስሊሞች ሰሞኑን በወቅታዊ የኢትዮጵያውያን 
ሙስሊሞች ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል ፡፡ኢትዮጵያውያኑና ኢትዮ አሜሪካውያኑ ነቫዳ ላይ ፌብሩዋሪ 22 2012 አስቸኳይ 
ስብሰባ በማካሄድ በወቅታዊ የህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡ውይይታቸውን ሲያጠቃልሉ 
ባወጡት ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫም በአወሊያ ተቋም በተማሪዎችና በመላው ህዝበ ሙስሊም የተጀመረውን መብትን 
የማስከበር ሰላማዊ ትግል እንደሚጋሩት አስታውቀዋል ፡፡የመጅሊሱ አመራር የህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄ የተወሰነ ቡድን 
ጥያቄ እንደሆነና የተወሰኑ የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ ነው በማለት ህዝቡን ከማደናገር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል ፡፡የኢትዮጵያ እስልምና 
ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራር አባላት የህዝቡ ተቀባይነት የሌላቸው በመሆኑ ቦታውን ለቀው በህዝበ ሙስሊሙ በሚመረጡ 
ሕጋዊ መሪዎች እንዲተኩም አጥብቀው ጠይቀዋል ፡፡በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ሕገመንግስቱ ላይ የተቀመጠውን
የእምነት ነፃነት በመተላለፍ በእስልምና ኃይማኖት ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት አጥብቀው እንደሚቃወሙ በአቋም መግለጫቸው 
አመልክተዋል ፡፡ኢትዮጵያውያኑና ኢትዮ አሜሪካውያን ሙስሊሞች ባወጡት በዚሁ የአቋም መግለጫ በህገመንግስቱ መሰረት የኢትዮጵያ 
ሙስሊሞች ኃይማኖታዊ ግዴታዎቻቸውን ያለ አንዳች ገደብና ተፅዕኖ በነፃነት እንዲተገብሩምጠይቀዋል ፡፡ለአብነትም የአበባበስ ፣
በጋራ በትምህርት ተቋማት ውስጥ መብቶቻቸው እንዲከበርላቸው ሲሉ ጠቅሰዋል ፡፡በቀጣይ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የጀመሩትን 
የመብት ማስከበር እንቅስቃሴ በሰላማዊና በተደራጀ መልኩ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ጠቁመዋል ፡፡ኢትዮጵያውያኑና ኢትዮ 
አሜሪካውያን ሙስሊሞች በአገር ቤትና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ከሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ጋር በመተባበር ከሰላማዊ ትግሉ ጎን 
እንደሚሰለፍምአረጋግጠዋል ፡፡ለሰላማዊና ለተደራጀው ቀጣይ ትግል አመቺ ይሆን ዘንድም ልዩ ኮሚቴ አቋቁመው መንቀሳቀስ መጀመራቸውን
 ኢትዮጵያውያኑና ኢትዮ አሜሪካውያኑ ለሬዲዮ ቢላል ዛሬ በላኩት በዚሁ የአቋም መግለጫቸው አስታውቀዋል ፡፡
  • talib4ever

    بسم الله الرحمن الرحيم
    ان الله سبحانه وتعالي لن يترك جهدكم واصراركم علي نصرة كلمته ودينه سدا واعلموابان رب ضارة نافعة إستمروا الله ناصركم (إن الله لايضيع أجر من أحسن عملا)

  • sebrina

    አላሁ አክበር!! የሁሉም ግዴታ ነው!!!

Latest Articles

Most Popular