be tegray Imamu yale mekniyat taseru

በትግራይ ክልል መሆኒ ከተማ ኢማሙ ባልታወቀ ምክኒያት ታሠሩ ኢማሙ ትላንት የጁምዓ ሠላት ከተሰገደ በኃላ ነው ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ያዋሏቸው፡፡ የሬዲዮ ቢላል ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት ከዛሬ 6 ዓመት በፊት በከተማዋ በሚገኘው ዋና መስጂድ መሰገድ በመከልከላችን ሣቢያ አንድ ባለሀብት ቤት ውስጥ ለ4 ዓመታት በመድረሳም በመስጂድም መልክ ስንጠቀምበት ብንቆይም በየግዜው የሚመነጡት ማስፈራሪያዎች ስጋት ጥሎብናል ብለዋል፡፡ ኃላም ይህ እየሰገዳቹ ያላችሁት ቤት እውቅና የለውም በሚል እንደወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ ኢማሙ የታሰሩበትንም ምክኒያት ሲያስረዱ እናንተ አሸባሪዎችና ዋሃቢዮቸ ናችሁ በሚል ምክኒያት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular