Facebook yaneqaneqeu tewuld na ye ahbash fetena

“ፌስቡክን ያንቀጠቀጠው ትውልድ” እና የአል-አሕባሽ ፈተና

ኡባህ አብዱሰላም ሰዒድ

የኢህአዴግ መሪዎች የነበሩበትን ትውልድ “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” ይሉታል። በዘመኑ እንደተራራ ገዝፈው ይታዩ የነበሩትን የደርግ ጄኔራሎች ባልጠበቁት መንገድ እያዘናጉ ጉድ እንደሰሩት ለመግለጽ የፈጠሩት ስም ነው። ከ2010 ማገባደጃ ጀምሮ በዐረብ ሀገሮች ሲካሄዱ የነበሩትን ሰላማዊ ንቅናቄዎች የመሩት የፌስቡክ ወጣቶች መሆናቸው ያስገረማቸው ታዛቢዎች ደግሞ እኔ ላለሁበት ትውልድ “ፌስቡክን ያንቀጠቀጠው ትውልድ” የሚል ስም ሰጥተውታል። እኔም እነርሱ በሰጡን ስም መጠራቱን ወድጄዋለሁ።

ይህ  ትውልድ አስገራሚ ተግባራትን የከወነው በውጪው ዓለም ብቻ አይደለም። በሀገራችንም ለዝክር የሚበቁ ታሪኮችን እያስመዘገበ ነው። ለምሳሌ ፌስቡክን ያንቀጠቀጠው ትውልድ የዓለም ሙስሊሞችን ግራ ሲያጋባ የኖረውን የአሕባሽ ቡድን ጉድ ሰርቶታል። በሌላ ዓለም ያልተቻለው አሕባሽ በሀገራችን ቅትረ-ቀላል ሆኗል። አንዳንድ ኩነቶችን ቀንጨብ እያደረግኩ ላሳያችሁ።  

አል-አሕባሽ የርስ በርስ ጦርነት በበጣጠቃት የሊባኖስ መዲና ውስጥ ሲቋቋም የተከተለው የገለልተኝነት ስልት በጣም ጠቅሞታል። ህዝቡ እንደ ነጻ አውጪ የሚመለከተው የሶሪያ ጦር ሀይል ጠንካራ ክንድ  ታክሎበት “ዘመናዊ የእስልምና ቡድን አሁን ተገኘ” የሚሉ ወጣት ደጋፊዎችን በብዛት አፍርቷል። ወደ ሀገራችን ሲመጣ ግን ጉዳዩ ሌላ ሆኖ ነው የተገኘው። የሀገራችን ወጣቶች ሰምተው የማያውቋቸውን እንደ “የብሪታኒያው ሰላይና የሙሐመድ አብዱልወሃብ ሚስጢር”ን የመሳሰሉ ታሪኮች እየደሰኮረ ወጣቶቻችን ለማማለል ቢሞክርም አልቀናውም። (“የነቢዩን ጸጉር ተመልከቱ” የሚለው ቀሽም ቲያትር ደረጃውን ያልጠበቀ የህጻናት ካርቱን ፊልም በመሆኑ በዚህ ጽሁፍ ሳልጠቅሰው አልፈዋለሁ።).

አንጃው ለራሱ ከፍተኛ ግምት ይሰጣል። ዓለም በተራቀቀበት ዘመን እንኳ ብልጣብልጥ ሆኖ ሙስሊሞችን መሸወድ የሚችል ይመስለዋል። ታዲያ ወጣቶቻችን ጉድ ሰሩት። የኢማም አቡል ሐሰን አል-አሽዓሪን የአቂዳ ትምህርት ለማስጠበቅ ብርቱ ትግል የሚያደርግ ሳተና በመምሰል የሙስሊሞችን ድጋፍ ለማሰባሰብ ቢሞክርም ማንም አልሰማውም። ከዚህ ይልቅ ወጣቶቻችን የኢማም አል-አሽዓሪ ትምህርት በስፋት ከሚሰጥበት የአል-አዝሀር ዩኒቨርሲቲ የተሰጠ ፈትዋ አምጥተው “የኑፋቄና የጥመት ቡድን ነህ” የሚል መርዶ ነገሩት። “ሱፊ ነኝ፤ ወሃቢዎች መውሊድ አይከበርም ይላሉ” እያለ ቢያላዝንም በዓለም የታወቁ የሱፊ ማዕከላት በአሕባሽ ላይ ያስተላለፉትን ውግዘት አሰሙት። “ወሃቢዎች ሙጀሲማ ናቸው፤ አላህን ከሰው ልጅ ጋር ያመሳስላሉ” እያለ ቢያወናብድም “አሊ ኢብን አቡ ጣሊብ በሰው መልክ የተገለጸው አምላክ ነው” ከሚሉት የሶሪያ መሪዎች ጋር ያለውን ግልጽ የወጣ ፍቅር በመንተራስ “ስለሙጀሲማ ለማውራት ከፈለግክ ትክክለኛ ምሳሌ ማድረግ የነበረብህ የሶሪያ የአሊዊ ፊርቃ ተከታዮችን ነው” አሉት። ከሁሉም የባሰው መርዶ ደግሞ በፌስቡክ ላይ ተነገረው። ወጣቶቻችን “አሕባሽ ADL የተባለው የጽዮናዊያን ድርጅት አባል ነው” የሚል በማስረጃ የተረጋገጠ ሚስጢር በማውጣት በህዝብ ፊት አዋረዱት። ይህንን ታላቅ መርዶ የነገሩት የውጪ ሀገር ሰዎች ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ነን። (ለዝርዝሩ ይህንን ሊንክ ይከተሉ www.adl.org/philadelphia/coalition.asp)

ወገኖቼ! አሕባሽ የተስፋዬ ሀገር ናት በሚላት ኢትዮጵያ ውስጥ ሺህ ምንተሺህ አባላት አፈራለሁ የሚል ሀሳብ ነበረው። ግን ወጣቶቻችን ውርደት አከናንበውታል። አምባሳደር ዴቪድ ሺንና ፕሮፌሰር ሀጋይ ኤርሊች አሕባሽን የሚያንቆለጳጵሱበትን ትክክለኛ ምክንያት ለመረዳት የቻልነው አንጃው ዘንድሮ በሀገራችን ውስጥ ይፋ ዘመቻ ከጀመረ በኋላ ነው። ከዚህ በፊት “ጽዮናዊው Anti-Defamation League (ADL) የአል-አሕባሽ የጡት አባት ይሆናል” የሚል ጥርጣሬ ኖሮን አያውቅም። በዚያ ላይ እስላማዊ ነኝ የሚል ቡድን ከግብረ-ሰዶማዊያን ጋር ጥምረት ይመሰርታል የሚል ግምት በማንም አእምሮ አልነበረም (ከጽዮናዊው ADL ጋር ጥምረት የፈጠሩ ድርጅቶችን በሚያሳየው ዝርዝር ውስጥ የግብረሶዶም መብት ተከራካሪ ድርጅቶችም እንደሚገኙበት ልብ በሉ”) ። ግን ሆነና ተገኘ። አሕባሽም  ተዋረደ። በኢማም አል-አሽዓሪና ኢማም ሻፊዒ ስም እያጭበረበረ ወደ ሽርክ፣ ባእድ አምልኮና ቢድዓ ሊያስገባቸው የተመኛቸው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ዋጋውን ሰጡት።  

አሁን አሕባሽ በኢትዮጵያ ውስጥ ምን ይቀረዋል? ሌላ እድል መሞከር ወይስ አርፎ ወደመጣበት መመለስ? እርግጠኛውን ነገር አላህ ነው የሚያውቀው። በኔ በኩል ሌላ ታክቲክ ይዞ የሚመጣ ይመስለኛል። ያኔ ደግሞ እኛም ሌላ ስልት ቀይሰን እንጠብቀዋለን። ኢንሻ አላህ!!!

ድል የኢስላም ነው!! አላሁ አክበር!!

  • Sebrina Ahmed Banned

    እላሁ አክበር!!! ድል ለኢትዮ ሙስሊም!!

Related Articles

Latest Articles

Most Popular