good news ye shashemene mejlis be fedralu mejlis almeram ale!!!

የሻሸመኔ መጅሊስ በፌደራሉ መጅሊስ እንደማይመራ ገለፀ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 12/2004 በኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሲመራ የቆየው የሻሸመኔ መጅሊስ ካሁን በኋላ በፌደራ ምክር ቤት እንደማይመራ ተናገረ፡፡ አዳማ ላይ በተደረገው የአህባሻ ስልጠና በኦሮሚያ መጅሊስ አመራሮች ውሃብይና አክራሪዎች በመባላቸው ልዩነት መፍጠሩን የሻሸመኔ የመጅሊስ ሀላፊዎች ገልፀዋል፡፡ የሻሸመኔ የእስልምና ጉዳይ የኦዲተር ኮሚቴ እንደገለፁት የፌደራልና የኦሮሚያ መጅሊሶችን የሚሠጡት የአህባሽ ስልጠና ባለመቀበላችን መዋቅሩን ያልጠበቀ የሥራ እግድ ደብዳቤ ተፅፎልናል ብለዋል፡፡ የፌደራልና የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች በሻሸመኔ ከተማና በአርሲ ዞን ያሉ ሙስሊሞች ውሃቢይዎችና አሸባሪዎች ናችሁ ብለው መፈረጃቸውንም የኦዲተር ኮሚቴው ገልፀዋል፡፡ የሻሸመኔ ሙስሊም ነዋሪዎች በሁለቱም ነዋሪዎች መጅሶቹ ላይ ተቃውሞአቸውን እያቀረቡ ሲሆን የሻሸመኔ መጅሊስ ከህዝቡ ጎን ነው ሲሉ በኢትዮጲያ ደረጃ ለመንግስት ጥያቄ ያቀረበው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እንደሚደግፍም ጠቁመዋል፡፡
  • jewar mohammed

    alihamidulilah allah haqin yizew miyafir ayaderigen

Latest Articles

Most Popular