ke 270,000 yemtegu yeharer newariwoch ahbashen teqawemu

የመጅሊስን አመራር በማውገዝና የአህባሽን አስተምህሮት በመቃወም ከሐረር ክልል ከ270 ሺ በላይ ነዋሪዎች የተቃውሞ ድምፃቸውን አሰሙ መጅሊስን አመራር የአህባሽን አስተምህሮት በመቃወም ከሐረር ክልል ሙስሊሞች ቅሬታቸውን ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ፅ/ቤት ትላንት አቀረቡ፡፡ ተወካዮቹ መንግስተ ለህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ሰሞኑን ይፋ ያደረገው ምላሽ ስላላስደሰታቸው ቅሬታቸውን ለማቅረብ ተገደዋል፡፡ ምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ ሁሉሉም ወረዳዎች ጨምሮ ከሐረር ድሬደዋ ከተሞች የሚገኘውን ህዝብ ሙስሊም በመወከል የመጡት አራት ተወካዮች ናቸው ትላንት በህዝብ የተፈረመውን የተቃውሞ ፒቲሽን ያስገቡት ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክላላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት ተወካዮቹ ለሬዲዮ ቢላል እንደገለፁት የክልሉ ሕዝብ ይህንኑ የተቃውሞ ድምፅ ለክልሉ ምክር ቤት አመራሮች ቢያሳውቅም ምላሽ አላገኘም ፡፡ እናም ለፌደራል መንግስት ለማሳወቅ ተገደዋል በሃረርና አቅራቢያ የሚገኙ የኦሮሚያ ወረዳዎች ያቀረቡት ቅሬታ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ፅ/ቤት መግባቱን ነው የገለፁት ፡፡ በአወሊያ የህዝብ ንቅናቄ የተቋቋመው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ለመንግስት ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ የመንግስትን ምላሽ ሲጠባበቁ እንደነበር ተወካዩ ገልፀዋል፡፡ ይሁንና በመንግስት የተሰጠው ምላሽ አላረካቸውም ግልፅም አልሆነም እናም የህዝቡን ቅሬታ ለማወቅ መገደዳቸውን ነው ያመለከቱት፡፡
  • sebrina@rocketmail.com

    Alahu Akber!! Gena Tarik yiseral....!Insh Allah

Related Articles

Latest Articles

Most Popular