SUNDAY, 11 MARCH 2012 ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በአፍራሽ ኃይሎች ብዥታ እንደተፈጠረበት የኡላማዎች ምክር ቤት አስታወቀ

SUNDAY, 11 MARCH 2012 00:00 BY HAILE MULU HITS: 642 ethiopian reporter news - ‹‹አገሩ እየተበጠበጠ ያለው ከውጭ በሚመጣ ዕርዳታ ነው›› የኢትዮጵያ ኡላማዎች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት - ‹‹የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጥያቄያችንን አልመለሰም›› የሙስሊም ማኅበረሰቡ ተወካዮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በተለያዩ ቦታዎች እየሰጠ ያለውን ሥልጠና በማስመልከት በአንዳንድ ኃይሎች የሚናፈሰው አሉባልታ፣ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ላይ ብዥታ የፈጠረ መሆኑን የኢትዮጵያ ኡላማዎች ምክር ቤት ገለጸ፡፡ የኡላማዎች ምክር ቤቱ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ ክልሎች እየተሰጠ ያለው ሥልጠና የሙስሊሙን የዲን ዕውቀት ለማጐልበት ታስቦ ትክክለኛውን መንገድ እንዲይዙ ለማድረግ የተከናወነ እንጂ፣ አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት ሌላ እምነት ለመስበክ አይደለም፡፡ የኡላማዎች ምክር ቤት በኡላማዎች የሚሰጠውን ትምህርት የተከታተለ መሆኑን የገለጹት የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሼክ ኢዘዲን አብዱልአዚዝ፣ በትምህርት ሒደቱ ላይ በጠቅላላው ማስረጃ ተደርገው የተጠቀሱት ከቁራን፣ ከሀዲስ ከኢጅማዕና ከአራቱ መዛሂብ መሪዎች መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ሥልጠናው እየተሰጠ ያለውም በፈቃደኝነት መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡ ዋና ጸሐፊው እንዳሉት፣ ሥልጠናውን በአሁኑ ጊዜ መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት ነብዩ መሐመድ እንደገለጹት አፍራሽ የሆኑ አስተሳሰቦች፣ ብቃትና ዕውቀት የሌላቸው፣ ያለፉትን ኡላማዎች የሚያጣጥሉ ሰዎች የሚመጡበት ወቅት በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ቀደም ሲል የነበሩትን ብርቅዬ ኡላማዎችን ፈለግ እንዲከተል ለማድረግ ታስቦ እንጂ፣ አዲስ እምነት የመጣ አለመሆኑን ሊያውቅ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡ በኡላማዎች ምክር ቤት የፈተዋ ዘርፍ ኃላፊ ሼክ ሙፍቲ አብዱልቃድር በበኩላቸው፣ በአሁኑ ጊዜ አገሩ እየተበጠበጠ ያለው ከውጭ በሚመጣ ዕርዳታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ትምህርት እየሰጡ ያሉት ኡላማዎች ከቁራንና ከሀዲስ ውጪ የተለየ ነገር ይዘው አለመምጣታቸውን የገለጹት ሼክ ሙፍቲ፣ በውጭ የገንዘብ ዕርዳታ የሚሽከረከሩት አንዳንድ ወገኖች የፈለጉትን ነገር ስላላገኙ ‹‹ኡላማዎች አዲስ ዲን (አስተምህሮ) ይዘው መጥተዋል፤›› በማለት ሙስሊሙን ኅብረተሰብ ብዥታ ውስጥ የከተቱት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአወሊያ ትምህርት ቤት የሚሰበሰቡ ሙስሊሞች የእስልምና ምክር ቤቱ አስገድዶ እያስተማረ ነው የሚል ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ የኡላማዎች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼክ መሐመድ ሀሰን ግን የእስልምና ምክር ቤቱ ትምህርት የሚሰጠው በፈቃደኝነት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ኡላማዎች እያሉ ለምን ከሊባኖስ መሻሂዎችን አስመጣችሁ?›› በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፣ ትክክለኛ ትምህርት እስካስተማሩ ድረስ ከየትም አገር ኡላማዎች መጥተው ቢያስተምሩ የሚያስከትለው ችግር እንደማይኖር ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ከሊባኖስ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች አገሮች የሚመጡ ኡላማዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አመልክተዋል፡፡ ‹‹የእስልምና ምክር ቤት ምርጫ መካሄድ አለበት፣ የአወሊያ ትምህርት ቤትም በመጅሊስ መተዳደር የለበትም፤›› በሚል በተደጋጋሚ እየቀረበ ያለውን ጥያቄ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የኡላማዎች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሼክ ኢዘዲን አብዱልአዚዝ፣ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. በተካሄደው የእስልምና ምክር ቤቱ ስብሰባ ምርጫ መካሄድ እንዳለበት መወሰኑንና ለዚህም ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ አወሊያ ትምህርት ቤት ግን እንደ ሌሎች ትምህርት ቤቶችና መስጂዶች ሁሉ በመጅሊስ መተዳደር ያለበት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በተያያዘ ዜና በብዙ ሺሕ በሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተወክለናል የሚሉ የኮሚቴ አባላት ለፌዴራል ጉዳዮች ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ያልተመለሱላቸው መሆኑን አስታወቁ፡፡ በተከታታይ ለዘጠነኛ ሳምንት በአወሊያ ትምህርት ቤት በተካሄደው የጁማ ሶላት ተገኝተው ሪፖርት ያቀረቡት የኮሚቴ አባላት ለሙስሊም ማኅበረሰቡ እንደገለጹት፣ ‹‹የእስልምና ምክር ቤቱ እያስገደደ ማስተማሩን ያቁም፣ የመጅሊስ ምርጫ መካሄድ አለበት፤ አወሊያ ትምህርት ቤት የሕዝብ በመሆኑ በመጅሊስ ሥር መሆን የለበትም፤›› የሚሉ የመደራደሪያ ነጥቦች የቀረቡለት ፌዴራል ጉዳዮች አጥጋቢ ምላሽ መስጠት አልቻለም ይላሉ፡፡ እነኝሁ ተወካዮች እንደሚሉት፣ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ምርጫ ይካሄዳል ቢልም መቼና እንዴት እንደሚካሄድ አልገለጸም፤ አወሊያ ትምህርት ቤትም በተመረጡ የቦርድ አባላት ይተዳደራል ቢልም ቦርዱ ውስጥ ማን እንደሚካተት በግልጽ አልተናገረም፡፡ አህበሽ የተባለው አስተምህሮም አዲስ ነገር ባለመሆኑ በፈቃደኝነት ማስተማሩ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ‹‹ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ያቀረብነው ጥያቄ በቂ ምላሽ አላገኘም፤›› ያሉት ተወካዮቹ፣ ፌዴራል ጉዳዮች የመንግሥት አካል እንጂ መንግሥት ባለመሆኑ በቀጣይ የሙስሊም ማኅበረሰቡን ጥያቄ ይዘው ወደ ፓርላማ፣ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮና ወደሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በመውሰድ ሰላማዊ ትግል እንደሚያካሂዱ አስታውቀዋል፡፡ በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ሙስሊሞች በተፈረመ ፒቲሽን ውክልና አለን የሚሉት እነኝሁ የኮሚቴ አባላት፣ ከፌዴራል ጉዳዮች ጋር ሳይስማሙ እንደተስማሙ ተደርጐ በሚዲያ መግለጫ መሰጠቱን በመቃወም ለፌዴራል ጉዳዮች ደብዳቤ የጻፉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ለሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ የጻፉትንም ደብዳቤ በአወሊያ ትምህርት ቤት ለተሰበሰቡት የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት ማንበባቸውንም አስታውቀዋል፡ bilal tube comment >> we are asking who is ethiopain ulema mekerebet they are same mejils enesu rasachewu meweged albeachew፡
  • Zuria Timtim

    It appears to me that all 23 comments were removed from Reporter.
    Can anyone explain to me why they would that while complaining on the government for the very same act.

Related Articles

Latest Articles

Most Popular