TRYING TO SHUT DOWN TV AFRICA BROADCASTING ዘመቻ ቲቪ አፍሪካን ለማዘጋት !!!

ዘመቻ ቲቪ አፍሪካ !

ከወራት በስተፊት በተላለፈለት ቀጭን ትዕዛዝ መሠረት አህመዲን አብዱላሂ ቲቪ አፍሪካ መቻቻልን እንደሚያጠፋ እና ለሀገር አደጋ እንደሆነ በመግለፅ ደብዳቤ ይፅፋል፡፡ ይህንኑ ደብዳቤ በማያያዝም አንድ የኮማንደር ማዕረግ ያላቸው ግለሰብ መጅሊሱ በፃፈልን መሠረት በማለት ለአረብ ሳትና ለቲቪ አፍሪካ TV Africa ይዘጋልን ሲሉ ደብዳቤ ፃፉ፡፡ ደብዳቤው የተፃፈላቸው አካላትም በመገረም የምትሉትን ነገር የሚያሳይ (ማለትም መቻቻልን እንዳጠፋና ግጭት እንደፈጠረ) ከፕሮግራሙ ላይ ቀድታችሁ በአንድ ወር ውስጥ አድርሱን አሏቸው፡፡ ይህ የሆነው አምና ረመዷን ላይ ነበር፡፡ ቲቪ አፍሪካ እንዲዘጋ ጥያቄ ያቀረቡት አካላት ከብዙ ቆይታ በኋላም ቢሆን የሚያቀርቡት አላገኙም፡፡ ሆኖም እነኚሁ አካላት ዙልሂጃ (ከ ሥምንት ወራት በፊት) ላይ ደውለው ጉዳዩን (ይዘጋልን የሚለውን) ምን ላይ አደረሳችሁት ሲሉ ቢጠይቁም አምጡ ሲባል ምንም ነገር አላመጣችሁም ስለዚህ ምንም ነገር ማድረግ አንችልም በማለት ይመልሷቸዋል፡፡ ከዚህ አልፎም ኢሳት ላይ እርምጃ ወስዳችሁ እንደዘጋችሁት ቲቪ አፍሪካን ለመዝጋት ብትሞክሩ የናንተን አረብ ሳት ላይ ያለውን ሁሉንም ጣቢያ እናጠፈዋለን በሚል ሁኔታ ነበር ጉዳዩ የተቋረጠው፡፡ አሁን ደግሞ ሁለተኛ ዙር ሙከራ ማድረጋቸው ሳይሆን አይቀርም የሚለተለውን ጆሯችን ሰማ፡፡

ሪያድ ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጫና ፈጥሮ ቲቪ አፍሪካነን ለማዘጋት ባለፈው እና በዚህ ሣምንት አረብ ሳት ቢሮ ሪያድ ላይ ሲመላለሱ ነበር ፡፡ የነኚህ ሰዎች ፍላጎትና ዓላማ ቲቪ አፍሪካ ኢ/ያ ውስጥ ችግር እየፈጠረብን ነውና ዝጉልን ማለት ሲሆን፣ከሶስት ወር በፊትም ልዑካን በመላክ ማን በገንዘብ እንሚደጉመው እና አልፎም ሊዘጋ የሚችልበትን መንገድ ለመፈለግ ልዑካኖቻቸውን ወደካርቱም ልከው እንደነበር ታውቋል፡፡ ሪያድ አካባቢ ከሚገኘው ቢሮ የተገኘውም መረጃ ይህንኑ የሚያመለክት ሲሆን ጥረታቸው በሙሉ ቲቪ አፍሪካን ማዘጋት ነው፡፡
Be the first to comment

Latest Articles

Most Popular