yemuslimu tegele beyemeskidu endeqetele tenegere Allahu akber

በአወሊያ ሲካሄድ የነበረው የሙስሊሙ ህብረተሰብ የመብት ጥያቄ በመስጂዶችም ቀጥሏል አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት17/2004 ለተከታታይ 11 ሳምንት በአወሊያ ሲካሄ የነበረው በአሁኑም ወቅት በከተማዋ ባ ሌሎች መስጂዶች መጀመሩን በየመስጂዱ የሚገኙ ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡ ታቃውሞው እየተገለፀያለው በተክቢራ ሲሆን እንቅስቃሴው ከተጀመረባቸው መስጂዶች መካከል የአንዋር የቄራ እንደሚጠቀሱ ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ የመፍትሄ አፈላላጊው ኮሚቴው ባለፈው ጁምዓ ከአወሊያ ኢስላማዊ ማዕከል ለተገኘው ሕዝብ ሙስሊም በየአካባቢው በሚገኙ መስጂዶች ሕዝቡ ሰላማዊ ትግሉን መቀጠል እንደሚችል ጠቅሶ ነበር፡፡ ኮሚቴው በቀጣይ ሶስት ሳምንታት ጅምር እንቅስቃሴዎች አጠናክሮ በመቀጠል የደረሰበትን ለህዝበ ሙሊሙ እንደሚያሳውቅ ቃል መግባቱ አይዘነጋም ፡፡ የህን ተከትሎ ባፈው ጁምዓ ቅዳሜ በርካታ ምዕመናን በየአቅራቢያቸው በሚገኙ መስጂዶች የህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጣቸው በተክቢራ ጠይቀዋል፡፡
Be the first to comment

Latest Articles

Most Popular