VOA NEWS AMHARIC የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን ሊቀ መንበር ዛይናቦ




5,070 Views

Published

የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን ሊቀ መንበር ዛይናቦ ሲልቪ ካዪቴሲ በቅርቡ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ደብዳቤ ጽፈው በእሥር ላይ በሚገኙት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ እየደረሰ ነው የተባለውን የመብቶች ጥሰት እንዲያጣሩ ጠይቀዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ለደብዳቤው እስካሁን ምላሽ እንዳልሰጠ ሲታወቅ መንግሥት ሰዎቹን በቁጥጥር ሥር ያዋለው ”አሸባሪዎች” ናቸው ሲል ከስሶ ነው።

ሰሎሞን ክፍሌ የኮሚሽኑን ደብዳቤ ይዘትና በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ ጠበቆቻቸውን አነጋግሮ ተከታዩን ለምሽቱ ፕሮግራም አጠናቅሯል።  

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Category
Dimtsachen Ysema Tegel Video
Be the first to comment