Camerawoman Petra Laszlo sentenced for kicking refugees

 ሰበር ዜና 
 የሶሪያ ስደተኞችን ጠልፋ የጣለችው ሐንጋሪያዊቷ የካሜራ ባለሙያ ፔትራ ተፈረደባት ዝርዝሩን ያንብቡ

 

 

ሐንጋሪያዊቷ የካሜራ ባለሙያ ፔትራ ላስሎ ባገሯ ድንበር የተጠለሉ ስደተኞች ላይ በፈፀመችው

ኢ–ግብረ ገብ ድርጊት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባለች። ፔትራ በቪዲዮ ተደግፎ የቀረበባትን ክስ ተከትሎ

«ራሴን ለመከላከል በጭንቀት ውስጥ ሆኘ ያደረግኩት ነው፤» በማለት በለቅሶ ታጅባ ብታስተባብልም ፤

ድርጊቷ ሆን ተብሎ የተደረገ የማጥቃት ተግባር መሆኑን የቪዲዮ ምስሉን በዝግታ በማንቀሳቀስ

ማሳዬት ተችሏል። ዳኛውም “ይህ ተግባር የማህበረሰቡን ግብረ ገብነት የሚፃረር ነው፤”

ካሉ በኋላ ለሶስት ዓመት በቁም እስር ላይ ሆና ካሳየችው የባህሪ ግድፈት እንድትታረም ወስነውባታል።

 

By 

DANA MULTI MEDIA