Dr. Zakir Naik’s IRF banned for five years

  የዶክተር ዛኪር ናይክ የዳዕዋና የንፅፅር ትምህርት ማዕከል የሆነው IRF አይ አር ኤፍ ታገደ!

በታዋቂው ህንዳዊ ዳዒ የተመሠረተውና በብዙ ሺዎች
ለሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ኢሥላም መመለሥ ሠበብ የሆነው
በምህፃረ ቃል(IRF)ኢሥላሚክ ሪሰርች ፋውንዴሽን
ከማንኛውም እንቅሥቃሴ ለአምሥት አመት ታግዷል።
ከወራት በፊት ባንግላዴሽ ውስጥ ለደረሠወ ፍንዳታድርጅቱ ላይ
ጣት ቢቀሠርም የህንድ መንግሥት በቂ መረጃ ስላላገኘ ክሱን
ውድቅ አድርጎት ነበር።
ይሁን እንጂ ድሮም ለመዝጋት ዳር ዳር ሲል የነበረው የህንድ
መንግሥት አጋጣሚውን ተጠቅሞበታል።ዶ/ሩ ሠላማዊ በሆነ
መንገድ የሚያደርጋቸው የመድረክ ውይይቶች መቸም
የማይዋጥላቸው የኢሥላም ጠላቶች ዳዕዋውን ለማደናቀፍ ወደ
ሐገራቸው እንዳይገባ ቪዛ ሁሉ እስከመከልከል ደርሠዋል
እንግሊዝ፣ካናዳ ወዘተ ይጠቀሳሉ።
ሀስቡነሏህ ወኒእመል ወኪል!