Health Benefits Geiger
የዝንጅብል የ ጤናጠቀሜታወች
1.ዝንጅብል ጤናማ የደም ዝውውር እንዲኖረን ከሚያደርጉ ነገሮች ቀዳሚው ነው፤ ዝንጅብል በውስጡ እንደ ክሮሚየም፣ ማግኒዝየም፣ ዚንክን የመሳሰሉና በሰውነታችን የደም ዝውውር ሂደትን የሚቆጣጠሩና የሚያስተካክሉ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ ይዟል።
በተጨማሪም እንደ ትኩሳት፣ ከልክ ያለፈ ላብ እና ድብርትን የመከላከል አቅሙም ከፍተኛ ነው።
2. ከአተነፋፈስ እንዲሁም ከአፍንጫችን ጋር የተያያዙ ህመሞችን የመፈወስ አቅሙም ከሁሉም ተመራጭ ያደርገዋል።
በመሆኑም እንደ ሳል፣ ለረዥም ጊዜ የሚዘልቅ የማስነጠስ ስሜት፣ የጉሮሮ ህመምን በመፈወስ ረገድ ወደር የሌለው እንዲሆን አስችሎታል።
3. ሰውነታችን ጠቃሚ ንጥረነገሮችን በሚገባ እንዲጠቀም መንገድ ከፋች በመሆን የውስጥ የአካል ክፍሎቻችንን ስራም ያግዛል፤
4.ዝንጅብል የአለማችን ቁጥር አንድ ጉንፋን ተከላካይ ዝርያ ነው፤በተለምዶ የብርድ በሽታ ለምንለውና ለጉንፋን ፤ ፍቱንነቱንም ባለፉት በሺዎች በሚቆጠሩት ዓመታት በእስያና በሌሎችም የዓለማችን ክፍሎች በጥቅም ላይ ውሎ አረጋግጧል።
5.የሆድ ህመምን ለማስታገስም ሆነ ለማዳን ተመራጭ የሆነው ዝንጅብል፥ የምግብ መፈጨት ሂደትን በማቀላጠፍ ፤ በመድሃኒት መልክ የምንወስዳቸውንና የጎንዮሽ ጉዳት ያላቸውን እንደ አስፕሪን የመሳሰሉት የመድሀኒት አይነቶች የሚሰጡትን ጥቅም ያለምንም የጎንዮሽ ጉዳት የሚተካም ነው።
6. ዝንጅብል የማቃጠል ስሜትና ህመምን በማስታገስ ባለው ተፈጥሮዓዊ ይዘቱም ህመም አስታጋሽ (pain killer) እየተባም ይሞካሻል።
7.ዝንጅብል ኦቫሪያን ካንሰር ተብሎ የሚጠራውን የካንሰር አይነት በመፈወስ ረገድ ውጤታማ ነው፤ በተለይም በዱቄት መልክ ቢወሰድ ውጤቱ ከፍ ይላል።
8.ዝንጅብልየሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም በእጅጉ የማጎልበት አቅም ያለው ሲሆን፥ በተለይም ስትሮክ(የልብ ህመም)፣ ከልክ ላለፈ ውፍረት፣ ጨጓራችን በባክቴሪያ እንዳይጠቃ ይከላከላል።
9. የማቅለሽለሽ እና የቃር ስሜቶችን በማስወገድ በኩልም ዝንጅብል ተወዳዳሪ የለውም፣ በመሆኑም በተለይም ነፍሰጡሮች በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ወራቶች ቢጠቀሙበት ጥቅሙ ከፍተኛ ይሆናል።
@ Ethio Bilal Tube Tena