SAUDI COURT FREED ETHIOPIAN MAN

ራሱን እና ቤተሰቡን ለማዳን የ ሳዉዲውን ወጣት የገደለዉ ኢትዮጲያዉ
በ ፍርድ ቤት ነፅ ተባለ

 

 

ጅዳ ውስጥ ከሁለት አመት በፊት ፈይሰልያ በተባለ አካባቢ የኢትዮጵያዊውን አባወራ ቤት ለመዝረፍ ሲመክር በተፈጠረ ግብግብ ነፍስ የጠፋው ኢትዮጵያዊ ኑረሁሴን ሀሰን ሙስ ጦፋ ከተከሰሰበት የግድያ ወንጄል ነጻ መሆኑ ታውቋል ። በመኖሪያ ቤቱ አገር ሰላም ብሎ ተቀምጦ እያለ ለዘረፋ ከመጡ ሳውዲ ወጣቶች ጋር ነበር የተጋጨው ። ዘራፊ ወጣቶች እሱን ወንድሞቹንና የቀሩትን ወንዶች በአንድ ክፍል በመዝጋት በቤቱ ያለውን ንብረት ከዘረፉ በኋላ ሚስቱን ሊደፍሩ ሲሞክሩ የተዘጋበትን ቤት ሰብሮ በመውጣት ከሳውዲ ወጣት ጋር ግብግብ የገጠመው ሁሴን ራሱን ለመከላከል ሳውዲው ወጣት ይዞት የነበረውን ስለት በመቀማት ሊገድለው እንደቻለ ለፍርድ ቤት አምኖ ነበር ።

ኢትዮጵያዊው ሁሴንን ከዚህ ቀደም ባቀረብኩት የማለዳ ወግ በሰጠን ቃለ ምልልስ ግድያ የፈጸመው ራሱ ለመከላከል መሆኑን በመግለጽ የሀገሩ መንግስት ተወካዮች ቀርበው ስለመብቱ መከራከር ባይችሉም ጉዳዩን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን አጫውቶን ነበር ። ከሳምንታት በፊት ጉዳዩን ለሁለት አመት ተኩል የመረመረው ከፍተኛ የሸሪያ ፍርድ ቤት ሁሴን ግድያውን ራሱን ለመከላከል ሲል መፈጸሙን በመግለጽ ከቀረበበት ወንጀል ነጻ እንዳለው በስልክ ባደረግነው ቃለ ምልልስ ግልጾልኛል ። አቅም ሲገቅድ ዝርዝሩን የጉዳዩ ባለቤት ሁሴን ሀሰን ያጫውቶኛል !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ