መንግስት ቤተክርስቲያን በማቃጠል ክርስቲያኑና ሙስሊሙመሐል መቃቃር ለመፍጠር አስቧል ተባለ!!

ድምፃችን ይሰማ
ዛሬ ከታማኝ ምንጮች የደረሱን መረጃዎች መንግስት በኢቲቪ
ያቀረበው ዶክመንተሪ ፊልም ባሰበው መልኩ ክርስቲያን
ወንድሞቻችንን ሙስሊሙ ላይ ማነሳሳት ባለመቻሉ ይህንኑ
ዐላማ ለማሳካት ሌላ ዘዴእንደቀየሰ ያሳያሉ፡፡ ሙስሊሙ
ተቃውሞ የሚወጣበትን ዕለት ጠብቆ በአቅራቢያ የሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን በማቃጠል (ምናልባትም የሙስሊም ምልክት
ባላቸው ሰዎች ሊሆን ይችላል) ክርስቲያኑና ሙስሊሙመሐል
መቃቃር ለመፍጠር ታስቧል፡፡ ይህን እርኩስና ያለፈበት
የከፋፍለህ ግዛ ዐላማ እንዳይሳካ ለማድረግ መጪው ጁሙዓ
በአንዋርመስጂድ ታስቦ የነበረው የተክቢራ ተቃውሞ በተክቢራ
መሆኑ ቀርቶ በዝምታ እንዲሆን ሰፊ ምክክር ተደርጎበት ተወስኗል፡፡ በመሰረቱ የደረሰብን ግፍና መከራ
በተክቢራጩኸንም የማይወጣልን መሆኑን የምንረዳ ቢሆንም
የመንግስትን እኩይ ዐላማ እንዳይሳካ ለማድረግና ቀኑ ፍጹም
የተረጋጋሆኖ እንዲያልፍ ከማሰብ አንጻር
በየክልልሉየታሰቡት የተክቢራ ተቃውሞዎች እንደተጠበቁ
ሆነው በአንዋር መስጂድ ግን ጁሙዓ ተቃውሟችንን በአስደንጋጭ ዝምታ እንገልጻን፡፡ ሁላችንም ለተፈጻሚነቱ
የተለመደውን ትብብር እንድናደርግና ላልሰሙት እንድናሰማ
እንጠይቃለን፡፡ ህዝብ ሰላም አስጠባቂ መንግስት ደግሞ
ሰላም አደፍራሽ የሆነበት አገር ግን ሰምታችሁ ታውቃላችሁ??
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular