መጅሊስ ሠላማዊ ትግሉን ለመበተን ግብረኃይል እያቋቋም ነው

የሚካሄደውን የሕዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል ለመበተን የሚያስችለውን ግብረ ኃይል እያደራጀ መሆኑ ተገለፀ፡፡ መጅሊሱ ዛሬ ጦርኃይሎች በሚገኘው ቅጥር ግቢው ከመዲናዋ የተለያዩ መስጂዶች ኢማሞች ጋር ባካሄደው ውይይት እንዳስታወቀው እየተጠናከረ የመጣውን የሕዝቡን ተቃውሞ ለመበተን የሚየስችል እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ባውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት የተለያዩ ኢማሞችና ዱዓቶች ሥራ መሰራቱን ለሬዲዮ ቢላል አስታውቀዋል፡፡ ለደህንነታችን እንደሰጋለን ያሉ አስተያየት ሰጪዎቻችን እንዲገልፁት የመጅሊሱን እንቅስቃሴና የስብሰባ አጀንዳ ግልፀኝነት እንደሚጎድለው አመልክተዋል፡፡ዛሬ ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ የሼህ አብደላ አልሃረሪ መፀገፎች መበተናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በስብሰባው በርካታ ወጣት ዳዒዎች፣ዑስታዞች እንዳይሳተፉ ታግደዋል፡፡ተሳታፊዎቹ የተመረጡት በመጅሊሱ አመራሮች መሆኑንም ታማኝ ገልጸዋል፡፡
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular