በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በቁርዓን ሽንት ቤት የተጠቀመው ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

አሰላምዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በቁርዓን ሽንት ቤት የተጠቀመው ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ ጉዳዩ እንዲህ ነው ከዛሬ 21 ቀናት በፊት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ አንባ ግቢ ጧት ሙስሊም ተማሪዎች ለሱብሂ ሰላት ሲንሱ ሽንት ቤት ውስጥ የቁረዓን ቅዳጆች በአይነምድር ተለውሰው ያገኛሉ፡፡ነግሩን በሚስጥር በመያዝ ጉዳዩን ለማጣራት ሥራቸውን ይጀምራሉ፡፡ክትትል ቢያደርጉም ምንም መረጃ አላገኙም፡፡ሁኔታውን በሚስጥር ቢይዙትም ከሶስት ቀን በኋላ ነገሩ ተደገመ፡፡አሁንም ግራ ተጋቡ፡፡አሁንም ከሶስት ቀን በኋላ ተደገመ፡፡ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ቢደርስም ተማሪዎቹ ስልት ቀየሱ፡፡ጉዳዩ የሚፈጸመው ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት በኋላ መሆኑን መረዳት በመቻላቸው ጥበቃቸውን አጠናክረው ቀጠሉ፡፡ ሰውየው ለአራተኛ ጊዜ ለመፈጸም እንደሚመጣ እርግጠኞች ስለነበሩ ሌሊቱን ዋርድያ ሆነው ማደር ጀመሩ፡፡ከአራት ቀናት ጥበቃ በኋላ በግምት 9፡45 አካባቢ አንድ አዲስ ፊት ከወደበር ብቅ አለ፡፡ሙስሊም ተማሪዎችም ጥግ ጥጋቸውን ይዘው ከታተሉት ጀመር፡፡ሰውየው ወደ ሽንት ቤቱ ቀጥ ብሎ ሲገባ ክትትሉን ቀጠሉ፡፡ከሽንት ቤት እስኪወጣ ድረስ በትግስት ከጠበቁት በኋላ ሰውየው ሲወጣ ተከታትለው ወደ ሽንት በቤት ሲገቡ የቁርዓን ቅዳጅ ያገኛሉ፡፡ተማሪዎችም የሰውየውን አድራሻ ለማወቅ ተከትለውት ነጎዱ፡፡ሰውየው ቀጥ ብሎ እዚያው አካባቢ ወዳለ አንድ ቤት ዘው ብሎ ይገባል፡፡ተማሪዎቹም የሰውየውን ማንነት ለማወቅ እዚያው አካባቢ ተቀምጠው አነጉ፡፡ሰውየው ሽንት የያዘ ፖፖ አውጥቶ ሲደፋ በማየታቸው የሰውየው ቤት መሆኑን ያረዳግጣሉ፡፡የሰውየውን ማንነት ለማወቅ ክትትላቸውን ቀጠሉ፡፡ሰውየው ልጁን ትምህርት ቤት ለማድረስ ሲሄድ ተከታተሉት፡፡ሰውየው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቴወድሮስ ካምፓስ ፕሮክተር መሆኑን አረጋገጡ፡፡ ተማሪዎቹ ውይይታቸውን ቀጠሉ፡፡ጉዳዩ ለዩኒቭረሲቲው ፕረዚደንት እንዲቀርብና እልባት እንዲገኝ ሀሳብ ቢቀርብም ሁኔታውን በትግስት መከታተልና ድርጊቱን የሚፈጽመውን ግለሰብ መያዝና ለፍርድ ማቅረብ እንደሚገባ ነገር ግን መጀመሪያ ሚስጥሩ ከወጣ ሰውየው ከድርጊቱ ሊቆጠብና ጉዳዩ ተደፋፍኖ ሊቀር ይችላል የሚለው ሀሳብ ገዢ ሆኖ የተገኘ በመሆኑ ጉዳዩን በትግስት መጠበቅ ጀመሩ፡፡ዱዓውም ቀጠለ፡፡ሚስጥሩ ጎንደር ከተማን ቀስ በቀስ ማዳረስ ጀመረ፡፡ሁሉም ዱዓውን ቀጠለ፡፡ታዲያ በ18 /07/04 ምሸት ላይ ሰውየው እንደለመደው ድርጊቱን ለመፈጸም እንደመጣ የጠረጠሩት ተማሪዎች ሰውየውን በቪዲዮ ለመቅረጽ ዝግጅታቸውን አጠናቀው መጠባበቅ ጀመሩ፡፡ ድርጊት ፈጻሚው እንደለመደው ድርጊቱን ሲፈጽም ቀረጹት፡፡ለመውጣት ቢሞክርም እጅ ከፍንጅ እንዲያዝ ተደረገ፡፡ አላሁ አክበር! የዛሬውን ውሎ ነገ አቀርባለሁ ሙስሊም ወንድማችሁ ነኝ ከጎንደር
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular