እንደ ካሮት እንደ እንቁላል ወይስ እንደ ቡና ?

አንዲት ወጣት ወደ እናቷ ጋር መጥታ በምሬትና በብሰጭት እንዲህ አለቻት”አልቻልኩም እማ በቃኝ ነገሮች ሁሉ እኔ በምፈልገው መንገድ እየተጓዙ አይደለም፤ችግሮች ተደራረቡብኝ፡አንዱን ችግር ሳቃል ሌላ ሁለት ችግር ይወለዳል፡ሁሉም ነገር ተሰፋ የሚያሰቆርጥ ነው እናም በቃኝ”ብላ ማልቀስ ስትጀምር እናቷ እያባበለች ይዛት ወደ ኩሽና ገባች ፡፡እሰቶቩን ትለኩስና በሶስት ድስት ውሀ ትጥድበታለች፡ከዚያም ካሮት እንቁላል እና የተቆላ ቡና አምጥታ ሶሰቱ ድስት ውሰጥ ለየብቻ ትከተዋለች፡፡ከ20 ደቂቃ በኃላ ውሀው መንተክተክ ጀመረ፡እናትም እሰቶቩን አጥፍታ ከድስቱ ውሰጥ ካሮቱን እንቁላሉን እና ቡናውን አውጥታ ሰሀን ላይ አሰቀመጠቻችው፡፡ከዛም ወደ ልጇ ዞራ እስኪ ካሮተን ንኪው አለቻት ፤ልጅ ሰትነካው ካሮቱ ለስልሶ ና ተልፈስፍሷል፡ከዛም እንቁላሉን ቅርፊቱን ላጪውና እስኪ ስበሪው አለቻት፡እንቁላሉ በጣም ጠንክሯል፡ከዛም ቡናው ቅመሽው አለቻት ፤ልጅም ፈገግ አለች የቡናው ማሪኪ ሽታና ጣዕም ያውዳልና፡፡እሺ ታዲያ ምን ማለት ነው ይዄ ብላ ጠየቀች? አናትም አየሽ ልጄ እነዚህ ሶስቱ ነገሮች አንድ አይነት ችግር ነው የተጋፈጡት ፤በውሀ መቀቀል ነገር ግን ለችግሩ የመለሱት ተለያየ መልኩ ነው፡ካሮቱን እይ መጀመሪያ ደረቅና ጠንካራ ነበር ነገር ግን በውሀ ከተቀቀለ በኃላ ለስላሳና ልፍሰፍስ ሆነ ፡እንቁላሉን ደግሞ ተመልከቺ መጀመሪያ ደካማና ተሰባሪ ነበር እንደውም በውስጡ ያለው እንዳይፈስ ያደረገው ቅርፊቱ ነበር፡ነገር ግን ከተቀቀለ በኃላ ጠንካራ ከመሆኑ በላይ ቅርፊቱን ልጠነው እንኳ ውስጡ ያለው አልፈሰሰም ፡ይህ ማለት ውስጡም በችግሩ የተነሳ በጣም ጠንክሯል ማለት ነው፡ቡናውን ደግሞ ተመልከቺው ጭራሽ እኮ የውሀውን ቀለም ቀየሩት ታዲያ ልጄ አንቺ የትኛው ነሽ ?ችግር በርሽን ሲያንኳኳ በምን መልኩ ነው የምትመልሺው? ካሮት ነሽ ጠንካራ መስለሽ ችግርና መከራ ሲያጋጥምሽ የምትልፈሰፈሽ ? ወይስ እንቁላል ነሽ ችግርና መከራ የሚያጠነክርሽ? ወይስ ደግሞ እንደ ቡናው ነሽ የሚቀቅለው ቡና ውሀ የቀየረው በተቀቀለ ቁጥር ማራኪ ጣዕሙና ማዕዛ የሚወጣው?በርግጥ እንደ ቡናው ከሆንሽ ችግሩ ሲበረታ አንቺ የተሻልሽ ሁነሽ ዙሪያሽን ትቀይሪዋለሽ? ችግሮች ሲደራረቡብሽ እራሰሽን ወደ ተሻለ ደረጃ ታሸጋግሪለሸ?መከራው ሲበዛ እንደ ካሮት እንደ እንቁላል ወይስ እንደ ቡና ትሆኛለሽ? የሚል ማራኪ ምክር መከረቻት እኔም እራሴን ጠየቅኩ ችግራ መከራ ሲበዛ እንዴት ነው የምመልሰው? ስጀምር ጠንካራ መስዬ ከዛም ችግሩ ሲጠነክር የምልፈሰፈሰ፡ወይስ ችግረ ውስጤን የሚጠነክረው?አልያም ከችገሩ በልጬ ችግሩን የማሸንፍ?ትላንት አያቶቼ በእምነታቻው የተነሳ ዛሬ እኔ ላይ ይደርስ ከነበረው ችግር ና መከራ በላይ ደርሶባቸዋል ግን እነሱ አልተልፈሰፈሱም ችግሩን ልቀውት ተገኝተው መከራን ድል አድርገውት ይሀው እምነታቸውን ለኔ አስረከቡኝ ፤መከራና ችግር ያልፋል ጠንካሮች ብቻ ያልፉታል አይደል የሚባለው፡የአጼዋቹ ማሰፈራሪያና ዛቻ እስራትና ግድያ መች በገራቸው አረ እንደው እምነቴን አትንኩብኝ ብለው በነቂስ ሰልፍ ወጥተው እንደነበርስ ዘነጋሁት እንዴ? በፍጹም በፍጹም አልረሳውም እኔም እንደ አያቴ በእምነቴ ጉዳይ የሚደርስብኝ ማሰፈራሪያና ዛቻ እስራትና ግድያ ሊበግረኝ አይችልም ፡፡ልክ እንደ ቡናው ችግርን ማሸነፍ ከአያቴ ተምሬያለውና አልበገረም፡፡በእምነቴ ላይ የሚደርሰው በደል ለመጣል ሆ …ብዬ ለመጣል ፍጹም ጠንካራ መስዬ ሳበቃ አሁን ችግሩ ሲበራታ መልፈስፈ ታዲያ ምን አመጣው?እስኪ እናንተንም ልጠይቃችሁ እንደ ካሮት እንደ እንቁላል ወይስ እንደ ቡና?መልሳችሁ ምንም ይሁን እኔ ግን እንደ ቡናው እሆናለው የአላህም እርዳታ ከኔ ጋር ነውና፡፡ አላህ ሆይ የአዩብን ትዕግስትን የኑህን ጥንካሬን የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ›ወ)ጽናት ትለግሰኝ ዘንድ እማጸንሀለው
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular