የኮሚቴዎቻችን ቤት ሲፈተሸ ከተከሰቱ አስደናቂ ነገሮች መሀል በጨረፍታ

የኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ቤት ሲፈተሽ ፖሊሶቹ አከራዮቹን ‹‹ለዐረብ እንዴት ታከራያለሽ?!›› አሏቸው፡፡ ‹‹አረ የሀበሻ ልጅ፡፡ ያውም ጠንቅቄ የማውቀው የጓደኛዬ ልጅ ነው!›› ብለው መለሱ፤ ባልቴቲቱ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ረዥም ክርክር ካደረጉ በኋላ የኡስታዝ አህመድ ፎቶ ተፈልጎ ኢትዮጲያዊ መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡ የሚያሳዝኑት ግን አከራይቱ ናቸው፡፡ ኡስታዙን (ዐረቡን) ስላከራዩት ይሁን እኛንጃ የሰባ አመቷ አዛውንት በውድቅት ለሊት ውጪ (ያውም በእንቅላል ፋብሪካ ብርድ እየተሰቃዩ) እንዲያድሩ ተደረጉ፡፡ (ጉድ ነው!) ኢትዮጲያዊ ሙስሊም መብት አይጠይቅም ነው ነገሩ ወይስ መብት መጠየቅ ዜግነት ያስነጥቃል?! 

ሌላ አጋጣሚ እንጨምር

ይህኛው የኮሚቴ አባል ባይሆንም ለመብቱ መከበር የሚታትር ኢትጲያዊ ነው፡፡ እርሱን ቤቱ ሄደው ሲፈልጉት አጡት፡፡ ከዚያም ‹‹ፖሊስ ሰንዝሮ አይመለስም!›› ብለው ይሁን እናቱን እና አባቱን ወሰዱ፡፡ እውነትም ፖሊስ ሰንዝሮ አይመለስም!
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular