al azhar university temariwoch le ethiopia muslim degafachewun geletsu

የአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኢትዮጲያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄዎች ድጋፋቸውን ገለፁ Details Category: International Hits: 2 አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 14/2004 በግብፅ የአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆኑ ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች መጅሊስን በመቃወምና አህባሽን በማውገዝ በሀገር ውስጥ እየተካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ አስታወቁ ፡፡ በካይሮ የሚገኙ ኢትዮጲያውያን ሙስሊም ማህበረሰብ አባላትና የአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዳስታወቁት በአወሊያ ህዝብ ንቅናቄ የተነሱትን የመብት ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ ይደግፏቸዋል፡፡ በአወሊያ ጎልተው የወጡትን የህዝብ ጥያቄዎች የነርሱም ጥያቄዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ የስምምነት ፊርማ/ፒቲሽን/ እያሰባሰቡ መሆኑንም ለሬዲዮ ቢላል በላኩት መግለጫ አመልክተዋል፡፡
Be the first to comment

Latest Articles

Most Popular