Allahu akber Allahu akber

አላሁ አክበር!!! አላሁ አክበር!!! በዛሬዉ እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በድል በትግል አዳራሽ የኢህአዴግ ሙስሊም አባለት ከክፍለ ከተማዉ የኢህአዲግ ዎና ስራ አሰፈፃሚ ጋር ዉይይት አደረጉ::በዉይይቱ መጀመሪያ ላይ በአወልያ እየተካሄደ ስላለዉ ሰላማዊ እንቅስቃሴን በመተቸት ገለፃ የተደረገ ሲሆን ለታዳሚያን መድረኩ ከተከፈተ ቡሀላ ግን አስገራሚ ትእይንቶች የታየበት እንደነበር ተገልፆል::በዛሬዉ ስብሰባ ከፍተኛ ተቃዉሞአቸዉን ሲያሰሙ የነበሩት እናቶች እና አባቶች ነበሩ::አንዲት እናት እንባ እየተናነቃት ያቀረበችዉ የተቃሞ ንግግር በስብሰባዉ የተገኘዉን ህዝብ በጣም የነካ እንደነበር ተገለፆል:: ከተሰብሳቢዎች የተነሱት ነጥቦች መካከል መጅሊስ አይወክለንም! ምርጫም ማካሄድ አይችልም! አስመራጮችን መምረጥ ያለብን እኛ ሙስሊሞች ነን!መንግስት ወሀብያ ሱፊያ የሚባሉ ጉዳዬች ዉስጥ መግባቱ ተገቢ አይደለም! የአወልያ የሙስሊሞች ሀብት ነዉ በመሆኑም ለሙስሊሙ ሊመለስ ይገባዎል የሚሉ ወሳይ ነጥቦችን የኢህአዴግ ሙስሊም አባላት ያነሱ ሲሆን የአዲስ ክ/ከተማ የኢህአዴግ ዎና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መስፍን መንግስቱ የተነሱት ጥያቄዎች በሙላ ተገቢ መሆናቸዉን ያመኑ ሲሆን መንግስት በማንኛዉም ሁኔታ ከህዝብ ጋር በመሆኑ የህዝቡን ጥያቄ ይመልሳል:: ህዝበ ሙስሊሙ ነፃ በሆነ መልኩ መሪዎቹን መምረጥ አለበት:: አስመራጮቹንም መምረጥ ያለበት ህዝበ ሙስሊሙ ብቻ ነዉ:: መንግስት የህዝበ ሙስሊሙ ዉክልና ከሌለዉ አካል ጋር ከንግዲህ አብሮ አይሰራም በማለት የስብሰባዉ ተሳታፊዎቹን ሀሳብ በመጋራት ስብሰባዉ በህዝበ ሙስሊሙ ድል አድራጊነት በድል ተፈፅሟል::አላሁአክበርby abu dawd
Be the first to comment

Latest Articles

Most Popular