ye alquds gazeta wana azegaje serawun leqeqe alqudsm yetesasate zena yawetal ale

የአልቁዱስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ስራን ለቀቀ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል የካቲት በማሪያ አልቅዱስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥር በየሳምንቱ ጁምዓ ለንባብ የምትበቃው የአል-ቁድስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሥራውን ማቆሙን አስታወቀ፡፡ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ አቶ መሐመድ ዳውድ ዛሬ ለሬዲዮ ቢላል እንዳስታወቁት ሥራውን በፈቃዱ ሊለቅ የቻለው ጋዜጣው በተከታታይ እያወጣ ያለውን የተሳሳተ መረጃ በመቃወም ነው፡፡ በጋዜጣው ላይ ሲወጡ የነበሩት ዘገባዎች ሆኑ መጣጥፎች በተመለከተ ምንም አይነት እውቅና እንደሌለው የጠቀሰው የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ በስሙ ለተፈጠረው ስህተት ሕዝበ ሙስሊሙን ይቅርታ ጠይቋል፡፡ በጋዜጣዋ ላይ ካለፉት 7 ወራት በላይ በዋና አዘጋጅነት ስሙ ቢጠቀስም የዋና አዘጋጅነት ሚና እዳልነበረው አቶ መሀመድ አስታውቀዋል፡፡ የአል-ቁድስ ጋዜጣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወቅታዊ የህዝበ ሙስሊሙን ጉዳዮች ላይ የተሳሳቱና ምንጫቸው በትክክል ያልተጠቀሱ ከወገንተኝነት ያልፀዱ ዘገባዎችን በተከታታይ በማውጣቱ በህዝበ ሙስሊሙ በሰፊው ሲወገዝ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
Be the first to comment

Latest Articles

Most Popular