BILAL TUBE NEWS AMHARIC

  • Strange News from Mekelle!አስገራሚ ዜና ከመቀሌ!!

    Strange News from Mekelle!
    Police in Mekelle is reported to have conducting a house-to-house query targeting Muslim residents asking whether they have young family member, whether they have long beards, whether they are followers of the "new" or "old" deen.
    አስገራሚ ዜና ከመቀሌ!!
    የመቀሌ ፖሊስ የቤት ለቤት አሰሳ እያደረገ መሆኑ ተሰማ! አሰሳው በሙስሊም ቤቶች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ ከሚጠይቋቸው ጥያቄዎች መሃከል፦
    በቤት ውስጥ ወጣት አለ ወይ? ካለስ ባለ ረዥም ፂም ነው ወይ?
    በቤት ውስጥ ያሉት ሰዎችስ "አዲሱ" እምነት ተከታዮች ናቸው ወይስ "የነባሩ"?

    Abu Huzeifa
    Read more
  • “አንድ ሀገር ብዙ ኃይማኖት” በሚል ርዕስ የተላለፈው ዘጋቢ ፊልም እንዳበሳጫቸው በቀረፃው የተሳተፉ ምሁራን ገለፁ


    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሰኔ 26/04

              ትላንት ምሽት “አንድ ሃገር ብዙ ሃይማኖት” በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተላለፈው ፕሮግራም ለሀሰት ፕሮፖጋንዳ እንዲመች ተደርጎ መቅረቡ እንዳበሳጫቸው በቀረፃ የተሳተፉ ኡስታዝ ሃሰን ታጁና አህመዲን ጀበል ገለፁ፡፡

              ኡስታዝ ሃሰን ታጁ የፕሮግራሙን መተላለፍ ተከትሎ ዛሬ በሰጡት አስተያየት ከፕሮግራሙ አጠቃላይ ይዘት ሶስት ዓላማዎችን መገንዘብ ችለዋል፡፡

     

              የመጀመሪያው በኢትዮጵያ አክራሪነት የሚለውን ለማሳየት ፣ሁለተኛ ኃይማኖታዊ ተቋሞች ላይ ጥያቄ የሚያነሱና የሚቃወሙ አክራሪዎች መሆናቸውንና የአክራሪነት መገለጫ መሆኑን የማሳየት ዓላማ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

    በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ በአወሊያ እየተካሄደ ያለው ሰላማዊ የሙስሊሞች ተቃውሞ ህገ-ወጥ እንደሆነ ለማሳየት መሆኑን እንደታዘቡ ነው ኡስታዝ ሀሰን ተጁ በፌስ ቡክ የሰጡት አስተያየት የሚያመለክተው፡፡

    ለኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛም ስልክ በመደወል የተሰራው ፕሮግራም እጅግ አሳፋሪና ከአንድ ሙያተኛ የማይጠበቅ መሆኑን እንደገለፁለት ጋዜጠኛውም ከቁጥጥሩ ውጪ የሆነ ነገር እንዳለበት መናገሩን አስታውቀዋል፡፡

              ከአራት ወራት በፊት ስለኃይማኖት መቻቻል በቴሌቭዥን ጣቢያው ጋዜጠኞች ቃለ ምልልስ መስጠታቸውን ያስታወሱት ኡስታዝ ሐሰን ታጁ፡-ለ2፡30 የሰጡት ማብራሪያ ለአምስት ደቂቃ ብቻ ተቀንጭቦ ለፕሮፖጋንዳ እንዲመች ሆኖ መቅረቡ እንዳሳዘናቸው ጠቅሰዋል፡፡

              በተመሳሳይ ከመካነ ሰላም የተጠየቀችውና ሁለት ኒቃብ የለበሱ እህቶች የሰጡት አስተያየት ከ3 ሰዓት በላይ የተቀረፀ ቢሆንም የተላለፈው ከሁለት ደቂቃ እንደማይበልጥ አመልክተዋል፡፡

              ባለፈው የካቲት ወር ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና መቻቻል ዘጋቢ ፊልም ለመስራት ሀሳብህን እናካት በሚል ከኢቲቪ ጋዜጠኞች ጋር ቀጠሮ ይዞ በመኖሪያ ቤቱ የ2 ሰዓት ከሩብ መቀረፁን የተናገረው ኢስላማዊ ታሪክ ፀሀፊው አህመዲን ጀበል ነው ፡፡

    ከመብት ጋር በተያያዘ የተነሱትን ጥያቄዎች ከአክራሪነት ጋር ለማያያዝ መሞከሩ ግርምትን ጭሮብኛል ያለው አህመዲን ጀበል እውነቱን ካልተነጋገርን የእውነት መቻቻል ይመጣልን ሲልም ጠይቋል፡፡

    Read more
  • USTAZ ABU BAKER SAID I have been detained by traffic police Around 6:00 o'clock

    Brothers and sisters, I have been detained by traffic police Around 6:00 o'clock till 6:40 on the main bole road. They told Me that an arrest warrant had been issued to arrest me but the authority that has issued the warrant was not known. So they have released me as it was a vague case. Rest assured that our peaceful struggle will not be hindered in any case and the committee is ready to pay any sacrifice to stand by the legitimate request of the Ethiopian muslims. Abuber Ahmed አሰላሙ አለይኩም ወ ወ ዛሬ ከቀኑ 6:00 ሰአት እስከ 6:40 አካባቢ ቦሌ መንገድ ላይ በበላይ አካል ትእዛዝ በፖሊስ ተይዜ ፖሊስ ጣቢያ ቀርቤ የነበረ ቢሆንም ትእዛዙን ማን እንዳስተላለፈ ስላልታወቀ ወዲያው ተለቅቄአለሁ:: እኛ የኮሚቴው አባላት ህጋዊውን የኢትዩጵያዊያን ሙስሊሞች ጥያቄ ከዳር ለማድረስ ማንኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችንን ከወዲሁ ለማረጋገጥ እንወዳለን:: ህዝበ ሙስሊሙም በተመሣሣይ ክስተቶች ባለመደናገጥ ህጋዊ መብቱን ለማስከበር ከበፊቱ በበለጠ ቆርጦ እንዲነሣ ለማሣሠብ እንወዳለን:: አቡበክር አህመድ Read more
  • TRYING TO SHUT DOWN TV AFRICA BROADCASTING ዘመቻ ቲቪ አፍሪካን ለማዘጋት !!!

    ዘመቻ ቲቪ አፍሪካ !

    ከወራት በስተፊት በተላለፈለት ቀጭን ትዕዛዝ መሠረት አህመዲን አብዱላሂ ቲቪ አፍሪካ መቻቻልን እንደሚያጠፋ እና ለሀገር አደጋ እንደሆነ በመግለፅ ደብዳቤ ይፅፋል፡፡ ይህንኑ ደብዳቤ በማያያዝም አንድ የኮማንደር ማዕረግ ያላቸው ግለሰብ መጅሊሱ በፃፈልን መሠረት በማለት ለአረብ ሳትና ለቲቪ አፍሪካ TV Africa ይዘጋልን ሲሉ ደብዳቤ ፃፉ፡፡ ደብዳቤው የተፃፈላቸው አካላትም በመገረም የምትሉትን ነገር የሚያሳይ (ማለትም መቻቻልን እንዳጠፋና ግጭት እንደፈጠረ) ከፕሮግራሙ ላይ ቀድታችሁ በአንድ ወር ውስጥ አድርሱን አሏቸው፡፡ ይህ የሆነው አምና ረመዷን ላይ ነበር፡፡ ቲቪ አፍሪካ እንዲዘጋ ጥያቄ ያቀረቡት አካላት ከብዙ ቆይታ በኋላም ቢሆን የሚያቀርቡት አላገኙም፡፡ ሆኖም እነኚሁ አካላት ዙልሂጃ (ከ ሥምንት ወራት በፊት) ላይ ደውለው ጉዳዩን (ይዘጋልን የሚለውን) ምን ላይ አደረሳችሁት ሲሉ ቢጠይቁም አምጡ ሲባል ምንም ነገር አላመጣችሁም ስለዚህ ምንም ነገር ማድረግ አንችልም በማለት ይመልሷቸዋል፡፡ ከዚህ አልፎም ኢሳት ላይ እርምጃ ወስዳችሁ እንደዘጋችሁት ቲቪ አፍሪካን ለመዝጋት ብትሞክሩ የናንተን አረብ ሳት ላይ ያለውን ሁሉንም ጣቢያ እናጠፈዋለን በሚል ሁኔታ ነበር ጉዳዩ የተቋረጠው፡፡ አሁን ደግሞ ሁለተኛ ዙር ሙከራ ማድረጋቸው ሳይሆን አይቀርም የሚለተለውን ጆሯችን ሰማ፡፡

    ሪያድ ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጫና ፈጥሮ ቲቪ አፍሪካነን ለማዘጋት ባለፈው እና በዚህ ሣምንት አረብ ሳት ቢሮ ሪያድ ላይ ሲመላለሱ ነበር ፡፡ የነኚህ ሰዎች ፍላጎትና ዓላማ ቲቪ አፍሪካ ኢ/ያ ውስጥ ችግር እየፈጠረብን ነውና ዝጉልን ማለት ሲሆን፣ከሶስት ወር በፊትም ልዑካን በመላክ ማን በገንዘብ እንሚደጉመው እና አልፎም ሊዘጋ የሚችልበትን መንገድ ለመፈለግ ልዑካኖቻቸውን ወደካርቱም ልከው እንደነበር ታውቋል፡፡ ሪያድ አካባቢ ከሚገኘው ቢሮ የተገኘውም መረጃ ይህንኑ የሚያመለክት ሲሆን ጥረታቸው በሙሉ ቲቪ አፍሪካን ማዘጋት ነው፡፡ Read more
  • ሽንኩርት እና ሀይላንድ ዉሀ በደረሰኝ መግዛት መግዛት ነበረባቹ << የኩታበር ወረዳ ፓሊስ

    በአማራ ክልል ከደሴ ከተማ 20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘዉ ኩታበር ወረዳ የፊታችን ቅዳሜ ታላቅ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ለማዘጋጀት የወረዳዉ ሙስሊሞች እየተዘጋጁ መሆናቸዉ ተገለፀ:: ሆኖም የኩታበር ወረዳ ሙስሊሞች ለፕሮግራሙ መሳካት ደፉ ቀና እያሉ በሚገኝበት ወቅት ለዝግጅቱ የሚሆን ሽንኩርት,ሀይላንድ ዉሀ እና እንዲሁም የተለያዩ እህሎችን ከገበያ ገዝተዉ ሲመለሱ መንገድ ላይ ፓሊስ ይዞአቸዉ የገዛችሁት ሽንኩርት,ሀይላንድ ዉሀ እና እህሉ ደረሰኝ የለዉም በማለት ፓሊስ የተገዛዉን ዕቃ በሙላ እንደያዘባቸዉ የወረዳዉ ሙስሊሞች አስታዉቁ:: የወረዳዉ ሙስሊሞች እንዳስታወቁት የገዙት ዕቃ የተያዘባቸዉ ሆን ተብሎ ፕሮግራሙን ለማጨናገፍ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ሽንኩርት በደረሰኝ መግዛት ነበረባቹ መባላቸዉ እንዳስገረማቸዉ ገልፀዎል:: በተመሳሳይም ባለፈዉ ሳምንት በደሴ ከተማበተካሄደዉ ታላቅ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ላይም የደሴ ሙስሊሞች ለፕሮግራሙ የሚሆን እንጀራ ለእንጀራ ጋጋሪዎች እንዲያዘጋጁ ቀብድ ከፍለዉ የደሴ ከተማ ፓሊስ እንጀራ ጋጋሪዎቹን በማስፈራራት እንጀራዉን እንዳይጋግሩ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን የደሴ ከተማ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ይህንን ሲሰሙ በአንድነት በመሆን ለፕሮግራሙ ከሚያስፈልገዉ እንጀራ በላይ ከየቤታቸዉ በማምጣት ፕሮግራሙን ለማሰናከል የተደረገዉን ጥረት ማክሸፉቸዉ የሚታወስ ነዉ:: የኩታበር ወረዳ ሙስሊሞችን አላህ ይርዳቸዉ!!! Read more
  • zare Mengest ke hezbe muslimu gar baderegew sebseba kefetegna teqawmo getemewu


    "አላሁ አክበር"

    መንግስት ምርጫው የሚካሄደው ወረዳ እንሆነና የሚፈጸመው በመጅሊስ መተዳደሪያ ደንብ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል:: ህገ ደንቡ ችግር ቢኖርበትም እንኳን እንዲቀየር አናደርግም ምክኒያቱም በበሃይማኖት "ጣልቃh" ስለማንገባ!

    ህዝበ ሙስሊሙም በርካታ ሃሳቦችን ያነሳ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው::

    ሙስሊሙ ህዝብ በወረዳ ለሚካሄድ ምርጫ ላይ እምነት የለነም! አንሳተፍም!
    ምርጫውን በመጅሊስ ህገ ደንjjብ ማካሄድ ፈጽሞ አይቻልም! ህገደንቡ ችግር አለበት!
    መጅሊስም የመጅሊስም ህገ ደንብም ሀገ ወጥ ናችው!
    ምርጫን በተመለከተ ለኮሚቴዎቻችን ይገለጽ!
    በሙስሊሙ ላይ እየደረሱ ያሉ የማሸማቀቅና ስም የማጥፋት ስራዎች ይቁሙ!
    እስልምናችን አንድ ነው "ነባር" አዲስ የሚባል የለውም! አትከፋፍሉን!

    በዛሬው እለት የሙስሊሙን ድምጽ ላሰሙት ወንድም እህቶቻችን "አላሁ አክበር" በማለት ደስታችንን እንግለጽላችው!

    "አላሁ አክበር"

    yeh be endih endale

    በዛሬው እለት እሁድ በአዲስ ከ/ክ /ከተማ ወረዳ 6 በሚገኘው ስብሰባ ተካሄዶ ነበር ስብሰባው ገና ሊጀመር ሲል ከመንግስት አካላት የመጡት እንዲህ ሲሉ ገለፁ ህዝቦ በጣም ብዙ ስለሁነ አዳራሹ ስለማይበቃቹ ሊላ አዳራሽ ተዘጋጅቱላችሃል ሲሉ ህዝቦ ግን እንዲህ ሲል ገለፁ እኛ መሬት ላይ ቢሁንም ብለው ቁጭ አሉ የመንግስት አካላቱች ግን አይ አይሁንም ሁላችሁም በተረጋጋ መንፈስ መቀመጥ na ሀሳባችሁም እንድትገልፁ ስለሚረዳ ለሁለት መከፈል አለበት ብለው ግግም አሉ ህዝቦም እንዲ አለ እኛ መሹራ እናድርግና እንወስናለን እስከዛ እናንተ ውጡልን አሉ የመንግስት አካላት እንዲህ ሲሉ ገለፁ ይሂ ስብሰባ መንግስት ይዘጋጀው ስለሁነ አንወጣም አሉ ከዛ አባላቱች በቃ ግማሾቻችን እንውጣ ውጪ እንሁን ተባባlawe ውጪ watu ውጪ ከወጡ ቡሀላ በእልህ ለምን አንሰበሰብም ብለው ወደ ሁለተኛ አዳራሽ ገቦ አብዛኛዎቹ ወጣቶች ነበሩ አዳራሽ ውስጥ ገቡ ከዛ የመንግስት አካላቱች መጡና ጀመሩ በጣም የሚገርመው በዚህ ስብሰባ ላይ የመጅሊስ አመራሮችን ምርጫ አስመልክቱ መንግስት የማይሻር የማይለወጥ የሚመስለውን አቇሙን ለአባላላቶቹ አስረግጦ ነው የጀመሩት መንግስት የመጅሊስ ምርጫ መካhiድ ያለበት በየቀበሌው ብቻ መሆን እንዳለበት ምርጫውን የሚያስፈፅመው የመጅሊስ አካላት ብቻ መሆናቸውን ለአባላቱ ገለፁ አባላቱም በበኩላቸው በከፍተኛ ሁኔታ የተለመደውን ተቃውአቸውን አሰምተው መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ ካልገባ ስለ ሀይማኖት መሪ ምርጫ ምን አገባውና ነው እኛን የሚሰበስበን እንደውም እየዋኘበት ያገኛ ስለዚ taleqa magebatune ማቁም አለበት እያሉ አዳራሹን በአንድ እግር በተክቢር ቀወጡት ጥለውም ወጡ ከዛ የመጀመርያው አዳራሽ ህዝbu ገባ እነሱ ደሙ ስብሰባ እያdaረጉ ነበር ከዛ እነሱንም እንዲ ወጡ እረግጠው እንዲወጡ ተደረገ ሁሉም ተበታተኑ መንግስት ምንም ሊሳካለት አልቻለም ወደ ፌትም አይሳካለትም አሏሁ አክበር
    በወረዳ 10 እየተደረገ ባለው ስብሰባ ሙስሊም ህብረተሰብ አወያዮችን አፍ በማስያዝ ግራ አጋብቶዋቸዋል!! መጀመሪያም ግራ የገባቸው ቢሆንም !!ስብሰባው እንደቀጠለው ነው ተሰብሳቢው በአንድ ድምፅ መንግስት ጣልቃ መግባቱን' ያስቀመጥናቸው የምርጫ መስፈርቶች ባልተሟሉበት ሁኔታ የሚደረግ ምርጫን እንደማይቀበል . ከወከልናቸው ሰዎች ሌላ የማንመራና መወያየቱን አስፈላጊ አለመሆኑን. ወዘተ ስብሰባው እንደቀጠለ ነው የአካባቢያችሁን አህዋል ፖስትአድርጉ ወላሁ አእለም፧፧!!!
    Read more
  • የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መሪዎችን ለመምረጥ ዝግጅት እያደረጉ ነው

    የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መሪዎችን ለመምረጥ ዝግጅት እያደረጉ ነው ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሙስሊሞቹ መንግስት በየቀበሌው ለማድረግ የሰበውን የመጅሊስ ምርጫ እንደማይቀበሉትና ምርጫውን በራሳቸው መንገድ በመስኪዶች ውስጥ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ሙስሊሞቹ በራሳቸው መንገድ ተጉዘው የመጅሊስ አባላትን የሚመርጡ ከሆነ፣ በመንግስት ተደግፈው ወደ ስልጣን ከሚመጡት የመጅሊስ አባላት ጋር ውዝግብ የሚፈጠር ይሆናል። መንግስት የመጅሊስ አባላትን ለማስመረጥ የሚያደርገው ጥረት ሙስሊሞችን እያስቆጣ መምጣቱንም ዘጋቢአችን ከአዲስ አበባ ገልጧል። በመንግስትና በሙስሊሞች መካከል ያለው ውዝግብ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎም የመንግስት የደህንነት ሀይሎች በእንቅስቃሴው መሪዎች ላይ የማስፈራራት ዘመቻ ከፍተዋል። ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ጊዜያዊ ኮሚቴ በመንግሥት የደህንነት ሰዎች ከበባ ውስጥ መግባታቸውን በመግለጥ እነሱ ቢታሰሩ እንኳ ህዝበ ሙስሊሙ ሰዋዊ እና ሕገ-መንግሥታዊ መብቱን ለማስከበር ተተኪ የኮሚቴ አባላትን እንዲመርጥ አሳስበዋል፡፡ በአወሊያ መስኪድ ከአምስት ወር በፊት የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮሚቴ ሰሞኑን በሲዲ በበተነው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጸው የህዝበ ሙስሊሙ ሠላማዊ የመብት ጥያቄ ወደ ፊት መቀጠል እንጂ በመንግሥት አሻጥር ወደ ኋላ መቀልበስ የለበትም ብለዋል፡፡ ለዚህም ህዝበ ሙስሊሙ ከወዲሁ የመብት ጥያቄውን ሊያስቀጥሉለት የሚችሉ አዳዲስ የኮሚቴ አባላትን በመጪው ዓርብ በየመስኪዶቹ እንዲመርጡ ያሳሰበ ሲሆን ተግባራዊ ለማድረግም በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡ ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ እንደተመለከተው በአዲስ አበባ በሚገኙ መስኪዶች የመብት ጥያቄውን ሊያስቀጥሉ የሚችሉ አቅጣጫ መሪዎችንና የአዲስ አበባ እና የክልል የእስልምና ምክር ቤት የ/መጅሊስ/ አመራሮችን ለመምረጥ የሚያስችሉ የአስመራጭ ኮሚቴ ለማዋቀርና እጩ ተመራጮችን ለመመልመል በዝግጅት ላይ ሲሆኑ በመጪው ዓርብ ተግባራዊ ይደረጋል በማለት ገልጸዋል፡፡ በአንፃሩ የኢህአዴግ መንግሥት የአዲስ አበባ እስልምና ምክር ቤት /መጅሊስ/ ምርጫን በቀበሌና በወረዳ መዋቅር በመንግሥት ባጀት ለማከናወን በመጪው ሰኔ 13 እስከ 15 2004 ዓ.ም በዑላማዎች ምክር ቤት በኩል ለማስፈጸም የራሱን ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡ ይህንን የመስኪድ ምርጫ ለማስቀረት ነው ሰሞኑን የደህንነት ኃይሎች የኮሚቴ አባላቶች ላይ ከበባና ክትትላቸው ያጠበቁት ሲሉ አንድ የኮሚቴ አባል ለዘጋቢያችን አስረድተዋል፡፡ በኮሚቴው ላይ የሚካሄደው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻም ተጠናክሮ ቀጥሎአል። አዲስ ዘመንን የመሳሰሉ በህዝብ ግብር የሚተዳዳሩት ጋዜጦች የሙስሊሙ መሪዎች ከግንቦት7 እና በውጭ አገር ከመኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት አባቶች ጋር ቁርኝት እንዳለቸው የሚገልጡ ጽሁፎችን ይዘው እየወጡ ነው። የሙስሊም መሪዎችን ከግንቦት7 ጋር ለማያያዝ የተፈለገው ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላቸው በማለት በአሸብሪነት ከሶ ለመምታት የታቀደው እቅድ፣ በህዝብ ዘንድ ድጋፍ አያገኝም በማለት መሆኑን አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የሙስሊም ጋዜጣ አዘጋጅ ገልጠዋል። ታዋቂዎችን የሙስሊሙን አመራሮች ከአልቃይዳ ወይም ከሌሎች የእስልምና ድርጅቶች ጋር አያይዞ መፈረጅ በአለማቀፍም ሆነ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነትን የሚያገኝ ባለመሆኑ፣ በፓርላማው አሸባሪ የሚል ስም የተሰጠውን ግንቦት7ትን ስም በመጥቀስ መሪዎችን ለመምታት መታቀዱን በመንግስት ጋዜጦች የሚወጡ ጽሁፎች ያሳያሉ ብሎዋል። Read more
  • ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለመረጣቸዉ ኮሚቴዎች ሂወቱንም አሳልፎ በመስጠት ጥላ ከለላ እንደሚሆናቸዉ ገለፀ !!

    የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ በኮሚቴዉ ላይ ማንኛዉም አይነት ጥቃት ቢደርስ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ ሊያስኬዱ የሚችሉ ተተኪ ኮሚቴዎችእንዲመርጥ ያቀረበዉ ሀሳብ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ በከፍተኛ ቁጭት ተቃዉሞ እየገጠመዉ ነዉ:: ህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴዎቻችንን መንካት እና ማጥቃት ሙስሊሙን በሙሉ ማጥቃት በመሆኑ አንዳች ነገር ቢደርስባቸዉ ህዝቡ በሙላ ከለላ እንደሚሆናቸዉ እየገለፀ ይገኛል:: ህዝበ ሙስሊሙ መርጧቸዉ እንጂ ምረጡን ብለዉ እንዳልሆነ እየታወቀ ኮሚቴዉን ማብጠልጠል ሙስሊሙን መናቅ መሆኑም እየተነገረገ ነዉ:: ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለመረጣቸዉ ኮሚቴዎች ሂወቱንም አሳልፎ በመስጠት ጥላ ከለላ እንደሚሆናቸዉ ነዉ እየገለፀ ያለዉ:: አዲስ ተተኪ ኮሚቴ መምረጥ ህዝቡ ለኮሚቴዉ እያሳየ ያለዉን ታዣዥነት እና መከታነት እንደሚጋርደዉ በመግለፅ ማንም አካል ኮሚቴዎቹን ቢተናኮል እስከ ሂወት ፍፃሜያቸዉ እንደሚታገሉ ነዉ እየገለፁ ያሉት :: በመሆኑም ህዝበ ሙስሊሙ ለኮሚቴዎቹ ያለዉን ድጋፍና መከታነት ከመቼዉም ጊዜበላይ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበት ነዉ እየተገለፀ ያለዉ:: Read more
  • አሳዛኝ የግፍ ዜና>እህታችን ፍርዶስ በ ዶ/ር ሽፈራዉ የድህንነት ሀይሎች በደርሰባት የ ኤሌክትሪክ ሾክ እና ድብደባ ከዚህ አልም በ ሞት ተለየች

    አሳዛኝ የግፍ ዜና ኢናሊላሂወኢና ኢለይሂ ራጂኡን በሴት ሙስሊሞች ላይ የሚደረሰዉ ግፍና መከራ እንደቀጠለ ነዉ:: ይህም የግፍ ዜና ምንጮቻችን እንደዘገቡልን እናቀርበዎል:: ጉዳዩ እንደሚከተለዉ ነዉ በቅርቡ የፌደራል ጉዳዮች ከየክፍለ ከተማዉ የተመረጡ ሰዎችን በመጥራ ስብሰባ አካሂዶ ነበር:: በዚህም ስብሰባ ላይ ከኮልፌ ክ/ከተማ ሶስት ሰዎች የተሳተፍ ሲሆን ሁለት ወንድ እና አንዲት ሴት ይገኙበታል:: በዚህ ስብሰባ ላይ የኮልፌ ክ/ከተማ ነዎሪ የሆነችዉ ፍርዶስ የተባለች እህታችን ትገኝበት ነበር:: በስብሰባዉ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራዉ ተገኝተዉ ስብሰባዉን አካሂደዉ እንደነበር ምንጮች ገልፀዎል:: በስብሰባዉም ላይ ዶ/ር ሽፈራዉ እጅግ አፀያፊና ድንበር ያለፍ ንግግሮችን በህዝበ ሙስሊሙ በተመረጡት ኮሚቴዎች ላይ በመናገራቸዉ ይህንን የሰዉየዉን ዘለፉና ስም ማጥፉት መሸከም እና መታገስ ያቃታት እህታችን ፍርዶስ ዶ/ር ሽፈራዉ ለተናገረዉ ንግግር እልህ በተሞላበት ቃል ተቃዉሞአን በመግለፅ "ዶ/ር ሽፈራዉ ሴት የሴት ልጅ ነህ" በማለት የስብሰባ አዳራሹን ጥላ ወታለች:: ከአዳራሹ ወታ ወደግል መኪናዎ(የመኪናዎ ስም ቶዬታ ቪትዝ ነዉ) በማምራት ወደ መጣችበት ለመሄድ እንቅስቃሴ ስትጀምር በሁለት ላንድክሩዘር መኪና ደህንነቶች ተከትለዉ ያስቆሟትና አፍነዉ እሷንም መኪናዎንም ይዘዎት የሰወራሉ:: ከዚ ቡሀላ ነበር እህታችን ፍርዶስ ላይ ይህንን ኢ ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙባት:: እህታችን ፍርዶስን ያለምንም እርህራሄ በኤሌክትሪክ ሾክ አቃጠሏት:: ወድያዉኑ እህታችን መናገርም መንቀሳቀስም አቆመች::ይህንን ኢ ሰብአዊ ድርጊት ከፈፀሙባት ቡሀላ መኪናዎን እና እሷን መኗሪያ ቤቷ በር ላይ ጥለዎት ሄዱ::ቤተሰቧ እጅግ በመደናገጥ ልጃቸዉን ለመታደግ ጥረታቸዉን ተያያዙት:: የፍርዶስ አባት የልጁን ሂወት ለመታደግ ለህክምና በፍጥነት ወደ ዉጪ ሀገር (ሳኡዲ አረቢያ) ይዟት ይሄዳል:: ነገር ግን በኤሌክትሪክ ሾክ ከጥቅም ዉጪ ባደረጉዎት ደህንነቶች ምክንያት የአላህ ዉሳኔ ሆነና ፍርዶስ ለህክምና በሄደችበት ይህንን መራራ ስቃይ ተገላግላ ወደ አኼራ ነጎደች:: ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን! ይህ ሁላ ግፍ ሳይበቃ ይህንን የፈፀሙትን ግፍ እንዳይሰማባቸዉ ለማድረግ ወላጅ እናቷን አፍነዉ ወስደዉ እስካሁን ድረስ እናቷ የደረሱበት አልታወቀም:: እንደምታስታዉሱት በቅርቡም በአንዲት የጃዕፈር መስጂድ ጀምአ አባል በሆነች እህታችን ላይ ተመሳሳይ አፈና አካሂደዉ አንድም ሰዉነቷን ሳያስቀሩ እራሷን ስታ እስክትወድቅ ድረስ በመደብደብ አዉራ መንገድ ላይ ጥለዎት ሄደዉ እስካሁን አልጋ ላይ እንደሆነች የሚታወስ ነዉ:: ኧረ ያ አላህ መከራችን ይብቃቹ በለን:: በሙስሊሞች ላይ የሚደርሰዉን ግፍና መከራ ላልሰሙት እናሰማ! ሁሌም በዳይ እንደበደለ አይቀርም! የእጁን ያገኛል ኢንሻላህ! ይህንን ጉዳይ እስከመጨረሻዉ በመከታተል የተደረሰበትን እናሳዉቃለን:: እስከዛዉ ይህንን የመንግስት አካላት እየፈፀሙ ያሉትን ግፍና በደል ላልሰሙት በማሰማት እና እህታችንንም አላህ ጀነት እንዲያስገባልን በዱአ እንለምነዉ:: Read more
  • የጎንደር ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ከሚያዚያ 08/2004 ጀምሮ የምግብ ማቆም አድማ እንደሚያደረጉ ተገለጸ

    የጎንደር ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ከሚያዚያ 08/2004 ጀምሮ የምግብ ማቆም አድማ እንደሚያደረጉ ተገለጸ፡፡ምክንያቱንም ሲናገሩ መጋቢት 19/2004 ዓ.ም በጂሲ ካምፓስ በቁርዓን ሽንት ቤት ተጠቅሞ ሲጸዳዳ እጅ ከፍንጅ የተያዘው የዩኒቨርሲቲው ባለደረባ ከእስር መለቀቅን ተከትሎ የሚደረግ ነው ማለታቸውን የዜና ምንጫችን ከጎንደር አስታውቋል፡፡የምግብ ማቆም አድማው እስከመቸ እንደሚቆይ የታወቀ ነገር የለም፡፡ዝርዝሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ኡኡ የመንግስት ያለህ…… ኡኡ የፍትህ ያለህ….. የጎንደር የአራቱ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊምተማሪዎች ድምጽ ይሰማ…… ኡኡ የፍትህ ያለህ…..ኡኡኡ ለዜናየ መነሻ እንዲሆነኝ አንድ ነገር ልጥቀስ፡፡በአውሮፓዊቷ ሀገር ዴንማርክ አንድ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ነብዩ ሙሀመድን(ሰ.ዓ.ወ)በካር ቶን ስዕል በመሳሉ በተነሳው ችግር ሀገሪቱ በየወሩ 7.3 ቢሊዮን ዩሮ ኪሳራ ይደርስባት እንደነበርና ሰውየው ለፍርድ ቀርቦ የቅጣት ውሳኔ ካገኘ በኋላ እንደድሮው ባይሆንም ለአመታት ገቢዋ እንደቀነሰ የቅርብ ትዝታ ነው፡፡ሁሉም ሙስሊም ሀገራት ከዴንማርክ የሚገዙትን ሸቀጣሸቀጥ በማቆማቸው ነበር ይህ ሁሉ ኪሳራ የደረሰባት፡፡ወደ ርዕሴ ልመለስ፡፡ አርብ የካቲት 22/2004 በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጂሲ ግቢ ሽንት ቤት ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች የቁርዓን ቅዳጅ በአይነ ምድር ተለውሶ ወይም ሰገራ ታብሶበት ያገኛሉ፡፡በሁኔታው ግራ የተጋቡት እነኚህ ተማሪዎች ጉዳዩን በሚስጥር ይይዙትና ክትትላቸውን ይቀጥላሉ፡፡ድርጊቱ በድጋሜ ፈጸማል፡፡ በጉዳዩየተበሳጩት እነዚህ ጥቂት ሙስሊም ተማሪዎች የራሳቸውን ዘዴ መቀጠስ ጀመሩ፡፡ነገሩን ለሁሊም ሙስሊም ተማሪዎች ቢናገሩ የሚመጣውን አደገኛ ችግር ለመፍታት ዘዴ ቀየሱ፡፡ 1. ጉዳዩን ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቢያሳውቁ እንንተ ናችሁ ይህንን ያደረጋችሁ ሊባሉና ችግሩ ወደራሳቸው እንደሚመጣ ግምት ውስጥ በማስገባት ጉዳዩን በሚሥጥር በመያዝ ድርጊቱን የሚፈጽመውን ግለሰብ እጅ ከፍንጅ መያዝ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አስቀመጡ 2. ጉዳዩ ከተወሰኑ ሙስሊም ተማሪዎች በስተቀር ሌሎች እንዳይሰሙ በሚስጥር እንዲያዝ ወሰኑ፡፡ 3. ሰውየው እጅ ከፍንጅ እስኪዝ ድረስ ሰዓታቶች ተከፋፍለው ተማሪዎቹ ዋርድያ እንዲወጡ ተወሰነ፡፡ጥበቃውም በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠንከር ያለ ውሳና አስተላለፉ፡፡ 4. ሰውየው ምን አልባት ቢገኝ ምን እርምጃ ይወሰድበት በሚለው ዙሪያም ከፍተኛ ውይይት ካደረጉ በኋላ ለህግ ማቅረብብቻ እንደሚገባ ወሰኑ፡፡ 5. የሰውየውን ማንነት መለየት፤ተማሪ፣የከተማ ነዋሪ ወይም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ እንደሆነ መጀመሪ ማረጋገጥና እጅ ከፍንጅ በመያዝ ድርጊቱን ሲፈጽም በፎቶግራፍና በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ መያዝ እንደሚኖርባቸው ውሳኔ አሳለፉ፡፡ እንደተባለው ጥበቃው እንደ ነገሩ ክብደት እየከበደና እየረቀቀ መጣ፡፡የነዚህ ተማሪዎች ተስፋ በከንቱ አልቀረም፡፡ሁለተኛውን ድርጊት ከፈጸመ ከጥቂት ቀናት በኋላሌሊት የተለመደውን ተግባር ለመፈጸም አንድ ግለሰብ ወደ ሽንት ቤቱ አመራ፡፡ዘብ ነበሩት ተማሪዎች ሰውየውን ሲከታተሉት ወዘ ልውጥ የነርሱ ግቢ ሰው አለመሆኑን አረጋገጡ፡፡እንግዳ ፊት፡፡ሽንት ቤት ተጠቅሞ ሲወጣ ተከታትለው ሲገቡ የቁርዓን ቅዳጁ አይነ ምድር ተለውሶ ያገኛሉ፡፡ጠባቂዎቹ በነገሩ ቢበሳጩም በትግዕስት ሰውየውን ተከትለው ቤቱ ሲገባ ያዩታል፡፡እዚያው አካባቢ ቁጭ ብለው በማንጋት ማንነቱን ለዩ፡፡የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ሞግዚትና የደህንነት ሰራተኛ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ አሁን ነበር ትልቁ ፈተና የመጣው፡፡ተረኛ ሆነው ያደሩት ዘብ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ካምፓሳቸው ተመልሰው ጉዳዩን ለሚያውቁት ሙሉ መረጃውን ይነግሯቸዋል፡፡በነዚህ ብልህ ተማሪዎች መካከል አለመግባባት ተፈጠረ፡፡በጉዳዩ የተበሳጩትእርምጃ መውሰድን ቢመርጡም ከብዙ ውይይት በኋላ መስማማት ላይ ተደረሰ፡፡ሰውየው እንደለመደው ሊጠቀምበት ሲመጣ እንደሚይዙት እርግጠና ነበሩ፡፡ጥበቃው ሽንት ቤት ውስጥ ሆነ፡፡ጉዳዩን የሚፈጽመው ግለሰብ የሚያድረው ከዘቦች ቤት እንደሆነ ተረጋገጠ፡፡ግን ለምን ቤት እያለው ያለሥራ ቦታው ያውም ጥበቃ ሰራተኞች ቤት እንዲተኛ ተደረገ፤ሁሉንም ጊዜ ይፈታዋል፡፡ ስለ ሰውየው መያዝ፡- ሙስሊም ተማሪዎቹ 27 ቀናት ያለመታከት ሌሊት ሽንት ቤት ውስጥ እየተፈራረቁ ከጠበቁ በኋላ መጋቢት 19/2004 ግለሰቡ እንደለመደው ከጥበቃ ሰራተኞች ቤት ወጥቶ ሽንት ቤትከተጠቀመ በኋላ በጁ ይዞት በነበረው የቁርዓን ቅዳጅ ሊጠቀምሲል “አላህን ፍራ የያዝከው የጌታ(የአላህ) ቃል ስለሆነ አትጠቀምበት በማለት በፎቶና በቪዲ ይቀርጹት ጀመር፡፡የያዘው የቁርዓን ቅዳጅ አጨማትሮ “ምን ታመጣላችሁ”በማለት ከሱሪው የመቀመጫ ኪስ ከቶ ለመማታትና ለማምለጥ ቢሞክርም አልቻለም፡፡የቁርዓኑን ቅዳጅ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁትም አሻከፈረኝ አለ፡፡ግብረ አበሮቹ በመምጣት ምንአደረጋችሁ በማለት ለማስለቀቅና ለማስመለጥ ሞከሩ፡፡አልተሳካም፡፡ ከዚያም ግርግር በመነሳቱ ሰውየው ከነግብረ አባሮቹ ወደ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ፡፡ የሙስሊም ተማሪዎች መስማትና መሰባሰብ፡- ጉዳዩ 27 ቀናት ሽንት ቤት ውስጥ በጥበቃ መከራቸውን ሲያዩለነበሩት ጥቂት ተማሪዎች አላህ አስደሰታቸው፡፡የ4ቱ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎችም በደቂቃዎች የጎንደር ዩኒቨርሲቲህክምና ሳይንስ ኮሌጅን ቅጥር ግቢ አጥለቀለቁት፡፡ውጥረት ነገሰ፡፡ግን ሙስሊም “ሰላም” ነውና በርጋታ ጉዳዩን መጠየቅና መስማት ጀመሩ፡፡አዎ ውጥረት ነገሰ፡፡የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕረዚደንት፣የተማሪዎች ዲን፣የጥበቃ ኃላፊዎችና የተለያዩ ባለሥልጣናት ሙስሊም ተማሪዎችን ተቀላቀሉ፡፡ሁሉም ተማሪዎችም ሆኑ የዩኒቨርሲቲውባለሥልጣናት የአንድ ቀን ውጤት መስሏቸው ነበር፡፡ግን አይደለም፡፡ነገር ግን ውይይቱ ተጀምሮ ጉዳዩን ይከታተሉት ከነበሩት ውስጥ አንዱ 27 ቀናት በሽንት ቤት ውስጥ ስላሳለፉት ችግርና ይህንንም ያደረጉት ከሌሎች ሙስሊም ካልሆኑ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር የነበራቸው ሰላም እንዳይደፈርስና የዩኒቨርሲቲውን ሥም ለማስጠበቅ እንደነበርሲያስረዳ ወንዶች ከመድረክ ፊትለፊት ሴቶች ደግሞ ከበስተጀርባ የተሰማቸውን ሀዘን በእንባ እየተራጩ መግለጽ ቀጠሉ፡፡የማይረሳ ቀን ነበር፡፡የተማሪዎች ዲንም ምንም እንኳ ሙስሊም ባይሆንም በሁኔታው በማዘን በእንባ ሲታጠብ ውሏል፡፡በዙሪያቸው የነበሩ ፖሊሶች እንኳ በተማሪዎች ምርጥሥራ ተገርመው ያዳምጡ ነበር፡፡ ሙስሊም ተማሪዎችም የሰውየውን ሁኔታ ማወቅ እንፈልጋለን በማለት ጥያቄያቸውን ማቅረብ ጀመሩ፡፡የውይይቱ ድባብ ተቀየረ፡፡በተለይ የሰውየው ሁኔታ ሲታወቅ ተማሪዎቹ እጅግ ተበሳጩ፡፡አንድ ውሳኔ እስኪሰሙም እንደማይንቀሳቀሱ አሳወቁ፡፡የዩኒቨርሲቲው ም/ፕረዚደንትም ጉዳዩን ከያዙት ወንድሞች ጋር በመሆን ውሳኔያችንን እንሳውቃችኋለን ጠብቁ ብለው ተሰናበቱ፡፡ሁሉም ምሳውን እዚያው ተመገቡ፡፡ሁሉም እህሉ እንደመረራቸው ያስታውቃል፡፡ከአስር ሰላት በኋላ ም/ፕረዚደንቱና ተማሪዎች ተመልሰው መጡ፡፡ተማሪዎች ምላሹንለመስማት ጓጉተዋል፡፡ሁሉም ነገር ጸጥ አለ፡፡የዩኒቨርሲቲውአስተዳደር የወሰነው ውሳኔ ቀረበ፡፡ 1. ዩኒቨርሲቲው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታግለሰቡን ከሥራ ማባረሩን አሳወቀ፡፡ 2. ዩኒቨርሲቲው ግለሰቡ ይህንን ተግባር ሊፈጽም የቻለበት ዓላማና ተልዕኮ ምን እንደሆነ እንደሚመረምርና ጉዳዩን በራሱ የህግ ባለሙያዎች ተከታትሎ ውሳኔ እንደሚያሰጥ ቃል ገባ፡፡ 3. ጉዳዩንም ሁሉም ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መከታተልእንደሚችሉ አስታወቀ፡፡ 4. ጉዳዩም በፍርድ ቤት እንደሚታይና ለዐቃቤ ሕግ እንደተሰጠ በማስረዳት ሙስሊም ተማሪዎች 27 ቀናት በትግዕስት ተሞልተው የተማሪዎችን ሰላም በማስጠበቅ ወንጀለኛውን በመያዛቸው አመስግነው ወንጀለኛውን እንደሚያስቀጡት ድስኩር አሰሙ፡፡ 5. በዚህ የ12 ሰዓት ቆይታ ሙስሊም ተማሪዎች ሙስሊም ባልሆኑ አንዳንድ ግለሰቦች የተፈጸመባቸውን፣የሚፈጸም ባቸውንና ሊፈጸምባቸው የታቀዱትን ጉዳዮች በማንሳት እየደረሰባቸው ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣እየደረሰባቸው ያለው ግፍና በደል እንዲቆምላቸው የሚጠይቅ የፓናል ውይይትም ተካሂዷል፡፡ውይይቱም በሰላም ተጠናቀቀ……………. የወንጀለኛው መለቀቅ፡- ይህ ከባድ ወንጀለኛ የተከሰሰው በጎንደር ወረዳ ፍርድ ቤት ነበር፡፡ሆኖም ወንጀሉ ክባድ በመሆኑ እኛ የማየት ሥልጣን የለንም በማለት ወደ ሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይገፋዋል፡፡የሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍ/ቤትም እኔን አይመለከተኝም በማለት ወደ አማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይልከዋል፡፡ይህም ፍርድ ቤት ወደ ፌደራል ይልከዋል፡፡ነገሩክብደት ተሰጥቶታል፤ በሚል ፍትህ ልናገኝ ነው እያሉ ሲጠብቅለነበሩት የአራቱ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች፣የጎንደር ሙስሊም ህብረተሰብ፣ጉዳዩን ለሰሙት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን አንጀታችንን የሚሳርር ውሳኔ ተሰጠ፡፡ሰውየው ቀኑን በውል ባላውቀውም (ሚያዚያ 1 ወይም 2)/2004 በ15000.00(አስራ አምስት ሽህ ብር)ዋስተለቀቀ፡፡እርግጠኛ ሁኑ፡፡በዓይናችን በብረቱ ስላየነው፡፡ሁላችንም ግራ ተጋባን፡፡ዕውን ፍትህ አለ ለማለት ተገደናል፡፡ለዚህ ነው ኡኡኡኡኡአ የፍት ያለህ…… የመንግስት ለህ ያልነው፡፡ ጥያቄ፡ 1. ጉዳዩ በመጀመሪያ እንደተፈጸመ ለሁሉም ሙስሊም ተማሪዎችቢነገራቸው ምን ይከሰት ነበር 2. ተማሪዎቹ 27 ቀን ሽንት ቤት እያደሩ በብርድ እየተንሰፈሰፉ የያዙትን “በዘመኑ ቋንቋ” ትልቅ አሸባሪ እንደያዙት ቢገድሉትስ ኖሮ 3. ተማሪዎቹ እንደሰሙ እረብሻ ቢያነሱ ኖሮ በሁሉም አካባቢዎች(ዩኒቭረሲቲዎች ) ምን ሊከሰት እንደነበር ገምተዋል 4. አንድ ሙስሊም (አያደርገውም እንጅ)መጽሀፍ ቅዱስን ለሽንት ቤት መጠቀሚያ ቢደርግ እውን በዋስትና ይወጣ ይሆን ይህንን ልተወው፡፡ ግለሰቡ ይባስ ብሎ ከተፈታ በኋላ በተማሪዎች የመኝታ ክፍል ዙሪያ፣በካፌዎችና በዙሪያው እየተንጎራደደ ድሮ ሽፍታ ከዚያም ወታደር ከዚያ ደህንነት ነኝ እያለ እነዚያን ለሰላም የተዋደቁ ምስኪን ሙስሊም ተማሪዎች ማሰፍራራት መጀመሩ ለምን ይሆን፡፡ለነገሩ”ጌታዋንየተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች”ይባል የለ፡፡ምን ይደረግ! ለነርሱ አላህ አላቸው፡፡ ማጠቃለያ፡- 1. ይህ ግለሰብ ሙስሊሞችንና የሌላ ዕምነት ተከታይ ተማሪዎችን በማፋጀት የዩኒቨርሲቲውን ሰላም፣የሀገራችንን ሰላምለማደፍረስና ሀገራችን ከሌሎች ሙስሊም ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ግንገኙነት በማሻከር ካለብን ድህነት ላይ ሌላ ድህነት ለመጨመር ዓላማው አድርጎ የተነሳን ግለሰብ በዋስ መልቀቅ ምን ይሉታል ፍትሀዊ ነው ይገርማል፡፡ለነገሩ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” ይባላልእኮ….. 2. ዩኒቨርሲቲው ለሙስሊም ተማሪዎች የገባውን ቃል ለምን አልጠበቀም ለነገሩ ከማን የተማረውን 3. ዩኒቨርሲቲው ምናልባት ምንም አያመጡም ብሎ አስቦ ከሆነ ችግረ አለ ችግርም ይኖራል፡፡ወንጀለኛውም እነዚህን ምስኪንተማሪዎች ከማስፍራራት የማይቆጠብ ከሆነ…… ሰውየው ሌላ ተልዕኮ አለው ማለት ነው 4. መንግስት በዚህ ግለሰብ ላይ አፋጣኝ እርምጃ የማይወስድ ከሆነ ሁሉም ሙስሊሞች ጉዳዩን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ሚዲያዎች በማሳወቅ የሙስሊሙን ችግር ማሳወቅ ኖርብናል፡፡ስለዚህ ሁላችንም ለዚህ ዝግጁ እንሁን፡፡ Read more

Latest Articles

Most Popular