Latest Articles

  • Palestine: Israeli soldiers invade several towns near Hebron

    24-03-2012 IMEMC: Israeli army invaded on Thursday at night several towns near the southern West Bank city of Hebron, and also invaded several neighborhoods in the city, clashes were reported. Eyewitnesses reported that several army vehicles invaded a number of suburbs in Hebron, and installed roadblocks at the entrances of Ithna and Beit Kahil towns, held dozens of residents and detained several youths for hours before releasing them. On Wednesday evening, soldiers invaded Doura town, near Hebron, and clashes with several youths who hurled stones and empty bottles at them; no injuries were reported. Late on Wednesday evening, a number of Palestinians hurled Molotov cocktails at an Israeli monitoring tower near Al-Arroub refugee camp, north of Hebron. Israeli media sources reported that three Molotov cocktails were hurled at the jeeps, no damages or injuries were reported. Two more cocktails were hurled at settler vehicles driving at the main road between Gush Etzion settlement and the Al-Arroub refugee camp leading to damages but no injuries, Israeli sources reported. Soldiers invaded the camp and conducted military searches of homes, no arrests were reported. Read more
  • al azhar university temariwoch le ethiopia muslim degafachewun geletsu

    የአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኢትዮጲያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄዎች ድጋፋቸውን ገለፁ Details Category: International Hits: 2 አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 14/2004 በግብፅ የአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆኑ ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች መጅሊስን በመቃወምና አህባሽን በማውገዝ በሀገር ውስጥ እየተካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ አስታወቁ ፡፡ በካይሮ የሚገኙ ኢትዮጲያውያን ሙስሊም ማህበረሰብ አባላትና የአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዳስታወቁት በአወሊያ ህዝብ ንቅናቄ የተነሱትን የመብት ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ ይደግፏቸዋል፡፡ በአወሊያ ጎልተው የወጡትን የህዝብ ጥያቄዎች የነርሱም ጥያቄዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ የስምምነት ፊርማ/ፒቲሽን/ እያሰባሰቡ መሆኑንም ለሬዲዮ ቢላል በላኩት መግለጫ አመልክተዋል፡፡ Read more
  • good news ye shashemene mejlis be fedralu mejlis almeram ale!!!

    የሻሸመኔ መጅሊስ በፌደራሉ መጅሊስ እንደማይመራ ገለፀ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 12/2004 በኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሲመራ የቆየው የሻሸመኔ መጅሊስ ካሁን በኋላ በፌደራ ምክር ቤት እንደማይመራ ተናገረ፡፡ አዳማ ላይ በተደረገው የአህባሻ ስልጠና በኦሮሚያ መጅሊስ አመራሮች ውሃብይና አክራሪዎች በመባላቸው ልዩነት መፍጠሩን የሻሸመኔ የመጅሊስ ሀላፊዎች ገልፀዋል፡፡ የሻሸመኔ የእስልምና ጉዳይ የኦዲተር ኮሚቴ እንደገለፁት የፌደራልና የኦሮሚያ መጅሊሶችን የሚሠጡት የአህባሽ ስልጠና ባለመቀበላችን መዋቅሩን ያልጠበቀ የሥራ እግድ ደብዳቤ ተፅፎልናል ብለዋል፡፡ የፌደራልና የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች በሻሸመኔ ከተማና በአርሲ ዞን ያሉ ሙስሊሞች ውሃቢይዎችና አሸባሪዎች ናችሁ ብለው መፈረጃቸውንም የኦዲተር ኮሚቴው ገልፀዋል፡፡ የሻሸመኔ ሙስሊም ነዋሪዎች በሁለቱም ነዋሪዎች መጅሶቹ ላይ ተቃውሞአቸውን እያቀረቡ ሲሆን የሻሸመኔ መጅሊስ ከህዝቡ ጎን ነው ሲሉ በኢትዮጲያ ደረጃ ለመንግስት ጥያቄ ያቀረበው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እንደሚደግፍም ጠቁመዋል፡፡ Read more
  • ዶ/ር ሽፈራው AHBASH LE MUSLIMU YETEMERET NEWU BEMALET BEDEFRET TENAGERE BETAM YASAZENAL

    መንግሥት ከእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በመተባበርም ዋህቢያ የሚቃረን የአህባሽ ትምህርት ለአማኙ እንዲሰጥ እየተደረገ ነው ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግሥት ዋህቢያ የሚባለውን አስተምሮ የሚያራምዱ ወገኖች በሕገ መንግሥቱ የሰፈሩ የእምነት ነፃነቶች እየጣሱ ነው፣ እስላማዊ መንግሥት እንዲቋቋም ይፈልጋሉ በሚል በአክራሪነት ፈርጆ ዕርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ከእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በመተባበርም እሱን የሚቃረን የአህባሽ ትምህርት ለአማኙ እንዲሰጥ እየተደረገ ነው፡፡ የዋህቢያ አስተምህሮ መፍለቂያ በሚባለው አወልያ የትምህርት ማዕከልም አንዳንድ ለውጦች እያደረገ መሆኑን ይናገራል፡፡ በዚህም ምክንያት መንግሥት ተቃውሞም እየቀረበበት ነው፡፡ ይህም በእምነቱ ተከታዮች መካከል ውዥንብር እየፈጠረ ሲሆን፣ ጉዳዩን በኃላፊነት ወስዶ እየተንቀሳቀሰ ያለው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሲሆን፣ ሚኒስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያምን በወቅታዊው የእስልምና እምነት ውስጥ በተከሰቱ ውዝግቦችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የማነ ናግሽ አነጋግሯቸዋል፡፡ ሪፖርተር፡- በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ በአሁኑ ወቅት ከሚታየው ሁኔታና ከሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ አንፃር መንግሥት የያዘውን አቋም ቢያብራሩልኝ? ዶ/ር ሽፈራው፡- ትልቁና እንደ መንግሥት እየተወያየን ያለነው ጉዳይ አቋማችን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በማክበርና በማስከበር ላይ የተመሠረተ መሆኑን ነው፡፡ በሃይማኖት ተቋም ውስጥ ያሉ የእምነቱ ተከታዮችና ሊቃውንት ከሃይማኖታቸው ተነስተው የሚያብራሯቸው ነገሮች ይኖራሉ፡፡ እንደ መንግሥት እኛ የምንገልጻቸው ነገሮች ግን ሙሉ በሙሉ ሕገ መንግሥታችንን በማስከበርና በማክበር ዙሪያ ላይ የሚያጠነጥኑና በዚያው የተወሰኑ ናቸው፡፡ ከዚያ የሚወጡበት አንዳችም መንገድ የለም፤ ሊወጡም የሚችሉ አይደሉም፡፡ በዚህ መሠረት ሦስት የሕገ መንግሥታችን መሠረታዊ የእምነት ድንጋጌዎች አሉ፡፡ የመጀመሪያው በአገራችን የእምነት ነፃነት የተከበረ ነው የሚል ነው፡፡ የዜጎቻችን የእምነት ነፃነት በምንም ዓይነት መገደብ አይቻልም፡፡ ሁለተኛው በአገራችን ያሉ ሃይማኖቶች እኩል ናቸው፡፡ አንደኛው ከሌላኛው አይበልጥም፣ አያንስም የሚለው ነው፡፡ ሦስተኛው መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው የሚል ነው፡፡ መንግሥታዊ ሃይማኖት ወይም ሃይማኖታዊ መንግሥት የሚባል የለም ለማለት ነው፡፡ እነዚህ መርሆዎች አንድ ላይ ተደምረው የዲሞክራሲያዊ ሥርዓታችን መገለጫዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ እንኳን ቢጎድል የተሳካ ሊባል አይችልም፡፡ አንዱ ቢጎድል ዲሞክራሲያዊ ሥርዓታችን ተጨናግፏል፤ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓታችን ተጥሷል ወደሚል ነው የሚወስደን፡፡ እንግዲህ የመንግሥት ኃላፊነት በእነዚህ ሦስት ጉዳዮች ላይ የተቀመጠ ነው፡፡ እነዚህ ሦስቱ መሠረታዊ መርሆዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ፀረ ሰላም፣ ፀረ ልማት፣ ፀረ ዲሞክራሲ የሆነ ድርጊት መፈጸም ክልክል ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱም ይደነግጋል፡፡ ምን ማለት ነው? ለምሳሌ የእምነት ነፃነት የግለሰቦች ነው፣ የዜጎች ነው፣ ማንም አያስገድድም ብለናል፡፡ አንደኛው የሌላኛውን ሃይማኖት ተከታይ የእኔን እምነት ካልተከተልክ ብሎ ማስገደድ ከጀመረ የሰላም መደፍረስ አለ ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው የግለሰቡ ዲሞክራሲያዊ መብት ተጥሷል፡፡ ዲሞክራሲያዊ መብት በሚጣስበት ወቅት፣ ሰላም በሚደፈርስበት ጊዜ መንግሥት ቁጭ ብሎ ሊያይ አይችልም፡፡ የመንግሥት አንዱ ተልዕኮ ሁላችንም እንደምናውቀው የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት ማስከበር ነው፡፡ ሁለተኛው የሁለት እምነቶችን እኩልነት የሚመለከት ነው፡፡ ሃይማኖቶች እኩል ሆነው ሲያበቁ የእኔ ሃይማኖት ነው የበላይ፣ የአንተ ሃይማኖት ነው የበታች እያሉ ሰዎች ኹከት፣ ብጥብጥና ግርግር ውስጥ የሚገቡ ከሆነ ሁለቱንም ይጥሳል፡፡ ሰላምን ያደፈርሳል፣ ዲሞክራሲን ይንዳል ማለት ነው፡፡ በዚህ ሒደት ልማትም ይስተጓጎላል፡፡ ዜጎች በድህነትና በኋላቀርነት ላይ መዝመታቸው ቀርቶ፣ ብዙኅነታቸው የእምነታቸው ጉዳይና ዋናው ትኩረታቸው ስለሚሆን ይህንን መብታቸውን ለማስከበር መንቀሳቀሳቸው አይቀርም፡፡ በአገራችን ረዥም ትግል የተካሄደው ይህንን ባለመቀበላችን ነው፡፡ ሰላምን፣ ዲሞክራሲንና ልማትን ተቃርኖ የሚቆም ነገር ሲገኝ ዜጎች ለመንግሥት በሰጡት አደራ መሠረት ለመከላከልና ለማስጠበቅ መንቀሳቀሱ ግድ ነው፡፡ ይህንን ባያደርግ ደግሞ የሚያስጠይቀው ነው የሚሆነው፡፡ በአገራችን ያሉት ሃይማኖቶች የቆየ ታሪካቸው ተቻችለው፣ ተባብረውና ተደማምጠው መኖር ነው፡፡ በእስልምናም በክርስትናም ሃይማኖቶች እንደዚህ ነው፡፡ ምናልባትም መንግሥታት ለራሳቸው ግዛትና ንግድ ለማስፋፋት ጭምር ሃይማኖትን እንደ መግቢያ አድርገው ለመውሰድ በሞከሩበት ጊዜ ጭምር አንደኛው ሌላኛውን እየሸፈነ፣ እየተከላከለና አንዱ ሌላውን ሲንከባከብ ለመቆየቱ ታሪክ የነበረን አገርና ሕዝብ ነን፡፡ በዚያ ውስጥ አሉ የሚባሉ ቅሪት አስተሳሰቦችም ጭምር በሒደት እየተስተካከሉ መጥተው በሕገ መንግሥታችን መቋጫ ያገኙበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እንደዚያም ሆኖ በሁሉም ሃይማኖቶች አካባቢ ቀደም ሲል ያነሳናቸውን መርሆዎች የሚፃረር እንቅስቃሴዎች ጠፍተዋል ማለት አይቻልም፡፡ ሪፖርተር፡- መንግሥት ከዚህ የሃይማኖትና የመንግሥት መለያየት መርህ አንፃር ዋህቢያ የተባለውን እንቅስቃሴ በአክራሪነት ሲፈርጅ ከምን ትንታኔ በመነሳት ነው? ዶ/ር ሽፈራው፡- በቅርብ ጊዜያት ፊት ለፊት አፍጥጦ የመጣው በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን እየተደረገ ያለው የዋህቢያ እንቅስቃሴ መሠረቱ ረዥምና ሰፊ ነው፡፡ በሳዑዲ ዓረቢያ አካባቢ ገና ከመነሻው መሐመድ ቢን አብዱል አልዋህድ የሚባሉ የሃይማኖቱ የመጀመርያ ፈላስፋ ተብለው የሚጠቀሱ የእምነቱ አባት፣ ከሳዑዲ ዓረቢያ ከነበረው መንግሥት ጋር ተደራድረው የመሠረቱት ነው፡፡ በሰውዬው ስያሜ ተመሥርተው ዋህቢያ ብለው ሲያስፋፉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በመንግሥት ክንፍ መንግሥታዊ ሃይማኖትን በንጉሣዊ ቤተሰብ ሥልጣን ይዘው ቆይተዋል፡፡ ስለዚህ ሲወርድ ሲዋረድ የጋራ መግባቢያ ሰነድ እየተፈራረሙ በአንድ በኩል መንግሥት ዋህቢያን እንዳይነካ፣ በሌላ በኩል ዋህቢያ መንግሥትን እንዳይነካ በጋራ የሚኖሩበት ሁኔታ ነበር፡፡ ስለዚህ ዋህቢያና የአብዱል አልዋህድ ልጅ፣ የንጉሣዊያን ቤተሰቦች የልጅ ልጆች አንደኛው አንደኛውን ጠብቆ በመኖር የጋራ መግባባት ፈጥረው የሄዱበት ነው፡፡ ይኼ እምነት በሳዑዲና በሌላ ቦታ ባለው ሲወሰድ አንዱና የመጀመርያው መንግሥታዊ ሃይማኖት መሆን ነው፡፡ ስለዚህ የዋህቢያ ዋና መነሻውና መደምደሚያው “መንግሥታዊ ሃይማኖት ካልሆንን በስተቀር በአንድ አገር ውስጥ ሃይማኖት አለን ማለት አንችልም፡፡ እኛ የምናምነውን የማይከተል በሙሉ ሙስሊም አይደለም፡፡ ከዚያ ውጪ ያለው በሙሉ እንደሰው ሊቆጠር የማይችል ከሃዲ ነው፡፡ ስለዚህ መጥፋት አለበት፤” ብሎ የሚንቀሳቀስበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ዋህቢያ የእምነት ነፃነትን አያስተናግድም፤ በራሱ በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ ሌሎች የትኛውም ዓይነት የእስልምና “ሴክቶች” መኖር የለባቸውም የሚል ነው፡፡ መጥፋት አለባቸው ብሎ ነው የሚሄደው፡፡ ይኼ የእምነት ነፃነትን የሚጋፋ ነው፡፡ ሌሎች ውስጥ ያሉ አማኞች ሰላም ሲሏቸው እንኳን “ሂዱ መጀመርያ ሰልማችሁ ኑ” በሚል የሚፈርጁና ከመንግሥት ጋር ባለው ማንኛውም ግንኙነት ደግሞ እስላማዊ ካልሆነ መንግሥት ጋር ትብብር ፈጥራችኋል ስለዚህ ከሃዲ ናችሁ በማለት በማስገደድ ጭምር ሌሎች ሴክቶችን መጀመርያ በማባበል፣ ከዚያ በማስፈራራት፣ ካልሆነ እስከ መግደል ድረስም ጭምር በመሄድ ወደ ራሱ ሴክት ለመቀየር የሚረባረቡ ኃይሎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ሦስቱን ሕገ መንግሥታዊ መርሆዎች የሚቃረን አስተሳሰብ ነው፡፡ እኛ እንደሱ ያለ ፍልስፍና አይደለም እያራመድን ያለነው፡፡ እኛ የምናራምደው ፍልስፍና ሕገ መንግሥታችን ነው፡፡ ከዚህ ተነስተን ነው ዋህቢያ ማለት አክራሪ ተቋም ነው፡፡ ይህንን አክራሪነትን በመተው በይፋ ሕገ መንግሥታችንን እንቀበላለን ብሎ አውጆ ከገባ እኛ ከዋህቢያ ጋር ነገር የለንም፡፡ መንግሥትም ሙስሊሙን ሕዝብ እየጠየቀ ያለው እነዚህ መርሆችን አክብሮ፣ የየትኛውንም ሃይማኖት መኖርን ለሕዝቡ ግልጽ አድርጎ ራሱን በዚያ መርህ መርቶ መሄድን ነው፡፡ “የእኛ እስልምና የመንግሥት ሃይማኖት ካልሆነ በስተቀር እዚች አገር ውስጥ ካለ አክራሪ (ከሃዲ) መንግሥት ጋር ተባብረን መኖር አንችልም፡፡ ስለዚህም ዋናው መፍትሔ መታገል መታገል ነው፤” የሚለው፡፡ ሪፖርተር፡- መንግሥት የአህባሽ ትምህርት (ሥልጠና) በሊባኖስ ኡላማዎች እንዲሰጥ እያመቻቸ ነው፡፡ የመንግሥትን ዕርምጃ የሚቃወሙ የእምነቱ ተከታዮች በበኩላቸው፣ ሁለቱም አስተሳሰቦች እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ የኖሩ መሆናቸውን ገልጸው፣ መንግሥት አንዱን ጎራ ለይቶ ሌላውን ለማዳከም እየሠራ ነው፤ በሃይማኖታችን ጣልቃ በመግባትም ሕገ መንግሥታዊ መርሁን ጥሷል ይላሉ፡፡ ዶ/ር ሽፈራው፡- ለያይተን ብናያቸው ጥሩ ነው፡፡ አህባሽን በሚመለከት አህባሽ የሚባል ሃይማኖትም ሴክተርም የለም፡፡ ይኼኛው ዋህቢዮችና የዋህቢያ ድምፅ የሚያስተጋቡት፣ አንዳንድ የግል ጋዜጦች ለማደናገር ይጠቅማል በሚል በስፋት ያሰመሩበትና ሕዝበ ሙስሊሙን እስከማደናገር ድረስ የሄዱበት ጉዳይ ነው፡፡ አህባሽ የሚባለው የዓረቦቹ አገላለጽ በንጉሡ ዘመን (እንደሚታወቀው ሃይማኖቶች በእኩል የማስተናገድ ችግር ስለነበር) ሃይማኖታቸውን ሊያስፋፉ የሚችሉበት ዕድል ስላልነበር፣ በሞከሩበት ወቅትም በእስር እንዲቆዩና የቁም እስረኛ ተደርገው፣ በኋላ በስደት ለቀው የሄዱ ሼክ አብዱላሂ የሚባሉ የሐረሪ ተወላጅ ማለት ነው፡፡ ሼክ አብዱላሂ ኢትዮጵያዊ እንደመሆናቸው (ዓረቦቹ ከኢትዮጵያ የሄደውን ሰው በሙሉ አህበሽ ነው የሚሉት) ከእሳቸውም ጋር በተያያዘ የሚሰጡት ትምህርት የአክራሪነት አስተሳሰብን በቅዱስ ቁርዓንና ሐዲስ አስተሳሰብ ቀይረው ማስተማር በመቻላቸው ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝተው፣ ትምህርቱንም አስፋፍተው በዓለም ደረጃ ወደ 54 አገሮች አካባቢም ጭምር የሚያስተምሩት ነው፡፡ ትምህርቱም ነባር የእስልምና እምነት የሚከተላቸው አስተምህሮዎችን ነው፡፡ ተለየ ተብሎ የሚቀርብ ነገር የለም፡፡ ተለየ ተብሎ የሚገለጸው አህባሽ የሚባለው አገላለጽ ኢትዮጵያዊ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ምሁር ከወሰዱት በኋላ ሊቃውንት ለአገራችን መልሰው አምጥተው ያስተማሩት ትምህርት ነው፡፡ ስለዚህ የአቀራረብ ጉዳይ ካልሆነ መሠረታዊ የእስልምና ሃይማኖት አባቶችና ምሁራን እንደሚናገሩት ከእምነት የወጣ ነገር አይደለም፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሃይማኖቶች የተለያዩ ምሁራንን እያስመጡ ያስተምራሉ፡፡ ለምሳሌ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ብንወስድ ከህንድ፣ ከግብፅ፣ ከሶሪያና ከተለያዩ መሠረታዊ የእምነቱ እውቀት አለ ብለው ከሚያስቡዋቸው አገሮች መምህራንን እያመጡ የሚያስተምሩበት ሁኔታ አለ፡፡ ዋህቢያም ምንም ማቆሚያ ሳይኖረው ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከፓኪስታን፣ ከአፍጋኒስታንና ከተለያዩ የአክራሪነት አስተሳሰብ ያለባቸው (ከሱዳንም ጭምር) ሰዎች እያመጣ ሕዝበ ሙስሊሙን በማደናገር ሲያስተምር ነው የቆየው፡፡ ስለዚህ እነዚህ በዚህ ዓይነት መንገድ ሲመጡ (ለምሳሌ ከህንድ የመጣ አስተማሪ ሂንዱዝም አምጥተሃል አልተባለም) የተለያየ አገር ዜግነት ይዘው መጥተዋል ያለ ሰው የለም፡፡ ዋናው ሰዎችን ያስተማሩት ትምህርት በእምነት ተከታዮች ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶና የሃይማኖት ዕውቀት ይጨምራል በሚል የተወሰደ ነው፡፡ ስለዚህ አዲስ ነገር አይደለም ለማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ የተሰጡት ትምህርቶች በምንም ዓይነት መንገድ እንደ ትምህርት ይሰጣሉ እንጂ፣ የግድ ተግተህ ወስደህ በዚህ ላይ ማመን አለብህ ብሎ የሚያስገድድ ሰው የለም፡፡ ይህንን ማድረግ ከሕገ መንግሥታችን ጋር የሚጋጭ ነው የሚሆነው፡፡ አሁን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያመጣቸው መምህራንም ቢሆኑ በራሳቸው ጊዜ የመጡና ትምህርቱን ያስተማሩ እንጂ፣ ይህንን ትምህርት ካልተቀበልክ በስተቀር የሚሉበት መንገድ የለም፡፡ ኅብረተሰቡ ትምህሩን ይወስዳል፣ መቀበልና አለመቀበል የራሱ መብት ነው፡፡ ስለዚህ በአህባሽ ዙርያ የሚነዙት መደናገሮች የዋህቢያው ቡድን ናቸው፡፡ ይህንን የሚያራምደው አካል ሕዝባችንን በቀላሉ ለማደናገር ያመቸናል ያለው መጤ ሃይማኖት መጅሊሱ አምጥቶ ጭኖብሃል ነው፡፡ ይህ አመለካከት በቀላሉ ሕዝቡ ውስጥ ገብቶ ሊያንቀሳቀስ የሚችል ነው ብለው ያመጡት ጉዳይ ነው፤ ግን ውሸት ነው፡፡ ስለዚህ አህባሽ የሚባል ሃይማኖት የለም፡፡ የእስልምና ጉዳዮች ሲያስተምር የነበረው የነባሩን እምነት ተከታዮች ዕውቀት ለማሳደግ ነው፡፡ እንደዚያም ሆኖ አልቀበልም፣ ይህንን ትምህርት አልወስድም የሚል አለመሳተፍ ይችላል፡፡ ትምህርቱንም ወስዶ አይጠቅመኝም ማለት የራሱ ሕገ መንግሥታዊ መብቱ ነው፡፡ ሪፖርተር፡- ዋህቢያ እንደ ተቋም ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ወይ? ከአልቃይዳና ከሌሎች የታጠቁ አሸባሪ ድርጅቶች ጋር ዋህቢያ የሚለይ መሆኑን ወይም አንድነት እንዳለው መንግሥት ምን ያህል አጥንቶዋል? ዋህቢያ አክራሪ ነው ለሚለው ፍረጃስ ተጨባጭ ማስረጃዎቹ ምንድን ናቸው? ዶ/ር ሽፈራው፡- እስልምና ወደ አገራችን ከገባ ወደ አንድ ሺሕ አራት መቶ ዓመታት ሲያስቆጥር የሚታወቀው በሱፊ-ሱኒ እምነት ነው፡፡ የአገራችን የእስልምና እምነት ተከታይ የሚከተለውም ይኼንን ነው፡፡ በሒደት ግን በተለያዩ ሰዎች አማካይነት የዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ያላቸው አካላት በተለያዩ ሽፋኖች በትምህርትና በማሠልጠን ሽፋን ወደ አገራችን የመጡበት ሁኔታ አለ፡፡ ምናልባትም የዛሬ 25 ወይም 30 ዓመት ይሆናል ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ ዋናው መተከያው የነበረው (የተለያዩ ቦታዎች እንዳሉ ሆነው) አወልያ የትምህርት ኮሌጅ የሚባለው ነው፡፡ አወልያ ሥራውን ሲጀምር ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለልጆቻችን ይጠቅማል ብለው ያደራጁት ተቋም ነው፡፡ ይህ ተቋም እየሰፋ ሲሄድ፣ በተለይም አንዳንድ የውጭ አገር መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በእገዛና በድጋፍ ስም ተቋሙን እየተቆጣጠሩት ሄደዋል፡፡ በተለይም ዓረብኛ ቋንቋ እናስተምራለን በሚለው የትምህርት ክፍል ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች አባትና እናት የሌላቸውን ወጣቶች በማሰባሰብና በመመልመል፣ የዋህቢያን ትምህርት በቀጥታ ከሙሐመድ ቢን አብደል ውሃብ የተጻፉትን መጻሕፍት በመጠቀም ዝግ በሆነ ሁኔታ በምንም ዓይነት መንገድ ከውጭ እንዳይገናኙ ከውስጥ ብቻ ቆልፈው፣ ወደ ውጭ በሚወጡበት ጊዜ ተናዳፊ እንዲሆኑ አሠልጥነዋል፡፡ እስከዛሬ ከ200 እስከ 300 የሚሆኑ ተማሪዎችን በዚህ ዓይነት መንገድ እስከ አራት ዓመት ድረስ አስተምረው እየተመረቁ እንዲሰማሩ አድርጓቸዋል፡፡ ስለዚህ የሚሰማሩ ተማሪዎች የእስልምና ትምህርት በሚሰጥባቸው የትምህርት ተቋማት መድረሻዎች ላይ ይሰማራሉ፡፡ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ በማስገባት የዋህቢያ አስተሳሰብን በመዝራት ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋ እንዲሄድ ያደረጉበት ሁኔታ አለ፡፡ ለዋህቢያ አስተሳሰብ ምንጮች ናቸው ከሚባሉ ውጭ አገር ካሉ ከተለያዩ ተቋማትም ጋር ግንኙነት እየፈጠሩ፣ ለዚህ የሚሆን ሀብት እያመጡ፣ ከሀብቱም ትልቁን ድርሻ ለራሳቸው እያዋሉ፣ ሌላውን ደግሞ የዋህቢያን አስተሳሰብ መግዣ እያደረጉ የተንቀሳቀሱበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለዚህ በገንዘብ ነው የሚገዙትና የሚያንቀሳቅሱት የሚለውን ለማስቀመጥ ነው፡፡ ሪፖርተር፡- መንግሥት በአወልያ የትምህርት ተቋም አንዳንድ ለውጦች ለማድረግ ሲንቀሳቀስ ግን ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበበት ነው ያለው፡፡ ዶ/ር ሽፈራው፡- በዓረብኛ ትምህርት ሽፋን የሚሰጠውን የአክራሪነት ትምህርት ማቆም አለበት ብሎ መጅሊሱ ሲንቀሳቀስ “አሁን ለመጨረሻ ጊዜ ምሽጋችን ተመታ ማለት ነው፡፡ ይኼ ተመታ ማለት የአይዲዮሎጂው መፍለቂያና ማስተማሪያ ማዕከልና የእኛ ህልውና አበቃ ማለት ነው” በሚል ነው የመጨረሻ የሞት ሽረት አድርጎ የመንቀሳቀስ ሥራ ውስጥ እየተገባ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ በአገራችን ቁጥሩ በጣም ትንሽ የሆነ ነገር ግን በሰፊው ከውጭ በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀስ አንዳንድ ባለሀብቶችም (ጥቂት ኢትዮጵያውያንም) ባሉበት ነው እየሠራ ያለው፡፡ በተለይም አዲስ አበባ ውስጥ በሚታወቁ ቦታዎች ላይ ዋና ማዘዣ ጣቢያ ሆነው የሚሠሩበት፣ በኦሮሚያም ወደ ስምንት ዞኖች አካባቢ ሰፍረው የሚገኙበት፣ በደቡብ ክልልም አንድ ሦስት አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ያሉበት፣ በአማራ ክልልም አንድ ሦስት ዞኖች አካባቢ ላይ በስፋት የሚንቀሳቀሱበት ሁኔታ ፈጥረው ነው እየሄዱ ያሉት፡፡ ስለዚህ በአገራችን ውስጥ የእምነት ነፃነትን የሚጋፋው የዋህቢያ አመለካከት ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴውም አለ፡፡ ምን እየሠሩ ነው ያሉት? ከራሳቸው አመለካከት ተነስተው እነሱን የማይከተለውን በአደባባይ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ለሕልፈተ ሕይወት የሚዳርጉበት ሁኔታ አለ፡፡ የእኔን ሴክት ካልተከተልክ ብለው የሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት በተገቢው የፀሎት በሥርዓት እንዳይፈጸም የሚከለክሉበት ሁኔታም አለ፡፡ የእነሱን ሴክት ያልተከተሉ ሰዎችም ማኅበራዊ መገለል እንዲደርስባቸው የሚደረግበት ሁኔታም አለ፡፡ ብዙ መገለጫዎች አሉት፡፡ በሌላ በኩል የእኔን ሴክት የማይከተል በሙሉ የከፈረ ነው (ከሃዲ ነው)፣ መንግሥትም ጭምር እስላማዊ አይደለም በሚል በትምህርት፣ በጤናና በግብር ከመንግሥት ጋር አንተባበርም፡፡ ወደ ትምህርት ተቋማትም እንዳትሄዱ፣ ከመንግሥትም ጋር እንዳትተባበሩ፣ ግብርም እንዳትከፍሉ በሚል ፀረ ልማት አካሄድም ጭምር የሚፈጽሙበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ “እስላማዊ መንግሥት ነው የምንፈልገው፣ ሃይማኖታችን ነው የሚያዘው” በሚል በአደባባይ የሚሄዱበት፣ በጋዜጦችም ጭምር በይፋ የሚገልጹበት ሁኔታ ጭምር ነው ያለው፡፡ በአንድ ጋዜጣ “ቅዱስ ቁርዓንን ሐዲሳችን ሕገ መንግሥታችን ነው፡፡ ስለዚህ እስላማዊ ያልሆነ ሕገ መንግሥት እኛን አይወክልም፤ እኛ አንገዛበትም፤” በይፋ ያሉበት ሁኔታ አለ፡፡ ሌሎችም በውይይት መድረኮች በግልጽ የሚናገሩት አሉ፡፡ የመቃብር ቦታዎችን፣ ቤተክርስቲያንና መስጊዶችን በስፋት የማቃጠል ተግባር ይፈጽማሉ፡፡ ባለፉት ሁለት ሦስት ሳምንታት ደግሞ አወልያን ማዕከል አድርገው የግብፁ “ታህሪር ስኩዌር” እናደርጋለን በሚል ራሳቸውን እያደራጁ፣ በአዲስ አበባም በሌሎች አካባቢዎችም የሚያደራጁበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ይህንን አስተሳሰብ ይዘው መቀጠላቸው ከሕገ መንግሥታችን ውጪ ስለሆነ ነው እየተንቀሳቀስን ያለነው፡፡ በእርግጥም በተጨባጭ የአገርና የሕዝብ ስጋት ሆኖ ያለ አካሄድ ነው፡፡ “ካርጅያ” የፖለቲካ (አይዲዮሎጂ) ክንፍ ሆኖ የሚሠራ ድርጅት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የራሱ ተቀጥላ ሆኖ የሚሠራ “ከዋርጅያ” በሚባለው ደግሞ፣ ከሌሎች እየተናበቡ ከፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር እያበሩ፣ ሰዎች በጣም አሰቃቂ በሆነ መንገድ እየገደሉና እያተራመሱ የሚሄዱበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ለምሳሌ ኦነግ እንደ ኦነግ ሆኖ በመንቀሳቀሱ ሕዝቡ አልቀበል ሲለው፣ በሃይማኖት ሽፋን ከዋርጅያ ሆኖ የኦነግ አስተሳሰብን ለማራመድ የሚንቀሳቀሱበት ሁኔታ ነበር፡፡ ይኼ በተጨባጭ ሰዎች ራሳቸው ተይዘው በዚያ ውስጥ የተገኙበትና የተፈረደባቸው ሁኔታ ነው፡፡ ሪፖርተር፡- ያም ሆኖ መንግሥት በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ ገብቶ እየተጫወተው ባለው ሚና፣ የችግሩን አቅጣጫ ለመቀልበስ እየተከተለው ያለው አካሄድ ትክክል ነው ይላሉ? ዶ/ር ሽፈራው፡- ዋናው የአክራሪነት ችግር በአገራችን ያለው ድህነትና ኋላቀርነት የሚወልደው ነው፡፡ በሰዎች ድህነት ላይ ዋሃቢዝምን ለማስፈን እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ያለው፡፡ ሁለተኛው የዕውቀት ችግር ነው፡፡ ይኼ በሁለት መንገድ ይታያል፡፡ አንደኛው ሕገ መንግሥታዊ ዕውቀት ነው፡፡ ሁለተኛው ራሱ የዲን (ሃይማኖት) ዕውቀት ነው፡፡ ስለዚህ የዚህ የዋህቢያ እንቅስቃሴ ምን እንደሆነ ሳይገነዘቡ በመደናገር የተቀላቀሉ ዜጎች አሉ፡፡ በአንድ በኩል ሕገ መንግሥታችን ምን እንደሚል ማስጨበጭ፣ በሌላ በኩል የዲኑ ዕውቀት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የተሠራው ሥራም ቢሆን መንግሥት እዚህ ውስጥ ያሉትን ለመፋረድ በሕግና በሥርዓት ከመሄዱ በፊት፣ መጀመርያ በውስጡ የተቀላቀሉትን ንፁኃን ዜጎችን፣ ሆን ብለው ይህንን ሥራችን ብለው ከገቡት የመለየት ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ምን ይላል ብሎ ለዜጎች ማስተማር የመንግሥት ግዴታ ነው፡፡ መንግሥት በተለያዩ ደረጃዎች ሲያደርግ የነበረው እያደረገም ያለው ይህንን ነው፡፡ አውቀውትም ይሁን ሳያውቁ የገቡ ዜጎች ግን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎቹን ማሳወቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ግዴታ ቢሆንም፣ ሕዝባችን ያለውን ንቃተ ህሊናና ሌሎች ነገሮችን ታሳቢ በማድረግ መንግሥት ሕገ መንግሥትን ለማስተማር ተንቀሳቅሷል፡፡ ሕገ መንግሥትን ለማስተማር በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ሕገ መንግሥትን በመቃረን መቆም ማለት ምን ማለት እንደሆነና ቆመውስ የተገኙ እነማን መሆናቸውን መናገር ማለት በዚያ ሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ መግባት ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ መንግሥት ያደረገው ነገር ቢኖር ሕዝባችን ሕገ መንግሥቱን አውቆ ራሱ ዘብ እንዲቆም ለማስቻል፣ በዚህ ዙሪያም ብዥታዎች ካሉም ጠርቶ እንዲወጣ ነው፡፡ ዋህቢያ ራሱ ተለይቶ እንደወጣ ራሱ ገልጿል፡፡ እነማን እንደሆኑ ተለይቶ የታወቀበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ሳዑዲ ዓረቢያ ካለው ዋህቢያ እኛ እንለያለን ብለው ሐሳባቸውን ቀይረው ከመጡ እኛ ጠብ የለንም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዋህቢያ የእምነት ነፃነትን፣ መንግሥትና ሃይማኖት የተለዩ ናቸው የሚለውን መርህ አክብሮ በዚህ መርህ በአመለካከትም በተግባርም ከቀረበ ዛሬውኑ የቤት ሥራችን ተጠናቋል ማለት ነው፡፡ ስለዚህም የመንግሥት ሚና በዋናነት ሕገ መንግሥቱን ማስተማር፣ የዲን ዕውቀቱን በሚማሩበት ወቅት የሰላም፣ የፀጥታና የደኅንነት ጥበቃ ተደርጎ ሊሆን ይችላል፤ ይህም ሕገ መንግሥታዊ መብት የማስጠበቅ ግዴታ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሪፖርተር፡- ይኼንን የመንግሥት እንቅስቃሴ የሚቃወሙ መጅሊሱን በአግባቡ ያልተመረጠ ነው አይወክለንም፤ ተቋሙም ሕዝበ ሙስሊምን ለማገልገል አቅም የለውም የሚሉ ቅሬታዎች ያቀርባሉ፡፡ መንግሥት ደግሞ አክራሪ ያለውን ቡድን ለመነጠል ከአንደኛው ወገን ጋር ነው እየሠራ ነው ይባላል፡፡ የመንግሥት የወቅቱ ሚናና ፍረጃ ከዚህ ጋር ተጣምሮ የችግሩን አቅጣጫ አያባብሰውም ወይ? ዶ/ር ሽፈራው፡- መጅሊሱን አልተመረጠም በሚለው አቀራረብ የምርጫው ጊዜ እንዳለፈበት እኛም እናውቃለን፡፡ የምርጫው ጊዜ ያለፈበት መጅሊስ ቢሆንም፣ በመጅሊሱ ውስጥ ያሉ ሰዎች ግን በምርጫ የመጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመጅሊሱ ኃላፊነት ከመስጊድ ጀምሮ ነው የሚመጣው፡፡ አንድ ሰው ሲጎድልም በዚያው ነው የሚተካው፡፡ ስለዚህ አዲስ ሰው (ያለ ምርጫ) ወደ መጅሊሱ የሚመጣበት ዕድል የለም ማለት ነው፡፡ አሁን ያሉት ሰዎች መንግሥት ያመጣቸው ናቸው የሚል ፍረጃ አለ፤ የተሳሳተ ነው፡፡ በየክልሉ ከተመረጡ መጅሊሶች ውስጥ ነው የፌዴራል መጅሊስ የሚመጣው፡፡ ስለዚህ ፌዴራል ላይ እገሌ እገሌ ሁን ተብሎ የሚሠራ ነገር የለም፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን የዋህቢያ አካል መጅሊስን አናውቀውም፣ ስለዚህም በባላደራ ቦርድ ማደራጀት አለብን፣ የመጅሊስ መዋቅርም በምርጫ ሳይሆን በሹመት ነው መቀመጥ ያለበት እስከሚል ድረስ ነው የሚሄደው፡፡ መጅሊሱ ግን ሥርዓት ባለውና ሕዝበ ሙስሊሙን በሰፊው ባሳተፈ መንገድና ከመስጊድ ጀምሮ በሚመጣበት ሁኔታ ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን የሚያከብሩ ሰዎች በሚሳተፉበት አኳኋን መምጣት አለበት ብለን ነው የምናስበው፡፡ መጅሊሱንም በተለያዩ ጊዜያቶች ይህንን አቋም ያመላከተበት ጊዜ አለ፡፡ ሌላው መንግሥት ከመጅሊስ ጋር ለምን አብሮ ይሠራል? የሚል ነው፡፡ መንግሥት ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር አብሮ ይሠራል፡፡ አብሮ የሚሠራው ለምንድን ነው የሚለው ነው የሚለየው፡፡ መንግሥት አብሮ የሚሠራው በሚያገባው የሰላም፣ የልማትና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ያሉት ዜጎቻችን ናቸው ሌላ አይደሉም፡፡ እነዚህ ዜጎች (እምነቱ ውስጥ እንዳለው ሌላ ዜጋ) እምነታቸውና ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ ይፈልጋሉ፤ ከድህነትና ከኋላቀርነት እንዲላቀቁ ይፈልጋሉ፡፡ መንግሥት የሰላም ፍላጎት አለው፡፡ ሃይማኖቶችም የሰላም ፍላጎት አላቸው፡፡ ልማትም እንደዚሁ፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ በሚያገባው ይሠራል፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ሲባል እያስቀመጥን ያለነው፣ ‘ይህንን ሃይማኖት ነው የምትከተለው፣ ይህንን መጽሐፍ ነው የምትሰብከው’ በሚል ውስጥ ገብቶ ሃይማኖታዊና እምነት ነክ መንፈሳዊ ግንኙነት ላይ ገብቶ አይሠራም እንጂ፣ ከሃይማኖትና ከእምነት ተቋማት ጋር አብረን የምንሠራባቸው አጀንዳዎች የሉም ማለት አይደለም፡፡ ከእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም ጋር የሠራነው ሰላምና ልማትን በሚመለከት ነው፡፡ ይህንን በሚመለከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስና ከሌሎችም ጋር አብረን እንሠራለን፡፡ ሁላችንም የሚያገባን የአገር ጉዳይና የሃይማኖት ጉዳይ ስለሆነ አይደለም፡፡ ወደፊትም ከእነዚህ የሃይማኖት ተቋማት ጋር በሚያገባንና በሚያግባባን ጉዳይ ላይ የየራሳቸውን ድንበር ጠብቀን አብረን መሥራታችን አይቀርም፡፡ ምክር ቤቱ አቅም የለውም ለሚባለው የአቅም ችግር የዚሁ ምክር ቤት ብቻ አይደለም፡፡ እኛም እንደ መንግሥት አገራዊ ችግር ነው የምንለው፡፡ አለ የሚባለውን የአቅም ችግር ሕዝበ ሙስሊሙ ነው መጠገንና ማስተካከል ያለበት፡፡ ይኼ የሚጠገነው ደግሞ በምርጫ ወቅት ነው፡፡ ፊት ለፊታችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርጫ ይከናወናል፡፡ በዚያ መሠረት ሕዝበ ሙስሊሙ በአንድ በኩል አቅምንና ብቃት ያላቸውን፣ በሌላ በኩል ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌን የሚያከብሩና የሚያስከብሩ መሆናቸው የተረጋገጠላቸውን የሃይማኖት መሪዎች ወደ ምርጫው እንዲገቡና እንዲመረጡ በማድረግ የሚንቀሳቀስ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እየተሰጡ ያሉት ሥልጠናዎችም ተቋሙ አቅም ኖሮት የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ ሊፈታ በሚችልበት ደረጃ ላይ ለማምጣት እንዲያስችሉ ነው፡፡ ሪፖርተር፡- ዋህቢያና ሌሎች መንግሥት በአክራሪነት የፈረጃቸው ድርጅቶች ድጋፍ በብዛት የሚያገኙት ከሳዑዲ ዓረቢያና መሰል ዓረብ አገሮች ነው ብለውኛል፡፡ የአሁኑ ሁኔታና የመንግሥት ሚና ኢትዮጵያ ከእነዚህ አገሮች ጋር ባላት ግንኙነት ላይ ተፅዕኖ አይፈጥርም? ኢንቨስትመንት በመሳብ ደረጃም. . . .? ዶ/ር ሽፈራው፡- በሳዑዲም ይሁን በሌሎች የመንግሥት አካላት ላይ ይህ የመንግሥት አቋም ነው ብለን አንወስድም፡፡ አስተሳሰቡን በገንዘብ የሚደግፉ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ ብለን እናስባለን፡፡ በአንዳንድ ኤምባሲዎችም ውስጥ አንዳንድ ግለሰቦች ይህንን ጉዳይ ከራሳቸው ጥቅም ተነስተው ሊደግፉና ሊያንቀሳቅሱ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ከዋህቢያ ጋር የምናደርገው የፀረ አክራሪነት ትግል ከአገሮች ጥቅም ጋር የሚጋጭ ነገር የለውም፡፡ የራሳችንን ውስጣዊ ሰላማችን፣ የራሳችንን ሕገ መንግሥት ከማስጠበቅ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ወደየትኛውም አገርና የመንግሥት ሥርዓት ሄደን የቀሰርነው ጣት የለም፡፡ ስለዚህ የትኛውንም አገር የሚያስቆጣ ተግባር ነው ብለን አናምንም፡፡ እነዚህ ድጋፍ ያደርጋሉ ተብለው የሚገመቱ ሰዎች ደግሞ በአገር ለአገር ግንኙነት ላይ የሚፈጥሩት ተፅዕኖ ይኖራል የሚል እምነት የለንም፡፡ በኢንቨስትመንትም ላይ ችግር የሚፈጠረው ሰላም በሌለበት አገር ነው፡፡ ትግላችን ሰላማዊ የሆነ አገር ለመገንባት ነው፡፡ አንድ ኢንቨስተር የሚሄደው ሠርቶ አተርፋለሁ በሚለው አገር ላይ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ አገር ከማንም በላይ ሰላም ስትሆን ነው፡፡ ስለዚህ ከዋህቢያ ጋር እያደረግን ያለነው ትግል በዋነኛነት ሰላም እንዳይደፈርስ፣ ልማት እንዲበለጽግና ኋላቀርነት እንዲጠፋ ለማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ ለኢንቨስትመንትም ምቹ ሁኔታ መፍጠርና በሃይማኖት ሽፋን የሚመጡ አክራሪነትን፣ የፖለቲካ ተልዕኮን፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ነው እየተሠራ ያለው፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙን የማደናበር ሥራ እየሠሩ ያሉት አክራሪዎች ከጀርባቸው ሌሎችም ኃይሎች እንዳሉዋቸው አውቆ፣ ለሰላሙና ለደኅንነቱ ዘብ ሆኖ እንዲቆም፣ ችግሮች ሲኖሩም እየተመካከርን እንድንፈታ ነው መንግሥት የሚፈልገው፡፡ Read more
  • Media hula ye ethiopia muslim lay tenesa ende ? ሪፖርተሮች>>መንግሥት ጣልቃ ለመግባት ተገዷል ale

    የሙስሊሙ ማኅበረሰብን የሚያወዛግበው አክራሪነት ጣልቃ ገብነት ወይስ አስተምህሮ? SUNDAY, 18 MARCH 2012 00:00 BY HENOCK YARED , YEMANE NAGISH & SOLOMON GOSHU HITS: 853 View Comments ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በእስልምና ሃይማኖት ሥር ያሉ በዋህቢያንና በአሕባሽ አስተምህሮ የአካሄድ ልዩነታቸውን ቢያሳዩም፣ ልዩነቱ እየተካረረ በመሄዱ መንግሥት ጣልቃ ለመግባት ተገዷል፡፡ የቡድኖቹ መሠረታዊ ልዩነት ከዋነኛዎቹ የእስልምና አስተምህሮቶች (መዝሃብ) የተነሳ ቢሆንም፣ አንዱ አክራሪ ሌላው ለዘብተኛ ተደርጎ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ ቡድኖቹ በቁርአን፣ በሃዲስ (በነብዩ መሐመድ አስተምህሮት) ላይ ልዩነት የሌላቸው ሲሆን፣ በአተረጓጎምና በአስተያይ (ቂያስና ቂጅማ) ላይ እንደሚለያዩ ይነገራል፡፡ ከ7ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አንድ ሃይማኖት ከፖለቲካ፣ ከማንነትና ከባህል ጋር ቁርኝነት ያለው ቡድን ሆኖ ቢቆይም በቅርብ ዓመታት ከውጭ ሲታይ ሃይማኖታዊ የሚመስል ውስጡ ግን ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ልዩነት በሁለቱ ቡድኖች መካከል ተፈጥሯል፡፡ ይህ ልዩነት ዓለም አቀፋዊ እንጂ አገር በቀል እንዳልሆነም ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ ሪፖርተር ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ የታሪክ፣ የፖለቲካና የሕግ መነሻዎችን በማንሳት የሁለቱን ቡድኖች አለመግባባት ከራሳቸው አንደበትና የመንግሥትን ጣልቃ የመግባት ምክንያት ከመንግሥት አንደበት አንባቢው እንዲረዳ በሚከተለው መንገድ አቅርቦታል፡፡ በዓለም ታሪክ የመንግሥትና የሃይማኖት ተቋማት የእርስ በርስ ግንኙነት ጠንካራ በመሆን ለሺሕ ዓመታት ቆይቷል፡፡ በዚህም በአብዛኛው የመንግሥት ቢሮክራሲ አመራር በሃይማኖት ተቋማት የሚፀድቅበት ሁኔታ (The Divine Power Theory) ነበር፡፡ ሆኖም በዚህ የእርስ በርስ ግንኙነት በአንዱ ወቅት የመንግሥት ቢሮክራሲው በሌላ ወቅት የሃይማኖት ተቋማቱ የበላይነት የሚይዙበት ሁኔታ ነበር፡፡ በ15ኛው ክፍለ ዘመን የተቀጣጠለው የህዳሴ ንቅናቄ ለመጀመሪያ ጊዜ የሃይማኖት ተቋማት ከመንግሥት ተለይተው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ጠቁሞ ነበር፡፡ ይህም ሃይማኖት መንግሥት በሳይንስ፣ በትምህርትና በዲሞክራሲ ጽንሰ ሐሳቦች ላይ ትኩረት እንዳይሰጥ ይከላከላል ከሚል መነሻ ሐሳብ የተሰጠ ነበር፡፡ ነገር ግን ሃይማኖትና መንግሥት ተነጣጥለው መሥራት አለባቸው የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ተቀባይነት ለማግኘትና የሕግ መሠረት ለመያዝ ተጨማሪ መቶ ዓመታትን ጠይቋል፡፡ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን መጠናቀቅ ተከትሎ ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶችን ተቀባይነት ባላቸው መርሆዎች ለመምራት የተረቀቀውና እ.ኤ.አ. በ1945 ሥራ ላይ የዋለው የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር በአንቀጽ 1 ላይ ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ልዩነት/አድልኦ በዜጎች ላይ ሊፈጸም እንደማይገባ ያትታል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1948 የተረቀቀው ሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ በአንቀጽ 18 ላይ የዜጎች የሃይማኖት መብት የማመንን ብቻ ሳይሆን እምነትን የመቀየር፣ ሃይማኖትን የማስተማር፣ ተግባራዊ የማድረግ፣ የማምለክና የመከተል ነፃነትን ጭምር እንደሚያጎናጽፍ አረጋግጧል፡፡ የዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ ቃል ኪዳን በአንቀጽ 18(3) ላይ መንግሥታት የሃይማኖት ወይም የእምነት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ከሕዝብ ደህንነት፣ ሰላም፣ ጤናና ሞራል አንጻር እንዲሁም የሌሎች ዜጎችን መሠረታዊ መብቶች ለመጠበቅ ገደብ ሊጥሉ እንደሚችሉና በእነዚህ ሁኔታዎች የመንግሥታቱ ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት እንዳለው ይደነግጋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1981 የተረቀቀው ሃይማኖትና እምነትን መሠረት ያደረጉ ሁሉንም ዓይነት ያለመቻቻልና አድልኦ የማስወገድ የተባበሩት መንግሥታት ድንጋጌ በአንቀጽ 6 ላይ ዜጎች እንደ ግለሰብ የማመን፣ የማምለክና የመሰባሰብ መብት ብቻ ሳይሆን ሃይማኖታቸውን ወይም እምነታቸውን በቡድን የማስተማርና መሪዎቻቸውን የማሰልጠንና የመመደብ፣ በሃይማኖት ጉዳይ ከሌሎች ቡድኖች ጋር ግንኙነት የመፍጠር መብት እንዳላቸው ይገልጻል፡፡ በአጠቃላይ በዓለም አቀፍ ሁኔታ የሃይማኖት ወይም የእምነት መብት የማመን፣ ያለማመንና እምነትን የመቀየር መብት (The right to believe, unbelieve and disbelieve) የተረጋገጠ ሲሆን፣ ይህ የመብት ጥበቃ በመንግሥትና በሃይማኖት ተቋማት ተለያይቶ መሥራት ላይ (Secularism) የተመሠረተ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከላይ የገለጽናቸው ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ፈራሚ አገር ነች፡፡ መንግሥትና የሃይማኖት ተቋማት በአንደኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የገባው የክርስትና እምነት ከአራተኛው ክፍለ ዘመን እስከ 1967 ዓ.ም. ድረስ የመንግሥት ሃይማኖት በመሆኑ አገሪቱ ለሌሎች እምነቶች የምትመች እንዳልነበረች የታሪክ ድርሳናት ይጠቁማሉ፡፡ ደርግ በሕግ የሃይማኖቶችን እኩልነት ቢያረጋግጥም፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) በተመሠረተበት ጊዜ በመንግሥት ምክር ቤት ሥር የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስቴር አቋቁሞ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በተግባር ያን ያህልም ለውጥ እንዳልመጣም ይነገራል፡፡ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ዜጎች ማንኛውንም እምነት የመከተል መብት እንዳላቸው፣ ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል መሆናቸውንና ሃይማኖትና መንግሥት የተለያዩ መሆናቸውን በሕግም በተግባርም አረጋግጧል፡፡ ሕገ መንግሥታዊ ከለላም ያለው መብት ሆኗል፡፡ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሥርም የሃይማኖቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት አቋቁቋማል፡፡ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ለምን? የሃይማኖት ተቋማት የኅብረተሰቡን ሞራል፣ ሥነ ምግባርና መልካም እሴቶችን በማዳበር በጎ ተፅዕኖ በመፍጠር የመንግሥት አጋር መሆን ብቻ ሳይሆን የግለሰቦችን ነፃነትና ሰብዓዊ መብት በመግፈፍ በግለሰብና በማኅበረሰቡ ብሎም በመንግሥት ላይ አደጋ የመፍጠር አቅምና ጉልበቱ አላቸው፡፡ በዚህ ጊዜ የሚነሳው ትልቁ ጥያቄ የሃይማኖት ተቋማቱ መሪዎች በግለሰብ ደረጃ ወይም ደግሞ ተቋማቱ ይፋዊ በሆነ መንገድ በሃይማኖት ምክንያት የአገሪቱን ሕግ ከተላለፉ ከሕግ የበላይነት ሊያመልጡ ይችላሉ ወይ የሚል ነው፡፡ ሃይማኖቶች እርስ በርስና በአንድ ሃይማኖት ውስጥ የታቀፉ ቡድኖች ግጭት የተለመዱ ቢሆንም፣ ከሃይማኖት ቡድኑ ውጪ አገርን፣ ሰብዓዊ መብትን፣ የግለሰብና የቡድን መብትን፣ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ደኅንነትን የመንካት አቅሙ ሰፊ ነው፡፡ በተለይ ሃይማኖታዊ አክራሪነት የሃይማኖት መብት አካል የሆነውን ያለማመንና ትችት የመሰንዘር ብሎም ከነበረበት የሃይማኖት እምነት ወይም ቡድን የተለየ ግለሰብና ቡድን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጭቆናዎች ባለፉት 20 ዓመታት እየጨመረ በመምጣት የዓለም ስጋት እስከመሆን ደርሷል፡፡ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች እርስ በርስና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ በፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያኖችና አሁን በቅርቡ ደግሞ በእስልምና እምነት ሥር ያሉት የዋህቢያና የአሕባሽ ቡድኖች ግጭትን ለማብረድ የኢፌዴሪ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ለመግባት ተገዷል፡፡ ለመሆኑ የመንግሥት ጣልቃ መግባት ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ተቀባይነትስ አላቸው? 1. ብሔራዊ ደኅንነት ከላይ እንደተገለጸው መንግሥት የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ለመጠበቅ የሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ ሊገባ ይችላል፡፡ በእርግጥ በአንድ ሃይማኖት ውስጥ የተነሳው የሐሳብ ልዩነት የመንግሥትንና የሕዝብን ሰላምን ደኅንነት አደጋ ላይ ጥሏል ለማለት የሚቻለው መቼ ነው? ለሚለው ጥያቄ ግልጽ የሆነ ምላሽ የለም፡፡ ቢሆንም የግልጽና ተጨባጭ አደጋ መለኪያ (Clear and Imminent Danger Test) ወይም የአደገኛ አዝማሚያ መለኪያ (Dangerous Tendency Test) እንደ ሁኔታው ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ በአንድ ሃይማኖት ውስጥም ሆነ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ባሉ የሃይማኖቱ መሠረታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ያሉ አለመግባባቶች ላይ ሐሳብን በነፃነት መግለጽና መደራጀት ብሎም በአስተምህሮቶቹ ዙሪያ ደጋፊ የማሰባሰብ የውትወታ ሥራ (Advocacy) የሃይማኖት መብት አካል ቢሆንም፣ ነፃ የሐሳብ ልውውጡ የአገርን ሰላምና ደኅንነት አደጋ ላይ ወደሚጥል ተግባር የሚቀየር ከሆነ (Adversive Advocacy) የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሞኑ በሁለት የተለያዩ የእስልምና ቡድኖች መካከል ያደረገው ጣልቃ ገብነት ከደኅንነትና ሰላም ጋር ብሎም ከሽብርተኝነት ጋር የተገናኘ ማስረጃ አግኝቻለሁ ማለቱ የግልጽና ተጨባጭ አደጋ መለኪያን መጠቀሙንና የሐሳብ ልዩነቱ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚለውጥ መሆኑን በተጨባጭ ማረጋገጡን በመግለጽ ጣልቃ ገብነቱ ተቀባይነት እንዳለው እየገለጸ ነው፡፡ 2. የግለሰቦች መብት ጥበቃ ዜጎች የመረጡትን እምነት የመከተል መብት ያላቸው ከሆነ ይህ መብት በእምነቱ ላይ ያላቸውን የሐሳብ ልዩነት የማራመድ መብትንና ጭራሹን ያለማመን መብትን ይጨምራል፡፡ አሁን በሁለቱ የእስልምና ቡድኖች መካከል የሐሳብ ልዩነቱን የሚያራምዱት ቡድኖች አንዱ አንዱን ‹‹እስላም አይደለም›› እስከ ማለት መድረሳቸውን የሚገልጹት አስተያየት ሰጪዎች፣ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት የአገሪቱን ሰላም ከማስከበር ዘሎ ለእምነቱ ተከታይ ግለሰቦች የሕግ ከለላ በመስጠት መብታቸውን ሊያስከብር እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ በዚህም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ተቀባይ የሚሆንበት ተጨማሪ ምክንያት ይጠቁማሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት መጅሊስ የአሕባሽ ትምህርትን አምጥቶ ሥልጠና እንዲሰጥ የተገደደበት ምክንያት የዋህቢያ ፀረ ዜጎች እምነትና እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት ይንቀሳቀስ በሚል ነው፡፡ አቶ መረሳ ረዳ በፌዴራላዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖትና የእምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጄነራል በጉዳዩ ላይ ያስጠኑት ጥናት እንደሚያመለክተው፣ የዋህቢያ አስተምህሮ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ለተከሰቱ ሃይማኖታዊ ግጭቶች መሠረት መሆኑን ነው፡፡ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱንም የሚጥስ ነው፡፡ ለዚህም ነው መንግሥት ከመጅሊስ ጋር በመተባበር የአሕባሽ ትምህርት እየሰጠ ያለው፣ በአመለካከት ደረጃ የሙስሊሙን ኅብረተሰብ ንቃት ህሊና ከፍ ለማድረግ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ሰሞኑን በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ የሰጡት የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሬድዋን ሁሴን ይህንን አስመልክተው፣ ‹‹ችግሩ ሃይማኖታዊ አይደለም›› ያሉበትን እንዲህ በማለት አስረድቷል፡፡ ‹‹በሸሪዓ ሕግ ነው የምተዳደረው ብለህ ከተነሳህ፣ ሽፋኑ ሃይማኖታዊ ነው፡፡ ይዘቱ ግን ሃይማኖት አይደለም፣ ፖለቲካ ነው፡፡ የሸሪዓ መንግሥት መመሥረት ፖለቲካ እንጂ ሃይማኖት አይደለም፡፡ እስልምና በሸሪዓ ካልታገዝክ አይልም፡፡ በሸሪዓ የመተዳደር አጀንዳ የሥልጣን ፍላጎት እንጂ የእስልምና ግዴታ አይደለም፡፡ የሥልጣን ጥያቄ ነው፤›› ብለዋል፡፡ በሌሎች ሃይማኖቶችም በተለይ በኦርቶዶክስ ‹አንድ አገር፣ አንድ ሃይማኖት› የሚለው አስተሳሰብ በመጥቀስ፣ ‹‹ሽፋኑ ከእምነቱ ጋር ዝምድና የለውም፤›› ይላሉ፡፡ መንግሥት ዋህቢያ የሚባለውን እንቅስቃሴ እስላማዊ መንግሥትን መመሥረትን ጨምሮ የዜጎች ሕገ መንግሥታዊ የእምነት ነፃነት በመጣስ የራሱን ብቻ እንዲከተሉ የሚያስገደድ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ትምህርቱ ከሳዑዲ ዓረቢያ የመጣ ሲሆን፣ ሃይማኖትና ሥልጣን በጋራ ተደጋግፈውና ተስማምተው አንዱ ሌላውን ተሸክሞ የሚኖርበት መሆኑን ይገልጻል፡፡ የዋህቢያ ትምህርት፣ ባህላዊ የእስልምና እምነትን አስቀርቶ በቅዱስ ቁርአንና በኻዲስ ትምህርት የሚያምኑ አስተምህሮ መሆኑን የሚገልጹ ደጋፊዎቹ ደግሞ፣ የአሕባሽን ትምህርት ቅዱስ ቁርአን መሠረታዊ ማዕዘኖችን ይጥሳል በሚል ይቃወማሉ፡፡ መንግሥት፣ ከመጅሊስ ጋር በመሆን የአሕባሽ ሥልጠና ትምህርት መስጠቱ መፍትሔ እንደማይሆን ይገልጻሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ‹‹እስልምና ጉዳዮች›› እና ‹‹ሰላፍያ›› የመሳሰሉ ሚዲያዎች የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት አክርረው የሚቃወሙ ሲሆን፣ መንግሥት ከእምነት እጁን እንዲያወጣ ይጠይቃሉ፡፡ አቶ አደም ካሚል የተባሉት በሳዑዲ ዓረቢያ ላለፉት 30 ዓመታት የኖሩ ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ፣ በመንግሥት እየተፈጠረ ያለው ጥርጣሬና ችግር መነሻ የመጅሊስ ድክመት መሆኑን ለሪፖርተር ያስረዳሉ፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ መንግሥት ከሚለው በተቃራኒ የአሕባሽ ትምህርት መሠረታዊ የእስልምና እምነት የሚጻረር መሆኑን ነው፡፡ መፍትሔውም፣ መጅሊስ (እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት) ማጠናከርና በተማረ የሰው ኃይል እንዲሠራ ማድረግ ነው፡፡ እንደ እሳቸው እምነት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እስልምና መሠረት ያለውና የራሱ የፀና ትምህርት ስላለው በማናቸውም መጤ እምነቶች አይጠቃም፡፡ ዋህቢያ የሚባለው እምነት የለም የሚሉት እኚሁ ምሁር፣ አይዲዮሎጂው ግን ምንም ክፋት እንደሌለው ያስረዳሉ፡፡ መንግሥት አሕባሽ የተባለው አስተምህሮ ማምጣቱን በመቃወም፡፡ በአሁኑ ወቅት፣ በአወሊያ ትምህርት ማዕከል የተከሰተው ውዝግብ የዚሁ አካል ሲሆን፣ መንግሥት አንዳንድ ለውጦች ለማድረግና ሥርዓተ ትምህርቱን ለማድረግ የተንቀሳቀሰው የዋህቢያ ማፍለቂያ ቦታ ሆኗል በሚል ነው፡፡ የመንግሥትንና ሕገ መንግሥታዊ የዜጎች መብት የሚጥስ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በምክንያትነት እየጠቀሰ ሲሆን፣ መንግሥትን የሚቃወሙ በበኩላቸው በጣልቃ ገብነት እየወነጀሉ ነው፡፡ የአወሊያው ውዝግብ የሕዝበ ሙስሊሙን ወቅታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ለማፈላለግ የተወከልኩ ኮሚቴ ነኝ፤ በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ሙስሊሞች በተፈረመ ፒቲሺን ውክልና አለኝ፤ የሚለው ኮሚቴ በአወሊያ በየሳምንቱ ዓርብ መሰባሰብ ከጀመረ 10ኛ ሳምንቱን እንደያዘ ይናገራል፡፡ የኮሚቴው ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ መሐመድ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ጥያቄዎቻቸው የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ የአወሊያ ትምህርት ቤት በቦርድ ስለመመራትና የአሕባሽ አስተምህሮን በተመለከተ ነው፡፡ ‹‹አመራሮቹ የመጡት በ2001 ዓ.ም. ላይ ነው፡፡ የቀድሞዎቹ ሲታገዱ ባለአደራ ሆነው የመጡ እንጂ ውክልና ተሰጥቷቸው የመጡ አይደሉም፡፡ ዛሬ ነገ ምርጫ ይካሄዳል ቢባልም አልተካሔደም፤ የመጀመሪያው ጥያቄ ሕዝበ ሙስሊሙ የመረጣቸው መሪዎች ሊቀመጡ ይገባል የሚል ነው፡፡›› የአሕባሽ አስተምህሮን በተመለከተም፣ ‹‹አስተምህሮው ከእስልምና መሠረታዊ አስተምህሮ ወጣ ያለ ነው ብለን ነው የምናምነው፡፡ አስተምህሮው በራሱ በግሉ በአገሪቱ ውስጥ ሊንቀሳቀስና ተቋም መሥርቶ ሊያስተምር ይችላል፤›› ያሉት ኡስታዝ አቡበከር፣ አሕባሽ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የማይቀበለው አስተሳሰብ ነውና በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተቋም በሆነው መጅሊስ ከለላና መሪነት ይባስ ብሎ የማስገደድ ተግባር እየተፈጸመ ያለው የተወሰነ ፍላጎት ባላቸው የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት አጋዥነት ሳይቀር በየመስጂዱ የሚሰጠው ትምህርት እንዲቆም እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ አወልያ ተቋምን በተመለከተም አወልያ በሕዝብ ለረዥም ጊዜ ሲመራ ቆይቷል፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መጅሊስ (እስልምና ጉዳይ) ተረክቦታል፡፡ ከተረከበው በኋላ ተቋሙን የማሳደግ ተግባር አልፈጸመም፡፡ ተቋሙን የበለጠ ከማሻሻል ያሉበትን ችግሮች ከመቅረፍ ይልቅ አሠራሩን የመቀየርና ይባስ ብሎ የማዳከም ሁኔታ ታይቶበታል ያሉት ገጽታውን በማመልከት ነው፡፡ ‹‹አወሊያ የሙስሊሙ ብቸኛና ትልቁ ተቋም ነው፡፡ ቢያንስ በውስጡ መስጊድ፣ ኮሌጅ፣ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታል፣ የሕፃናት ማሳደጊያና ሁሉን ነገር የያዘ የተሟላ ተቋም ነው፡፡ ይህን የያዘ ተቋም አላግባብ ዕርምጃ ሲወሰድበት ሙስሊሙ ማየት ስለማይችል አገራዊ ጥያቄ ሆኖ መጥቷል፡፡›› የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ.ም. በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ስድስት ሰዓት የፈጀ ውይይት መደረጉን ያስታወሱት ኡስታዝ አቡበከር፣ በመድረኩ የተሰጠው ምላሽ የሚመስል ግን ማብራርያ የሚፈልግ ብዥታ እንዳለው የመጅሊስ ምርጫ ይካሄዳል ቢሉም መቼ እንዴት፣ በምን መልኩ ይካሄዳል? የሚያስመርጠውንስ ገለልተኛ ማን ይመርጠዋል ቢባል ምላሽ ያልተገኘበት በማለት ገልጸዋል፡፡ አወሊያን በተመለከተም ሕዝበ ሙስሊሙ የሚወክላቸው ሰዎችና ምሁራን በቦርድ እንዲመሩት ቢጠየቅም፣ ቦርዱን ማን ያስመርጣል? በሚለውም ስምምነት ላይ እንዳልደረሱና ድጋሚ ለውይይት ይጠራሉ ብንልም አልጠሩንም ብለዋል፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅልንም ጠይቀን ምላሽ እየጠበቁ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በወቅቱ በተፈጠረው ሁኔታ ስለዋህቢያም ይነሳል ብለን ለጠየቅነውም ሰብሳቢው ሲመልሱ፣ ‹‹ዋህቢያ ስል ተቋማዊ ሆኖ ባለቤት ይዞ የመጣ አካል ካለ ያ አካል ነው ባለቤት ሆኖ የሚቀርበው፤ ነኝ የሚል አካል ካለ ዋህቢያ ነኝ ብሎ ስለሚያምንበት ሴክት መግለጽና ማስረዳት ግድ ይለዋል፣ ይገባዋል ብለን ነው የምናምነው፡፡ እዚህ ባለው ግን በአሕባሽና በመጅሊስ ላይ ባለው ሒደት ውስጥ ዋህቢያ የሚል ነገር የለም፣ ከሙስሊም ማኅበረሰብ ጋር እየተካሄደ ያለ ተቋምን ወይም መሠረታዊ እምነትን በተመለከተ እየተደረገ ያለ ፍጥጫ እንጂ ከሌላ ሴክት (የእምነት ክፍል) ጋር የተያያዘ አይደለም፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡ በወቅታዊ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ ኡላማዎች ምክር ቤት አሕባሽ የሚባል ዲን (አስተምህሮ) እንደሌለ አስረግጦ ተናግሯል፡፡ ‹‹አሕባሽ የሚባል ዲን በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ በማንኛውም ዓለም የለም፡፡ አሕባሽ ማለት ኢትዮጵያውያን ከሚል የመጣ ነው፡፡ የኢትዮጵያዊ ሼኽ የሚከተሉ ወይም እርሱ ያስተማራቸው በሚል አሕባሽ መጣ እንጂ ዲን ማለት አይደለም፤›› በማለት አብራርቷል፡፡ ምክር ቤቱ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ ክልሎች እየተሰጠ ያለው ሥልጠናም የሙስሊሙን የዲን ዕውቀት ለማጐልበት ታስቦ ትክክለኛውን መንገድ እንዲይዙ ለማድረግ የተከናወነ እንጂ፤ አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት ሌላ እምነት ለመስበክ አይደለም፡፡ በምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሼክ ኢዘዲን አብዱል አዚዝ አገላለጽ፣ በትምህርት ሒደቱ ላይ በጠቅላላው ማስረጃ ተደርገው የተጠቀሱት ከቅዱስ ቁርአን ከኻዲስ፣ ከኢጅማዕና ከአራቱ መዛሂብ መሪዎች ሲሆን፣ ሥልጠናው እየተሰጠ ያለውም በፈቃደኝነት ነው፡፡ የኡላማዎች ምክር ቤት በኡላማዎች የሚሰጠውን ትምህርት የተከታተለ መሆኑን የገለጹት የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ እንዳሉት፣ ሥልጠናውን በአሁኑ ጊዜ መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት ነብዩ መሐመድ እንደገለጹት አፍራሽ የሆኑ አስተሳሰቦች፣ ብቃትና ዕውቀት የሌላቸው፣ ያለፉትን ኡላማዎች የሚያጣጥሉ ሰዎች የሚመጡበት ወቅት በመሆኑ ነው፡፡ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሔድ ምክር ቤቱ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ መወሰኑንና ምርጫው በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወን በመሆኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራው እየተካሔደ መሆኑንና ኅብረተሰቡም ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ያመለከተው የኡላማዎች ምክር ቤት፣ ለዚህ ምርጫ የሚመጡ ሰዎች ለሙስሊም ኅብረተሰብም ሆነ ለአገራችን የሚበጁ፣ ሙስሊም ኅብረተሰቡን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የማይወስዱ ሰዎች መሆን እንዳለባቸው ጥሪ አድርጓል፡፡ አወሊያ ትምህርት ቤት ግን እንደሌሎች ትምህርት ቤቶችና መስጂዶች ሁሉ በመጅሊስ መተዳደር ያለበት መሆኑን አስታውቋል፡፡ አያይዞም በአሁን ጊዜ ትምህርት ቤቱ መደበኛ ሥራውን እያከናወነ መሆኑን ተቋሙን ያስተዳድሩ የነበሩ ድርጅቶች የአገሩን ሕግ ተከትለው መሥራት ባለመፈለጋቸውና የሠራተኞችን ወጪ መሸፈን ባለመቻሉ የእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት በጀት መድቦ ሥራውን እንዲቀጥል ማድረጉን አብራርቷል፡፡ ትምህርት ቤቱ አፍራሽ ለሆኑ አስተሳሰቦች ሽፋን ሆኖ መቆየቱን የገለጸው የኡላማ ምክር ቤቱ መጋቢት 6 ቀን ባወጣው መግለጫ፣ ‹‹ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የሚነገረውንና የሚሠራውንም ነገር እያረጋገጠ መሄድ ይሻላል ነው የምንለው፤ ዝም ብሎ በተነሳው ወሬ ማጎብደድ አብሮ መጓዝ አይደለም፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ ወደ ግርግር የሚመሩ አንዳንድ ሰዎች አሉ፡፡ ወይ ለጥቅማቸው ሲሉ ወይ ደግሞ ከውጭ የሚያገኙትን ነገር ፍለጋ በሙስሊሙ ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ስላሉ እነዚህን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፤›› በማለትም አሳስቧል፡፡ (ለዚህ ዘገባ ኃይሌ ሙሉ አስተዋጽኦ አድርጓል) Read more
  • AHBASH & SUFIYA

    አህባሽ እና “ሱፊያ” ኡባህ አብዱሰላም ሰዒድ (I want all of you to compare this article with what “Majlis” and Alquds says about “Sufi”) በቅርቡ የአንድ ታላቅ መስጊድ ኢማም በሱፊያ ላይ ያተኮረ ኹጥባ ማድረጋቸውን ሰማሁ፡፡ ታዲያ አንዳንድ የፌስቡክ ጓደኞቼ ኢማሙ “እኛ ወሀቢዎች አይደለንም፤ እኛ ሱፊ ነን፤ አሁን ጊዜው የሱፊያ ነው፤ ሱፊያ ደግሞ የሰሀባዎችና የነቢያችን መንገድ ነው፤ ወዘተ...” ብለው ተናግረዋልና ስለዚህ ጉዳይ የምታውቂው ነገር ምን አለ?” የሚል ጥያቄ አቀረቡልኝ፡፡ በሰማሁት አባባል በእጅጉ ተገረምኩ፡፡ አዘንኩ!! ምን እንደማደርግም ግራ ገባኝ፡፡ ኢማሙ እንዲህ አይነት ተራ ንግግር በኹጥባ ላይ ማድረጋቸውን ለማመን ቢከብድም በራሴ መንገድ ባደረግኩት የማጣራት ሙከራ ነገሩ እርግጥ መሆኑን ተረዳሁ፡፡ በሌላ በኩል ለነዚያ ጓደኞቼ የሚሆን ምላሽ በዚያች ቅጽበት መስጠቱ ከበደኝ፡፡ ምክንያቱም የተሰውፍ መጽሀፍት በአጠገቤ የሉም (መካሺፉል ቁሉብ ከሚለው የኢማም አቡ-ሐሚድ አል-ገዛሊ መጽሀፍ በስተቀር)፡፡ በኢንተርኔት ላይ በተሰውፍ ስም የተለቀቁ ዌብሳይቶች ደግሞ ከጥቂቶቹ በስተቀር ምንም እምነት የሚጣልባቸው አይደሉም፡፡ ነገር ግን አህባሽ ሙስሊሞችን ከሚያጭበረብርባቸው ዘዴዎች አንዱ “እኛ ሱፊዎች ነን” የሚለው ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ ስለማውቅ ዝም ከማለት የቻልኩትን ያህል ልጻፍላቸው በማለት ተነሳሁ፡፡ ወደ ዋናው ጽሁፍ ከመግባታችን በፊት ግን መጠነኛ ማሳሰቢያ አለኝ፡፡ ይህንን ጽሁፍ ስጽፍ መነሻ የሆነኝ በአብዛኛው ድሮ ካነበብኩት ሀሳብ የተረፈኝ መጠነኛ እውቀት እንጂ በቅርብ ጊዜ ያነበብኩት መረጃ አይደለም፡፡ ስለዚህ የመረጃ ክፍተት ሊኖር እንደሚችል አምናለሁ፡፡ የጽሁፌን መልእክት ለማገናዘብ የሚፈልግ አንባቢያ ሰይድ አቡል-አእላ መውዱዲ የጻፉትን Towards Understanding Islam፤ አቡል ሐሚድ አል-ገዛሊ የጻፉትን አል-ኢሕያእ ኡሉሙድዲን እና መካሺፉል ቁሉብ፣ ሼኽ አብዱልቃዲር አል-ጄይላኒ የጻፉትን “አል-ጉንያ ሊጣሊብ ጠሪቀል ሐቅ”፣ ታዋቂው ገጣሚ ፈሪዱዲን አጣር የጻፈውን “ተዝኪራቱል አውሊያ” ወዘተ.. የመሳሰሉ መጽሀፍትን መመርመር ይችላል፡፡ ተሰውፍ “ተሰውፍ” (Sufism) በጥሬ ትርጉሙ “ሱፍ መልበስ” ማለት ነው፡፡ በተገቢው መንገድ ሲተረጎም ግን “የልብ ጥራት” ማለት ነው፡፡ ሙስሊም የሆነ ሰው ልቡ በአካሉ ከሚያደርገው ኢባዳ ጋር በእኩል ሁኔታ እንድትራመድለት ሲፈልግ ልዩ ልዩ ጥበባዊ ዘዴዎችን የሚማርበት መንገድ ነው- “ተሰውፍ”፡፡ ይህም ልብን ከልዩልዩ የልብ በሽታዎች ማጥራት ማለት ነው፡፡ በቁርአንና በሀዲስ በስፋት እንደተገለጸው ሰዎች ከፈጣሪ ጋር ያላቸውን ትስስር የምታበላሽባቸው አንዲት አካል አለች፡፡ እርሷም ልብ ናት፡፡ ሙእሚኖች ቁርኣናዊ ግዳጃቸውን በተገቢው መንገድ ለመወጣት ከፈለጉ ልባቸውን ከበሽታ ማጥራት አለባቸው፡፡ በሌላ በኩል ፈጣሪያችን አላህ (ሱ.ወ.) ለምንሰራቸው መልካም ስራዎች የሚከፍለንን ምንዳ (አጅር) የሚወስነው የልባችንን ጥራት በመመዘን ነው፡፡ በከፍተኛ የልብ ጥራት የአንድ ብር ሰደቃ የሰጠ ሰው ከፍተኛ ሽልማት አለው፡፡ ሰውየው መካከለኛ የልብ ጥራት ካለው ሽልማቱ ያንስበታል፡፡ የልብ ንጽህናው በጣም የጎደፈ ሰው ደግሞ ሽልማቱ እጅግ ዝቅተኛ ነው (ሰውዬው መቶ ብር ቢሰጥ እንኳ በንጹህ ልብ አንድ ብር የሰጠውን ሰው ያህል ሽልማት አያገኝም)፡፡ ልቡ ሙሉ በሙሉ የቆሸሸ ሰው ግን ከአላህ ዘንድ ምንም ሽልማት አያገኝም፡፡ እንግዲህ ይህንን የልብ ጥራት ማምጣት የሚቻለው እንዴት ነው? ኡለማ ለዚህ ጥያቄ የሚሆን ምላሽ ሲፈልጉ ነው “ተሰውፍ” የሚባለው አስገራሚ (አንዳንድ ጊዜ አወዛጋቢ) ኢስላማዊ የትምህርት ዘርፍ የተወለደው፡፡ ተሰውፍን እንደ አንድ የትምህርት ዘርፍ አድርጎ ማስተማር መቼ እንደተጀመረ በትክክል አይታወቅም፡፡ በርካታ ምንጮች ታዋቂዎቹን የበስራ ምሁራን ሐሰን አል-በስሪንና ራቢአቱል አደዊያን እንደ ጀማሪዎች ይጠቅሳሉ፡፡ ለመጀመሩ ሰበብ የሆነውም በጊዜው የነገሰው የልዩ ልዩ ፊርቃዎች (ሺዓ፤ ኻዋሪጅ፤ ሙርጂአ፤ ጀሀሚያ፤ ሙእተዚላ፤ ቀደሪያ፤ ጀብሪያ ወዘተ…) ሽኩቻ እንደሆነ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡ በተሰውፍ ላይ የሚያተኩሩ መጽሀፍት መጻፉንም ማን እንደጀመረው በርግጥ አይታወቅም፡፡ እንደሚመስለኝ ከሆነ የተሰውፍ መጽሀፍት መጻፍ የጀመሩት ከሂጅራ በኋላ በ4ኛው መቶ አመት ገደማ፤ ማለትም እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ900 አ.ል. በኋላ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በ10ኛው፤ በ11ኛውና በ12ኛው ክፍለ ዘመናት ፈሪዱዲን አጣር፤ አቡ ሀሚድ አል-ገዛሊ፤ አህመድ አል-ሪፋኢ፤ ሼኽ አብዱልቃዲር አል-ጁይላኒ ወዘተ… የመሳሰሉ ምሁራን በተሰውፍ ላይ ያተኮሩ በርካታ መጽሀፍትን አበርክተዋል፡፡ ተሰውፍና የልብ በሽታዎች ልባችን የሚቆሽሸው በተለያዩ በሽታዎች ነው፡፡ እነዚህ የልብ በሽታዎች ያሉበት ሰው ኢባዳውን በወጉ አያደርግም፡፡ ውሎውና ድርጊቶቹ ከኢስላማዊ አዳብ ጋር አይገጥሙለትም፡፡ ከግለሰቦችና ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ግንኙነትም የተስተካከለ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በዚህች አለም ብቻ ሳይሆን በወዲያኛውም አለም ታላቅ አደጋን ያስከትልበታል፡፡ ስለዚህ ከአደጋው ለመዳን ልቡን ከበሽታ ማጥራት ይጠበቅበታል፡፡ የሰውን ልብ ከሚያደርቁትና ኢማንን ከሚያጎድሉት በሽታዎች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡ ኒፋቅ፡- የሙናፊቅነት ስሜት ጡግያን፡- ጥመት ኪብሪያእ፡-ኩራት ጁብር፡ ትዕቢት ሪኣእ፡- ልታይ ልታይ ማለት ዘን፡- ከንቱ ጥርጣሬ ገፍላን፡- መሰላቸት ሻህዋእ፡- ከገደብ ያለፈ ስጋዊ ፍላጎት ወዘተ… አላህና መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ከነዚህ በሽታዎች እንድንጠቀቅ አስተምረውናል፡፡ የተሰውፍ ሰዎች ለነዚህ በሽታዎች የሚሆኑ መድሃኒቶችን ነው የሚያስተምሩት፡፡ የነዚህ መድሃኒቶች ምንጭ ቁርአንና ሱንና ነው፡፡ ልቡን ከነዚህ በሽታዎች ያጠራ ሰው ዒባዳውን በታላቅ ኹሹእ (የአላህ ፍራቻ) ማከናወን ይችላል፡፡ በተሰውፍ ከምንታከምባቸው መድሀኒቶች መካከል ከሁሉም የሚበልጠው “ዚክር” (አላህን ማስታወስ ) ነው፡፡ ቁርኣን “ልቦች በዚክር ይረጥባሉ” በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷልና!! እንግዲህ “ሱፊ” የሚባል ሰው ልቡን ከበሽታ ለመጠበቅ ሲል የተሰውፍን ጥበብ የሚከተል ማለት ነው፡፡ ይህ የተሰውፍ ጥበብ ደግሞ ከቁርአንና ከሀዲስ ጋር የማይጋጭ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ሰውየው ሌላውን ኢባዳ ትቶ ተሰውፍን ብቻ የሙጥኝ ብሎ መያዝ አይችልም፡፡ “ተሰውፍ” ሰውዬው በኢባዳ ላይ ብርቱ ሆኖ እንዲቆይ የሚረዱትን ጥበባዊ ዘዴዎች ያስተምረዋል እንጂ በራሱ የቆመ ለየት ያለ ኢስላማዊ ጎዳና ወይም የሸሪኣ ዘርፍ አይደለም፡፡ ማንም ሰው የተሰውፍ ዘዴዎችን ሳይማር ኢባዳውን ማድረግ ይችላል፡፡ “ልቤ በትእቢትና በኩራት ተወጥራለችና ምን ይበጀኛል?” ብሎ የሚጨነቅ ከሆነ መድሃኒቱን ከተሰውፍ መንገድ መፈለግ ይፈቀድለታል፡፡ እዚህ ላይ የታዋቂውን የሱፊ ጥበብ አዋቂ የሼኽ አብዱልቃዲር አል-ጄይላኒን ምሳሌዎች ልጥቀስ፡፡ ሼይኽ አል-ጄይላኒ “አል-ጉንያ ሊጣሊብ ጠሪቀል ሀቅ” በተባለ መጽሀፋቸው ውስጥ እንዲህ ይላሉ፡፡ መቼም ቢሆን አትማል፤ መማል ካስፈገለ ግን በአላህ ስም ብቻ ማል! በምላስህ አትዋሽ! ጥሩ ነገር ብቻ ተናገር! በመንገድህ ላይ በእድሜው ካንተ የሚያንስ ሰው ቢያጋጥምህ “ከርሱ የተሻልኩ” ነኝ ብለህ አታስብ፡፡ ከዚህ ይልቅ በልብህ “ይህ ልጅ በምድር ላይ የኖረበት ዘመን ከኔ እድሜ ያንሳል፡፡ ስለዚህ ሀጢአቱም ከኔ ያነሰ ነው” በል፡፡ በእድሜው ካንተ የሚበልጥ ሰው ከገጠመህ ደግሞ “ይህ ሰው በዚህች ምድር ላይ ከኔ እድሜ ለሚበልጥ ጊዜ ኖሯል፤ ስለዚህ ለአላህ ባደረገው ኢባዳ ከኔ ይበልጣል” በል እንጂ በመጥፎ ነገር አትጠርጥረወ፡፡ ደስ ይላል አይደል? ከማስደሰቱ ጋር መጠየቅ ያለበት ጥያቄ “ሼኽ አብዱልቃዲር የተናገሯቸው ነገሮች ከኢስላማዊው ሸሪዓ ጋር ይቃረናሉ ወይ?” የሚለው ነው፡፡ ሼኽ አብዱልቃዲር የጻፉት ነገር ከኢስላማዊ ሸሪዓ ውጪ አይደለም፡፡ ይልቅ ኢስላማዊ ሸሪዓን በትክክል ለመተግበር ያግዛል፡፡ ተሰውፍ ማለትም እንዲህ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ነው ሙስሊሞች ልባቸውን ከበሽታ የሚፈውሱባቸውን ልዩ ልዩ ምክሮች የሚሰጡ መጽሀፍት መጻፍ የተጀመሩት፡፡ አንዳንድ መምህራንም ሙሉ ጊዜያቸውን ለዚሁ ሰጥተው የማስተማሪያ ማእከላትን ያቋቋሙት ለዚሁ አላማ ነው፡፡ ተሰውፍ ሲበላሽ ጥንት በሰላማዊ ሁኔታ የተጀመረው ተሰውፍ ከዘመናት በኋላ መስመሩን ሳተ፡፡ ሰዎችን በሸሪአ ላይ የሚያበረታታ መሆኑ ቀርቶ ከሸሪአ የሚያስወጣ መሆን ጀመረ፡፡ ለምሳሌ፤ በተሰውፍ ስም ከሸሪአ ጋር የሚቃረኑ ተግባራትን መፈጸም ተጀመረ፤ ዳንስና ሙዚቃ እንኳ በተሰውፍ ስም ተፈቀዱ (ለምሳሌ በቱርክ ያሉትና “Whirling Dervishes” የሚባሉት የመውላዊ ጠሪቃ ተከታዮች የሚያደርጉትን የዳንስ ትርኢት “ዚክር” ነው ይሉታል፡፡ አስተግፊሩላህ!!) እንደ አል-ሀለጅ እና ኢብን አረቢ የመሳሰሉት “ሱፊ” ነን ባዮች ደግሞ ግልጽ የወጣ ኩፍር ውስጥ የሚያስገቡ ፍልስፍናዎችን በተሰውፍ ስም መጻፍና ማስተማር ጀመሩ፡፡ ለምሳሌ አለ-ሀለጅ “ማነው ሀቅ?” በሚል ጥያቄ ጀመረና “አነል ሀቅ”፤ ማለትም “አል-ሀቅ እኔ ነኝ” የሚል ፍልስፍና ላይ ደረሰ፡፡ እኛ ሙስሊሞች “አል-ሀቅ” የምንለው አላህን ብቻ ነው፡፡ ሰውዬው ግን ራሱን “አል-ሀቅ” ብሎ ጠራ፡፡ ይህንን እንዲተው ቢመከር እንቢ አለ፡፡ በዚህም የተነሳ በጊዜው የነበረው የባግዳድ ኸሊፋ በስቅላት ቀጣው፡፡ ከአይሁድና ክርስቲያን መነኮሳት ጋር የተቀራረቡ ሙስሊሞች በበኩላቸው በተሰውፍ ስም ምንኩስናን ወደ ኢስላም አስገቡ፡፡ አንዳንዶቹ ተሰውፍን ከልብ ንጽህና አርቀው ከአላህ ጋር በቀጥታ የምንነጋገርበት ጥበብ ነው እያሉ ከሸሪዓው ያነፈገጡ የግጥም ውዳሴዎችን የሚያቀርቡበት መድረክ አደረጉት፡፡ አንዳንዶቹ ከዚህም ራቅ ብለው ተሰውፍን ከአላህ በስተቀር ማንም ሊደርስበት የማይችለውን ስውር አለም (ገይብ) የሚመረምሩበት መነጽር አደረጉት፡፡ ተሰውፍ ኢስላማዊ ባህልን መከተል ሲገባው የባእዳን ባህል ተከታይ የሆነበት ሁኔታም ተፈጠረ፡፡ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ ነገሩ ሁሉ ተቀየረና “ተሰውፍ” የአውሊያ መቃብሮች የሚመለኩበት የሽርክ ጋሻና መከታ ሆነ፡፡ ተሰውፍ በስተመጨረሻው ላይ እንደዚህ ውጥንቅጡ የወጣ ዝባዝንኬ ነገር ሆነ፡፡ ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነው “ጠሪቃ” እና “ሀድራ” የሚባሉ ነገሮች መከሰታቸው ነው፡፡ “ጠሪቃ” የተሰውፍ ዚክር ከአንዱ ሼኽ ወደሚቀጥለው ሼኽ የሚተላለፍበት መንገድ ነው፡፡ በጠሪቃው ውስጥ የሚታቀፉት ሼኾች እንደ ተማሪና መምህር ሳይሆን እንደ ጌታና ባሪያ ነው የሚተያዩት፡፡ ሀድራ ደግሞ አንድ ሼኽ ዚክርን የሚያስተምርበት ማእከል ማለት ነው፡፡ በኋላ ላይ ግን ሼኹ ራሱ የሚመለክበት ማእከል ሆኖ ተገኝ፡፡ ከዚህ ሌላ የሀድራ ሼኾች ራሳቸውን ወደ ፈውዳላዊ ባላባቶች እየቀየሩ ሀብት ያግበሰብሱ ገቡ፡፡ እነዚህን አላማዎች የሚደግፉላቸውን የቅጥፈት ወሬዎች፤ ተረቶች፤ ታሪኮች ወዘተ ማስወራት ጀመሩ፡፡ አላህ በቁርአኑ የተናገረው “የአላህ አውሊያ” የሚለው አባባል ትልቅ የማጭበርበሪያ ዘዴ ሆነ፡፡ በዚህ ውጥንቅጡ የወጣ ሁኔታ ውስጥ ነው በርካታ የተቃውሞ ድምጾች በተሰውፍ ላይ የተነሱት፡፡ ከነዚህ ድምጾች መካከል በጣም ከፍ ብሎ የተሰማው የሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ ድምጽ ነው፡፡ ሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ በተሰውፍ ስም የሚነገድበትን አይን ያወጣ ኩፍር፤ ሽርክ፤ ቢድአና ባእድ አምልኮ በሀይለኛ ሁኔታ ተቃውሟል፡፡ ነገር ግን ኢብን ተይሚያህ አሁን እንደሚባለው ተሰውፍን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አላደረገውም፡፡ ሙስሊሞች በዚክር ከልብ በሽታ የሚፈወሱበትን “ተሰውፍ” በእጅጉ ደግፏል፡፡ ኢብን ተይሚያህ እነ ሼይኽ አብዱልቃዲር አል-ጀይላኒ ያስተማሩትን እውነተኛ ተሰውፍ በጣም ያበረታታ ነበር፡፡ እርሱ የተቃወመው በተሰውፍ ስም የሚካሄዱትን ከላይ የገለጽኳቸውን አስነዋሪ የሆኑ ኢ-ኢስላማዊ ድርጊቶችና አመለካከቶችን ነው፡፡ አህባሾችና የተሰውፍ አመለካከታቸው ከላይ የቀረበውን ትንተና ያነበበ ሰው አህባሾች በተሰውፍ ላይ ያላቸውን አመለካከት በቀላሉ ይረዳል ብዬ አምናለው፡፡ ስለዚህ ነገሩን በዚሁ እናሳጥረው፡፡ ለመሰናበቻ አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡ በተለምዶ “ገሪባ” ሲባል ሰምታችኋል? ምን ማለት ነው? አህባሾች “ሱፊ” የሚሉት ልቡን ከበሽታ ለማንጻት የሚታገለውን እውነተኛ ሱፊ ሳይሆን ነፍሱን ለሼይኽና ለአውሊያ አምልኮ የሰጠውን እንደ “ገሪባ” አይነት ሰው ነው፡፡ የአውሊያ መቃብሮችን በየጊዜው እንድንዘይርና እንድንስም ለማድረግ ሲባል አህባሾች እንደ ምክንያት ከሚያቀርቡልን ሰበቦች አንዱ “ተሰውፍ” ነው፡፡ ነኡዙ ቢላህ!! በተሰውፍ ስም ግልጽ ሽርክ?? አላህ ከሽርክ ይጠብቀን!! በተሰውፍ ስም ሽርክን ከሚያበረታቱ አሳሳቾችም ይጠብቀን!! አሚን!!! Read more
  • በትግራይ ክልል መሆኒ ከተማ ኢማሙ ባልታወቀ ምክኒያት ታሠሩ

    ኢማሙ ትላንት የጁምዓ ሠላት ከተሰገደ በኃላ ነው ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ያዋሏቸው፡፡ የሬዲዮ ቢላል ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት ከዛሬ 6 ዓመት በፊት በከተማዋ በሚገኘው ዋና መስጂድ መሰገድ በመከልከላችን ሣቢያ አንድ ባለሀብት ቤት ውስጥ ለ4 ዓመታት በመድረሳም በመስጂድም መልክ ስንጠቀምበት ብንቆይም በየግዜው የሚመነጡት ማስፈራሪያዎች ስጋት ጥሎብናል ብለዋል፡፡ ኃላም ይህ እየሰገዳቹ ያላችሁት ቤት እውቅና የለውም በሚል እንደወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ ኢማሙ የታሰሩበትንም ምክኒያት ሲያስረዱ እናንተ አሸባሪዎችና ዋሃቢዮቸ ናችሁ በሚል ምክኒያት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ Read more
  • መጅሊስ ሠላማዊ ትግሉን ለመበተን ግብረኃይል እያቋቋም ነው

    የሚካሄደውን የሕዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል ለመበተን የሚያስችለውን ግብረ ኃይል እያደራጀ መሆኑ ተገለፀ፡፡ መጅሊሱ ዛሬ ጦርኃይሎች በሚገኘው ቅጥር ግቢው ከመዲናዋ የተለያዩ መስጂዶች ኢማሞች ጋር ባካሄደው ውይይት እንዳስታወቀው እየተጠናከረ የመጣውን የሕዝቡን ተቃውሞ ለመበተን የሚየስችል እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ባውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት የተለያዩ ኢማሞችና ዱዓቶች ሥራ መሰራቱን ለሬዲዮ ቢላል አስታውቀዋል፡፡ ለደህንነታችን እንደሰጋለን ያሉ አስተያየት ሰጪዎቻችን እንዲገልፁት የመጅሊሱን እንቅስቃሴና የስብሰባ አጀንዳ ግልፀኝነት እንደሚጎድለው አመልክተዋል፡፡ዛሬ ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ የሼህ አብደላ አልሃረሪ መፀገፎች መበተናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በስብሰባው በርካታ ወጣት ዳዒዎች፣ዑስታዞች እንዳይሳተፉ ታግደዋል፡፡ተሳታፊዎቹ የተመረጡት በመጅሊሱ አመራሮች መሆኑንም ታማኝ ገልጸዋል፡፡ Read more
  • Ethiopian Woman Beaten on Camera Kills Herself

    Ethiopian Woman Beaten on Camera Kills Herself, Community Appeals for Help Published by Tadias March 14th, 2012 in Featured. 0 Comments TV broadcast shows 33-year-old Alem Dechasa being forced into a car outside the Ethiopian consulate in Lebanon. (LBC) Tadias Magazine News Update Wednesday, March 14, 2012 New York (TADIAS) – The Ethiopian domestic worker that was violently mistreated outside the Ethiopian embassy in Beirut, as shown in a viral video last weekend, has committed suicide, Ethiopia’s Consul General confirmed to local media in Lebanon. Alem Dechasa, 33, hanged herself using her bed sheets Wednesday morning, the Daily Star newspaper reported. “My body is shaking and my heart is broken” said Ms. Zewditu Fessehaa, Chairwoman of the Ethiopian Social Assistance Committee in New York City, whose organization has been mobilizing efforts to assist the victim. “It’s depressing, it’s very sad and it’s unfair. She added: “As a mother I want to appeal to the Prime Minister of Ethiopia to do something. Our daughters are being treated like dogs and there is nothing we can do about it.” Ethiopian General Consul Asaminew Debelie Bonssa spoke to the Daily Star following a visit to the hospital where she killed herself. According to the newspaper, the Ethiopian consulate official said he saw Alem Dechasa Saturday and she appeared fine. The diplomat also said doctors told him they checked on her at 5 a.m. this morning and when they returned at 6 a.m. she was dead. Bonssa said he was ‘deeply shocked’ by the news.” In New York, the ESAC chairwoman called for a collective response. “I want to appeal to everyone. We need to pull together to stop this madness,” Ms. Fessehaa said. “The cruelty directed against domestic workers is a human rights issue.” She added: “It needs an in-depth understanding, and an innovative solution within and beyond the Ethiopian community. We need people from every profession to assist us to make sure that our sister did not die in vain.” Meanwhile, a vigil to mourn Alem Dechasa’s death is scheduled in front of the Lebanon embassy on Thursday, at 11 AM in Washington D.C. – Read more
  • Top Secret Dcouments mejlis's role in Arart-Kilo mosques demolition

    Elias Redman justifies the demolition of the Arart-Kilo mosques which angered Muslims followed by peaceful demonstration,accusing the Muslims chanting against Meles Zenawi during the protest! He also claims that he secured and alternative peace of land to contain the anger. C) Sheikh Elias discussed the recent unrest in Addis Ababa sparked by the destruction of a mosque in the central area of Arat Kilo (reftel), saying what was reported in newspapers was only partially correct. He explained the property on which the mosque was to be constructed was purchased by an individual who received money from a Saudi NGO (an NGO is not legally able to purchase property) at Arat Kilo. The property had contained a residence and a building permit was granted to renovate the house. Regardless, the new owner proceeded to illegally build a mosque and fence around the original structure, which led to city officials demolishing the newly built mosque. This resulted in large scale demonstrations in Addis Ababa on three consecutive Fridays. The largest clash took place on August 11, for which police were called, resulting in a clash between rock-throwing Muslim protestors and police. (NOTE: Only minor injuries and no deaths were reported in this demonstration. END NOTE) The Sheikh reported that, prior to the break-up of the demonstration, some protestors were calling for PM Meles Zenawi to step down and for the establishment of an Islamic government. (C) Sheikh Elias met with Addis Ababa Mayor Berhanu Deressa to diffuse the issue. The mayor agreed to grant the EIASC a larger tract of empty land on which to build a mosque near Addis Ababa University, not far from the original site. The Sheikh called for the community to relinquish the property at Arat Kilo and to focus efforts towards building a new mosque. The Sheikh reported that hardliners criticized and blamed the EIASC for the destruction of the mosque. Nevertheless, the Sheikh said that the wider Muslim community was satisfied with the new grant of land and there have been no reports of demonstrations since. FULL DOCUMENT HER Read more

Latest Articles

Most Popular